‹‹አዲሱ አስተዳደር ከመጣ ጀምሮ በሰብዓዊ መብት ሕግ፣ ሐሳብን በነፃነት በመግለጽና በማክበር ረገድ ቃል የገባውን ያህል ስለማክበሩ ሥጋት ያደረባቸው አሉ››
በተመድ የነፃ አስተሳሰብና ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት ባለሙያ የተመድ ልዩ ጸሐፊ ዴቪድ ኬይን፣ ከሰሞኑ በኢትዮጵያ ስለሚያደርጉት ጉብኝት ከተናገሩት የተወሰደ፡፡ የተመድ መልዕክተኛው ስለጉብኝታቸው ሲናገሩ፣ አዲሱ የኢትዮጵያ አስተዳደር የወሰዳቸው የፖለቲካ ዕርምጃዎች በብዙኃን ዘንድ ሙገሳ ማግኘቱንም ጠቅሰዋል፡፡ በአዲስ አበባና በባህር ዳር ለሳምንት ያህል ቆይታ እንደሚኖራቸው፣ ስለጉብኝታቸውም ለተመድ ሪፖርት እንደሚያቀርቡ አስታውቀዋል፡፡