Sunday, May 26, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ኪንና ባህልየጥምቀት ክብረ በዓል በዩኔስኮ የዓለም ወካይ ቅርስ ሆነ

የጥምቀት ክብረ በዓል በዩኔስኮ የዓለም ወካይ ቅርስ ሆነ

ቀን:

ዓለም አቀፉ የባህል ተቋም ዩኔስኮ፣ በወርኃ ጥር የኢትዮጵያ አደባባዮች ደምቀው እንዲታዩ የሚያደርገውን የጥምቀት ክብረ በዓልን በሰው ልጅ ወካይ የማይዳሰስ ባህላዊ ቅርስነት መዘገበ።

በቦጎታ ኮሎምቢያ የማይዳሰሱ ባህላዊ ቅርሶች የበይነ መንግሥታት ኮሚቴ የረቡዕ ታኅሣሥ 1 ቀን 2012 .. ውሎው ጥምቀትን ጨምሮ አምስት ባህላዊ ቅርሶችን ነው በሰው ልጆች ወካይ ቅርስነት መመዝገቡን በድረ ገጹ ያበሠረው።
ከኢትዮጵያ ሌላ ሱዳን፣ ግብፅ፣ ቱኒዝያ፣ ሞሮኮና ሞሪታንያ ከዘጠኝ የመካከለኛ ምሥራቅ አገሮች ጋር በጋራ የዴት ፓልም ዕውቀት፣ ክሂል፣ ባህላዊ ተግባርም በሰው ልጅ ወካይ ቅርስነት ተመዝግቦላቸዋል።

ሌላው በቅርስነት የተመዘገበው የቢዛንታይን ጥንታዊ ሥርዓተ ማኅሌት (ዜማ) ሲሆን የሚከተሉትም ቆጵሮስና ግሪክ፣ በዳያስፖራ ያሉት የኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት በአንጾኪያ፣ በእስክንድርያ ዜማውን ለሥርዓተ አምልኮት ይጠቀሙበታል። የቢዛንታይን ዜማ (ሙዚቃ) በባልካንና በዐረብኛ ተናጋሪ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናትም ይከወናል።

- Advertisement -

የጥምቀት ክብረ በዓል በዩኔስኮ የዓለም ወካይ ቅርስ ሆነ

 

ከእምነቱ ውጪም በሙዚቃ ትምህርት ቤቶች በባህላዊ መድረኮችም በኮንሰርቶችም ዜማው እንደሚቀርብ ሰነዱ ያስረዳል። እንዲሁም ኢራን ባህላዊ የዕደ ጥበብ ክሂልና የዶተር ጨዋታ ከቅርሱ ባሕረ መዝገብ ከገባላቸው መካከል ይጠቀሳሉ። በፋይል ማጣቀሻ፣ 1491 የቀረበላቸውን የጥምቀት ክብረ በዓል መዝገብ መርምረው ለውሳኔ ካደረሱት የበይነ መንግሥታት ኮሚቴ አባል 24 አገሮች መካከል አጋርነቷን ያሳየችው ጅቡቲ፣ ሴኔጋል፣ ካሜሩን፣ ቶጎ፣ ሞሪሸስና ዛምቢያ ይገኙበታል።

ክብረ በዓሉን በዩኔስኮ በሰው ልጅ ወካይ የማይዳሰስ ባህላዊ ቅርስነት  ለማስመዝገብ (Representative List of Intangible Cultural Heritage of Humanity)  የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን ካለፉት አራት ዓመታት ወዲህ በይፋ  እንቅስቃሴ ጀምሮ በተለያዩ አካባቢዎች  ያደረገውን ጥናት አጠናቆ  ከቀነ ገደቡ  ከመጋቢት 22 ቀን 2010 ዓ.ም. በፊት ለዩኔስኮ መላኩ ይታወሳል፡፡

ኢትዮጵያ በዩኔስኮ በሰው ልጅ ወካይ የማይዳሰስ ባህላዊ ቅርስነት (Representative List of Intangible Cultural Heritage of Humanity) ካስመዘገበችው አራተኛ ባህላዊ ቅርሷ የጥምቀት ክብረ በዓል በፊት የመስቀል ክብረ በዓል፣ የፊቼ ጫምባላላ እና የገዳ ሥርዓት ማስመዝገቧ ይታወቃል፡፡
‹‹የአፍሪካ ኤጲፋኒያ›› 

የውጭ ጸሐፍት ‹‹የአፍሪካ ኤጲፋኒያ›› (African Epiphany) በመባል በልዩ ልዩ ድርሳኖች የሚታወቀው የጥምቀት በዓል በኦርቶዶክሳዊቷ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የሚከበረው እግዚእ ኢየሱስ ክርስቶስ 30 ዓመቱ በኢትዮጵያ አቆጣጠር ጥር 11 ቀን 31 .. (5531 ዓመተ ዓለም) በአጥማቂው ዮሐንስ እጅ በዮርዳኖስ ባሕር የተጠመቀበትን ዕለት የሚያስታውስ ነው፡፡ ‹‹ኤጲፋንያ›› በመባልም ይታወቃል፡፡ ጥር 10 ቀን በከተራ፣ በገጠርም ሆነ በከተማ ታቦታት ከየአብያተ ክርስቲያናቱ ወደ የባሕረ ጥምቀቱ የሚያደርጉት ጉዞና መንፈሳዊ አዳር በማግስቱ የጥምቀት ዕለት ‹‹ተጠምቀ ሰማያዊ በእደ መሬታዊ›› ሰማያዊው በመሬታዊው እጅ ተጠመቀን ይዞ የሚኖረው ያሬዳዊ ዝማሬ የበዓሉ ገጽታ ነው፡፡

