Saturday, July 13, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናበኢትዮጵያ አሳሳቢ ችግሮችና መልካም ዕድሎች ላይ የሚመክር ዓለም አቀፍ ጉባዔ ሊካሄድ ነው

በኢትዮጵያ አሳሳቢ ችግሮችና መልካም ዕድሎች ላይ የሚመክር ዓለም አቀፍ ጉባዔ ሊካሄድ ነው

ቀን:

ከ40 በላይ ጥናታዊ ጽሑፎች ይቀርቡበታል

የሙያ ማኅበራትና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተጣምረው በመጪዎቹ 30 ዓመታት ውስጥ በዕጥፍ እንደሚያድግ በሚጠበቀው በኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር ዕድገት ሳቢያ፣ ሊፈጠሩ በሚችሉ አሳሳቢ ችግሮችና መልካም ዕድሎች ላይ የሚመክር ዓለም አቀፍ ጉባዔ ሊያካሂዱ ነው፡፡

ሐሙስ ኅዳር 25 ቀን 2012 ዓ.ም. በተጠራው ጋዜጣዊ መግለጫ፣ ‹‹ኢትዮጵያ 2050›› በሚል ርዕስ፣ ከታኅሳስ 9 እስከ 10 ቀን 2012 ዓ.ም. በስካይላይት ሆቴል የሚካሄደውን ጉባዔ የኢትዮጵያ የምሕንድስና ሙያ ማኅበራት ጥምረት፣ የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዴሚ፣ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ ማኅበር ከዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ጋር በጋራ የሚያዘጋጁትና የኢትዮጵያ አርክቴክቶች ማኅበርም በአስተናጋጅነት በሚሳተፍበት ዓለም አቀፍ ጉባዔ ላይ፣ በመጪዎቹ 30 ዓመታት ውስጥ ለኢትዮጵያ በሥጋትና በመልካም ዕድልነት የሚታዩ ጉዳዮች ላይ ሳይንሳዊ ጥናቶች ቀርበው ውይይት እንደሚካሄድባቸው አዘጋጆቹ አስታውቀዋል፡፡

የኢትዮጵያ የምሕንድስና ሙያ ማኅበራት ጥምረት ፕሬዚዳንት ተስፋዬ ወርቅነህ (ኢንጂነር)፣ ከ30 ዓመታት በኋላ የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር ከዕጥፍ በላይ በመጨመር ከ200 ሚሊዮን በላይ ሊደርስ እንደሚችል ጠቁመው፣ የዚህን ሕዝብ ፍላጎት ማሟላት የሚያስችሉ የመሠረተ ልማትና የኢኮኖሚ አውታሮች፣ እንዲሁም የማኅበራዊ አገልግሎቶች አቅርቦት ላይ ለመመምከር የተጠራ ጉባዔ መሰናዳቱን ገልጸዋል፡፡

የሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚና ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲን በመወከል መግለጫ የሰጡት አረጋ ይርዳው (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ ዓለም አቀፍ ጉባዔው በኢትዮጵያ የወደፊት ዕጣ ፈንታ ላይ አዎንታዊም ሆነ አሉታዊ ገጽታዎችን የሚሳዩ ምርምሮች የሚቀርቡበት መሆኑን፣ መንግሥት ከእነዚህ የምርምር ውጤቶች የሚመነጩ የፖሊሲ ምክረ ሐሳቦችን እንዲጠቀምባቸው ለማገዝ የሚረዳ መድረክ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ እንደ አረጋ (ዶ/ር) ማብራሪያ፣ የሚቀርቡት ጥናቶች በአገር ውስጥና በውጭ በሚኖሩ ምሁራን የተሠሩ ናቸው፡፡ ታዳሚዎችም ሆነ ሌሎች አካላት የምሁራኑ ሐሳብ ላይ በማተኮር እንዲሞግቱ ጠይቀዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዴሚ ፕሬዚንዳት ጽጌ ገብረ ማርያም (ፕሮፌሰር) በበኩላቸው፣ አካዴሚው እስካሁንም ልማት ተኮር በሆኑ ጉዳዮች ላይ ምክረ ሐሳቦችን ለመንግሥት በማቅረብ ሲሳተፍ መቆየቱን አስታውሰው፣ በጉባዔውም ይህንኑ ሚናውን ይወጣል ብለዋል፡፡ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ ማኅበር ዋና ጸሐፊ አቶ ደምረው ጌታቸው እንዳስታወቁት፣ ማኅበሩ ከዚህ ቀደም ለመንግሥት በርካታ የጥናት ውጤቶችን በማቅረብ ብሎም የልማት ሞዴሎችን በማዘጋጀት ጭምር ሲያግዝ ቆይቷል፡፡ ማኅበሩ፣ ‹‹ርዕይ 2020›› በተሰኘውና ለበርካታ ዓመታት ሲያስተናግደው በቆየው ፕሮግራሙ እንደሚታወቅ፣ ይህ እንቅስቃሴው ስላስገኘው ውጤት ግምገማ መጀመሩንም አቶ ደምረው አስታውሰዋል፡፡

በፍጥነት እያደገ ለሚገኘው ለዚህን ያህል ሕዝብ በበቂ ሁኔታ የሚያገለገልግሉ የዕድገትና የልማት፣ የውኃ ሀብት፣ የምግብ ዋስትና፣ የጤናና የትህምርት፣ የግዙፍ ከተሞች ግንባታ፣ ቀጣይነት ያለውና የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖችን መቋቋም የሚችል ኢኮኖሚ፣ የመጓጓዣና የመገናኛ አውታሮች ዝርጋታ፣ የኃይል አቅርቦት፣ የዘመናዊ ፋብሪካዎችና ማምረቻዎች እንቅስቃሴ፣ የኤሌክትሮኒክስ መገናኛ ዘዴዎች መስፋፋትን ጨምሮ በጠቅላላው ከሕዝቡ የዕድገት መጠን ጋር ተጓዳኝነት ያላቸው ፖሊሲዎችና ዕቅዶች ወጥተው እነሱን ያማከሉ ዕርምጃዎች ከወዲሁ ካልተወሰዱ የምግብ ዋስትና ችግር፣ የመኖሪያ ቤት እጥረት፣ የሕክምና፣ የመጓጓዣና የሌሎችም አቅርቦቶች ችግሮች በሕዝቡ ኑሮና ህልውና ላይ ሥጋት እንደሚደቅኑ አዘጋጅ ኮሚቴው አሳስቧል፡፡

‹‹ኢትዮጵያ፣ 2050›› ዓለም አቀፍ ጉባዔ፣ ከ300 በላይ ታዳሚዎች የሚገኙበት፣ ከ40 በላይ የጥናት ጽሑፎች የሚቀርቡበት እንደሚሆን ተገልጿል፡፡ 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የሰብዓዊ መብት ጉዳይና የመንግሥት አቋም

ሰኔ ወር አጋማሽ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ከፍተኛ የሰብዓዊ...

ከሰሜኑ ጦርነት አገግሞ በሁለት እግሩ ለመቆምና ወደ ባንክነት ለመሸጋገር የተለመው ደደቢት ማክሮ ፋይናንስ

በኢትዮጵያ የፋይናንስ ኢንዱስትሪ ውስጥ በቀዳሚነት ስማቸው ከሚጠቀሱት ውስጥ ደደቢት...