Friday, March 24, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

መንግሥት የውጭ ኩባንያዎች የምግብ ፍጆታዎች እንዲያቀርቡ ፈቀደ

- ማስታወቂያ -

ተዛማጅ ፅሁፎች

እየተባባሰ የመጣውን የዋጋ ግሽበት ለማስታገስ መንግሥት የውጭ ኩባንያዎች የምግብ ሸቀጦች በጅምላ እንዲያቀርቡ ፈቀደ፡፡

የገንዘብ ሚኒስቴር ስንዴ፣ ዘይትና ስኳር የሚያቀርቡ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች በቅርቡ በሚያወጣው ማስታወቂያ ይጋብዛል፡፡ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ፣ ከንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር፣ ከገንዘብ ሚኒስቴርና ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የተውጣጡ ኃላፊዎች የሚገኙበት ኮሚቴ ኩባንያዎቹ የሚያቀርቡትን ዕቅድ እንደሚገመግም ታውቋል፡፡ የተመረጡት ኩባንያዎች ስንዴ፣ ዘይትና ስኳር በጅምላ ለአገር ውስጥ ገበያ እንደሚያቀርቡ ተገልጿል፡፡

መንግሥት የኑሮ ውድነቱን ለመቀነስ ስንዴ፣ ዘይትና ስኳር ከውጭ በመግዛት በተመጣጣኝ ዋጋ ለኅብረተሰቡ እንደሚያከፋፍል ይታወቃል፡፡ ለዚህም በየዓመቱ ለድጎማ ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ ይመድባል፡፡ ይሁን እንጂ በተለይ የዘይት ማስገባትና ማከፋፈል ንግድ በተወሰኑ ግዙፍ ድርጅቶች በመያዙ፣ በዋጋ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ እንደሚያሳድሩ ምንጮች ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

ስንዴ፣ ዘይትና ስኳር ለአጠቃላይ የአገሪቱ ዋጋ ግሽበት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያደርጉ፣ የኑሮ ውድነቱን ለማባባስ የእነዚህ የምግብ ሸቀጦች አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን፣ የተወሰኑ አስመጪና አከፋፋዮች የተቆጣጠሩት የምግብ ሸቀጥ ንግድ ከአንድ መቶ ፐርሰንት በላይ ትርፍ የሚያጋብሱበት በመሆኑ ኅብረተሰቡ ላይ ጫና ሲፈጥር መቆየቱን፣ ይህን ያልተገባ የንግድ ሥርዓት መንግሥት መለወጥ እንደሚያስፈልግ የገለጹት ምንጮች፣ ተወዳድረው የሚመረጡት ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች ስንዴ፣ ዘይትና ስኳር በመንግሥት የማከፋፈያ አውታሮች በጅምላ እንዲያቀርቡ እንደሚደረግ አስረድተዋል፡፡

የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ በነሐሴ 2010 ዓ.ም. ያወጣው ሪፖርት በሰኔ ወር በምግብ ዋጋ ላይ 19.6 በመቶ፣ በሐምሌ ወር 20.1 በመቶ የዋጋ ግሽበት እንደተመዘገበ ይጠቁማል፡፡ አጠቃላይ አገራዊ የዋጋ ግሽበት 15.6 በመቶ እንደደረሰ ሪፖርቱ ያመለክታል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች