ዝክረ ዕለት በፎቶ
በዓለም የዩኒቨርሲቲዎች እግር ኳስ ዋንጫ አፍሪካን በመወከል በቻይና ጂንጂያንግ ከተማ የተካፈለው የኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ ቡድን ኅዳር 23 ቀን 2012 ዓ.ም. ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ በባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ሒሩት ካሳው (ዶ/ር) አቀባበል ተደርጎለታል፡፡ የተለያዩ አካላት ለልዑካን ቡድኑ የአበባ ጉንጉን አበርክተዋል፡፡
የፊሊፒንሷን ለጋዝፒ ከተማ ኅዳር 22 ቀን 2012 ዓ.ም. የመታው ታይፎን የተባለው አውሎ ነፋስ ከተማዪቱን እንዳልነበረች አድርጓታል፡፡ ነዋሪዎቿ ከወደሙት መኖሪያቸው አካባቢ ቆመው ይታያሉ፡፡
አርጀንቲናዊው የባርሴሎና አጥቂ ሊዮኒ መሲ ለስድስተኛ ጊዜ የባሎን ዶርን ሽልማት ከተቀዳጀ በኋላ የተፈጠረበት ስሜትና ገጽታ፡፡
የዓለም የአብሮነት ቀን በአፋር
ሰሞኑን በአፋር ሰመራ ከተማ የዓለም የአብሮነት ቀን “አብሮነታችን ለአገር ሰላምና አንድነት” በሚል መሪ ቃል በሥነ በዓሉ ከነበሩት መሰናዶዎች መካከል በአቶ ተሾመ ብርሃኑ “አፋር የሰላምና የመቻቻል ክልል ለምን ሆነ?” እንዲሁም በአቶ አብድልፈታ አብደላ “የአብሮነት የመቻቻል ፋይዳ ለአገር አንድነት” በሚል የቀረቡ ጥናታዊ ጽሑፎች ይገኙበታል፡፡ በክልሉ ከሚገኙ አምስት ዞኖች የተውጣጣ የባህል ቡድን ትርዒቱን አቅርቧል፡፡
“አርት ኦፍ ኢትዮጵያ”
ከሃምሳ በላይ አንጋፋና ወጣት ሠዓልያን የሚካፈሉበት “አርት ኦፍ ኢትዮጵያ” 11ኛው የሥነ ሥዕል ዓውደ ርዕይ፣ ዓርብ ኅዳር 26 ቀን 2012 ዓ.ም. በሸራተን አዲስ ላሊበላ አዳራሽ ከምሽቱ 11 ሰዓት ይከፈታል፡፡ ዓውደ ርዕዩ እስከ ኅዳር 29 ቀን 2012 ዓ.ም. እንደሚቆይም ታውቋል፡፡ “አርት ኦፍ ኢትዮጵያ” ዓመታዊ የሥዕል ዓውደ ርዕይ በሸራተን አዲስ ከተጀመረ 12 ዓመታትን አስቆጥሯል፡