Sunday, June 4, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜና‹‹ብልፅግና ፓርቲ ሕዝብን የሚጠቅም ሐሳብ ከማንኛውም ወገን ለመቀበል ዝግጁ ነው›› ጠቅላይ ሚኒስትር...

‹‹ብልፅግና ፓርቲ ሕዝብን የሚጠቅም ሐሳብ ከማንኛውም ወገን ለመቀበል ዝግጁ ነው›› ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር)

ቀን:

እሑድ ኅዳር 21 ቀን 2012 ዓ.ም. የብልፅግና ፓርቲን ለመመሥረት የኢሕአዴግ ሦስቱ አባል ድርጅቶችና አምስቱ አጋር ድርጀቶች ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡ የኢሕአዴግ መሥራች የነበረው ሕወሓት ውህድ ፓርቲውን አለመቀላቀሉን በይፋ ማስታወቁ የሚታወስ ሲሆን፣ ስምንቱ የብልፅግና ፓርቲ መሥራቾች ግን ፊርማቸውን አኑረዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ከፊርማ ሥነ ሥርዓቱ በኋላ ባደረጉት ንግግር፣ አዲሱ ውህድ ፓርቲ ኢትዮጵያን ካለችበት ሁኔታ ወደ ብልፅግና ጎዳና የሚያሸጋግር የአሥር ዓመት ዕቅድ ተዘጋጅቶለታል ብለዋል፡፡ ውህደቱን በተመለከተ ሲያስረዱም፣ ‹‹የኢሕአዴግ አደረጃጀት ለውጥ ያስፈለገው በፅኑ የታመመ በመሆኑ ነው፤›› ብለው፣ ‹‹ከውስጥ የለውጥ ሐሳብ ባይመጣ ኖሮ አገራዊ ኪሳራ ያጋጥም ነበር፤›› ሲሉ አክለዋል፡፡ ‹‹የውህደት ጉዞው ሕግና ሥርዓት ጠብቆ በአስተማማኝ ሁኔታ ይቀጥላል፤›› ሲሉም አስረድተዋል፡፡ ብልፅግና በሕግና በዕውቀት የሚመራ በእውነት ላይ የቆመ ድርጀት እንጂ፣ እንዲሁ ግሰቦች ተሰብስበው የፈጠሩት ድርጅት አይደለም ብለዋል፡፡ ዘመኑን የሚመጥን አደረጃጀት አስፈላጊ መሆኑን፣ ብልፅግና ፓርቲን ለመመሥረት የተደረገው ሒደት ትክክለኛ እንደነበር፣ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡ ለዚህም ሲባል ውህዱ ፓርቲ ዴሞክራሲና ልማትን አጣምሮ ይይዛል ብለዋል፡፡ ‹‹ብልፅግና ፓርቲ በሕግና በደንብ የሚመራና ሕዝብን የሚጠቅም ሐሳብ ከማንኛውም ወገን ለመቀበል ዝግጁ ነው፤›› ሲሉ አስታውቀዋል፡፡ የፊርማ ሥነ ሥርዓቱ ላይ በመገኘት ሦስቱ የኢሕአዴግ ድርጅቶችና አምስቱ የአጋር ድርጅቶች ሊቃነ መናብርት ውህደቱን የሚያፀድቀውን ፊርማቸውን አኑረዋል፡፡ በሥነ ሥርዓቱ ላይ ሚኒስትሮች፣ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮችና ጥሪ የተደረላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

አወዛጋቢው የሕገ መንግሥት ማሻሻያ ጉዳይ

በኢትዮጵያ የሕገ መንግሥት ማሻሻል ጉዳይ ከፍተኛ የፖለቲካ ውዝግብ የሚቀሰቀስበት...

 መፍትሔ  ያላዘለው  የጎዳና  መደብሮችን  ማፍረስ

በአበበ ፍቅር ያለፉት ስድስት ዓመታት በርካቶች በግጭቶችና በመፈናቀሎች በከፍተኛ ሁኔታ...

የተናደው ከቀደምቱ አንዱ የነበረው የአዲስ አበባ ታሪካዊ ሕንፃ

ዳግማዊ አፄ ምኒልክ በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ መናገሻ ከተማቸውን...

የአከርካሪ አጥንት ሕክምናን ከፍ ያደረገው ‘ካይሮፕራክቲክ’

በአፍሪካ ከጀርባ ሕመም ጋር በተያያዘ በርካታ ሰዎች ለከፍተኛ የአካል...