በቻይና የተሠራችውና 72 ኪሎ ግራም የምትመዝነው የኢትዮጵያ ሳተላይት ታኅሣሥ 10 ቀን 2012 ዓ.ም. ከቻይና ቤጂንግ 400 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ትወነጨፋለች::
ከመሬት 700 ኪሎ ሜትር ርቃ የምትቀመጠው ሳተላይት፣ በግብርና በአካባቢ ጥበቃና በአየር ሁኔታ ዙሪያ መረጃ የምትሰጥ ይሆናል፡፡
የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ቴክኖሎጂ እንዳስታወቀው፣ ኢትዮጵያ የራሷን የሳተላይት ቴክኖሎጂ መጠቀሟ ከቀሪው ዓለም ጋር እንድትወዳደር ያስችላታል፡፡
የተለያዩ መረጃዎችን ለማግኘት ከፍተኛ የኪራይ ገንዘብ ስትከፍል የነበረችው ኢትዮጵያ ሳተላይቱ ጥቅም ላይ ሲውል ግን በዓመት ከ350 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪን ማስቀረት ትችላለች፡፡
ሳተላይቱ ጥቅም ላይ ሲውል፣ አስፈላጊ መረጃዎችን በአራት ቀናት ውስጥ አደራጅቶ ማምጣት የሚቻል ሲሆን፣ የግብርና እና ሌሎች መረጃዎችን በፍጥነትና በጥራት ለማግኘትም ያስችላል፡፡
ኢትዮጵያ ሳተላይት ለማልማትና ለማምጠቅ በ2009 ዓ.ም. ከቻይና መንግሥት ጋር ከስምምነት መድረሷ ይታወሳል።
በእንጦጦ ኦብዘርቫቶሪና ምርምር ማዕከል ውስጥ ሲገነባ የቆየው የሳተላይት መቆጣጠሪያና መረጃ መቀበያ ጣቢያ መጠናቀቁንም ኢንስቲቲዩቱ አስታውቋል፡፡
የሳተላይት ቴክኖሎጂው ከቻይና መንግሥት ጋር በተደረገ ትብብር የተገነባ መሆኑ ይታወቃል፡፡