Thursday, June 8, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየተዛባ የአመጋገብ ሥርዓት ችግሮችን ዜሮ የማድረግ እንቅስቃሴ

የተዛባ የአመጋገብ ሥርዓት ችግሮችን ዜሮ የማድረግ እንቅስቃሴ

ቀን:

በተመስገን ተጋፋው

ኢትዮጵያ በምግብ እጥረትና በተዛባ የአመጋብ ሥርዓት ምክንያት የሚከሰቱ ችግሮችን በ2022 ዓ.ም ዜሮ ለማድረግ ዓለም አቀፍ የሥርዓተ ምግብ ማስፋፋት ንቅናቄን ‹The scaling up Nutrition (Sun) Movement› እ.ኤ.አ. በ2012 ተቀላቅላለች፡፡ ንቅናቄውን አገር አቀፍ የሰቆጣ ስምምነት በሚል መሪ ቃል ስትቀላቀል ከሁለት ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትን ቅንጨራ በጥቂት ዓመታት ውስጥ ዜሮ ለማውረድ ነበር፡፡

እስካሁን በተሠሩ ሥራዎች የማይናቅ ለውጥ ማስመዝገብ ቢቻልም ቅንጨራን ዜሮ ለማድረግ ግን ገና ብዙ ርቀት እንደሚቀር መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ የኢትዮጵያ የምግብ መሪዎች ኔትዎርክ ከፍተኛ የሥርዓተ ምግብ ባለሙያዎች፣ የመንግሥት ተቋማትና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በተገኙበት ኅዳር 14 ቀን 2012 ዓ.ም. በካፒታል ሆቴል በጉዳዩ ውይይት አካሄዷል፡፡

በመድረኩም መንግሥት አጋር ድርጅቶችን በማስተባበር ባለፉት አሥር ዓመታት በሥርዓተ ምግብ ዙሪያ ትኩረቱን አድርጎ በመሥራቱ በምግብ እጥረትና በተዛባ የአመጋገብ ሥርዓት ችግር ምክንያት የሚጠቁ ሕፃናት ቁጥርን በከፍተኛ ደረጃ ለመቀነስ መቻሉን፣ የሥርዓተ ምግብ መሪዎች ኔትዎርክ ኃላፊ ወ/ሮ እስራኤል ኃይሉ ተናግረዋል፡፡

በተለይም የመቀንጨር ችግርን ባለፉት አሥር ዓመታት ውስጥ ከ58 በመቶ ወደ 37 በመቶ መቀነስ መቻሉን ወ/ሮ እስራኤል አስረድተዋል፡፡ የተመዘገበው ውጤት ይበል የሚያሰኝ ቢሆንም የሥርዓተ ምግብ ችግር ካለባቸው አገሮች መካከልም አሁንም ኢትዮጵያ አንዷ እንደሆነች ኃላፊዋ ጠቁመዋል፡፡  

የሥርዓተ ምግብ አመራር ትግበራን ለማሳለጥና አገሪቱ የገባቻቸውን በሥርዓተ ምግብ መዛባት ምክንያት የሚከሰቱ የጤና ቀውሶችን ዜሮ ለማድረግ የተነደፉትን  ዕቅዶች ተግባራዊ በማድረግ ቁርጠኛ፣ ታታሪና ተፅዕኖ ፈጣሪ የሆኑ የሥርዓተ ምግብ መሪዎችን ከከፍተኛ አመራሩ እስከ ማኅበረሰቡ ድረስ በማፍራት ሁሉም የድርሻውን በመወጣት ኢትዮጵያ ከምግብ እጥረትና ከሥርዓተ ምግብ መዛባት ችግር ነፃ እንድትወጣ መረባረብ ያስፈልጋል በማለት ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ድርጅቱም ኅዳር 14 ቀን 2011 ዓ.ም. የመጀመርያ የሆነው የምግብና የሥርዓተ ምግብ ፖሊሲ አፅድቆ ወደ ትግበራ ለመግባት ዝግጅቱን በማጠናናቀቅ ላይ እንደሚገኝ በውይይቱ ላይ ተነግሯል፡፡

ሰላሳ ለሚሆኑ ኢትዮጵያውያን የሥርዓተ ምግብ ባለሙያዎች ሥልጠና እንደተሰጠ የሥርዓተ ምግብ መሪዎች ኔትዎርክ ምክትል ኃላፊ አቶ አፈወርቅ ሙሉጌታ ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ ያለችበትን የሥርዓተ ምግብ መዛባት ለማስተካከል ድርጅቱ ዕቅዶችን ነድፎ መንግሥታዊ ከሆኑ ድርጅቶችና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር አብሮ እየሠራ እንደሚገኝ አቶ አፈወርቅ ተናግረዋል፡፡

የምግብና የሥርዓተ ምግብ ጉዳይ ዓለም አቀፍ አኅጉራዊና አገራዊ ጉዳይ በመሆኑ፣ ሁሉም አገሮች ርብርብ በማድረግ መሥራት እንደሚገባቸው አቶ አፈወርቅ ገልጸዋል፡፡ ለዚህም ችግር አብኛውን ጊዜ ተጋላጭ የሚሆኑት የአፍሪካ አገሮች በመሆናቸው ሁሉም እጅና ጓንት ሆነው መሥራት እንደሚገባቸው ገልጸዋል፡፡ መንግሥትም የምግብና የሥርዓተ ምግብ ችግሮችን ለመቀነስ ትኩረት አድርጎ መሥራት ይገባል በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡   

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ከቀጣዩ ዓመት በጀት ውስጥ 281 ቢሊዮን ብሩ የበጀት ጉደለት ነው ተባለ

ለቀጣዩ በጀት ዓመት ከቀረበው 801.65 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ በጀት...

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ከተለመደው አሠራር ወጣ ያለውን ‹‹የወደፊት ግብይት›› ሥርዓት በይፋ አስጀመረ

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ከተለመደው የማገበያየት ተግባሩ ወጣ ያለና በኢትዮጵያ...

የባንክ ማቋቋሚያ መሥፈርት እንደሚጠነክር ሚኒስትሩ ተናገሩ

 ባንኮች ስለውህደት እንዲያስቡም መክረዋል በኢትዮጵያ ውስጥ ባንክ ለማቋቋም የሚያስፈልገው መሥፈርት...