ሥዕላዊ ከሆነው ከሃይማኖታዊና መንፈሳዊ አከባበሩ በተጓዳኝም ባህላዊ ገጽታው ይታያል፡፡ ወጣቶች የሚተጫጩበት የትዳር አጋራቸውን የሚመርጡበት አጋጣሚዎችን ከመፍጠሩም ባለፈ በከተማም ሆነ በገጠር ሰውን የሚያገናኝ ድልድይ ነው፡፡

በየዓመቱ በመላ ኢትዮጵያ የሚከበረው የጥምቀት በዓል፣ ታቦታት ከመንበራቸው ወጥተው፣ በየባሕረ ጥምቀቱ የሚከበሩ በመሆናቸው፣ አገሬውን ብቻ ሳይሆን ዓለም አቀፋዊ መስህብነትን በመጎናጸፉ፣ ቱሪስቶችን እንደሳበ ነው፡፡ ከዝዋይ ሐይቅ እስከ ጣና ሐይቅ፣ ከአዲስ አበባ እስከ ላሊበላ፣ ከአክሱም እስከ ጎንደር፣ ከሐዋሳ እስከ ጅማ፣ ከአሶሳ እስከ ጋምቤላ በሁሉም ሥፍራዎች በዚሁ ዓይነት ደምቆ ይከበራል። የምእመናኑም ሆነ የካህናትና ዲያቆናት አለባበስ  በሚማርኩ ባህላዊ አልባሳት የተዋበ በመሆኑ ከውጭም ሆነ ከአገር ውስጥ ለሚመጡ ጎብኚዎች ሁልጊዜ አዲስ ነው።

ከሃይማኖታዊው ሥነ ሥርዓት በኋላ ካህኑ በሃሌታ፣ ወንዱ በሆታ፣ ሴቱ በእልልታ ታቦተ ሕጉን አጅበው፣ እንደያመጣጣቸው ወደየአጥቢያቸው ይመለሳሉ።

ሊቃውንቱ እንደሚናገሩት፣ ዘመነ አስተርእዮ የሚባለው፣ ከጥር 11 ቀን ጀምሮ እስከ ጾመ ነነዌ ያለው ጊዜ ነው። በዚህ ጊዜ ውስጥ ‹‹አምላክ ሰው ሆኖ በሥጋ መገለጡ፣ በዮርዳኖስ በተጠመቀ ጊዜ የአንድነትና የሦስትነት ምሥጢር መታወቁ፣ በቃና ዘገሊላ በተደረገው ሠርግ ላይ የመጀመሪያው ተዐምር በመፈጸሙ፣ አምላካዊ ኃይሉ መገለጡ›› እየታሰበ ምስጋና ይቀርባል። ይህ ኩነት ኢትዮጵያ ብሂልን ከባህል ጋር አዛምዳ ከሌላው የክርስቲያን ዓለም በተለየ አከባበር በዓሉን ማክበሯ፣ አያሌ ቱሪስቶችን ለመሳብ አስችሏታል።

የጥምቀት ክብረ በዓል በዩኔስኮ የዓለም ወካይ ቅርስ ሆነ

 

በከተማ የሎሚ ውርወራው፣ የከተራው ሽልምልም ዱላ አሁን አሁን በከፊል ሎሚው ወደ ፕሪም፣ ሽልምልሙ ዱላ ወደ ረዥም ቄጠማ (ጨፌ ላይ የሚበቅል) ተለውጦ መታየቱ፣ ከባህላዊ ጭፈራው በተጓዳኝ ወጣቱ በአመዛኙ ከመንፈሳዊ ማኅበራት (ሰንበት ትምህርት ቤቶች) መዘምራን ጋር ወደ ዝማሬ አዘንብሏል፡፡
ከሃይማኖታዊው ሥነ ሥርዓት በኋላ ካህኑ በሃሌታ፣ ወንዱ በሆታ፣ ሴቱ በእልልታ ታቦተ ሕጉን አጅበው፣ እንደያመጣጣቸው ወደየአጥቢያቸው ይመለሳሉ።
‹‹እዩት ወሮ ሲመለስ መድኃኔ ዓለም በፈረስ ወሮ ሲመለስ የሚካኤል አንበሳ ሎሌው ሲያገሳ። ማር ይፈሳል ጠጅ በእመቤቴ ደጅ።» እያሉ ምእመናኑ ታቦታቱን በዝማሬቸው ያጅቡታል። ታቦተ ሕጉም ቅጽር ግቢው ሲደርስ ሁሉም ምኞታቸውን በፍሡሕ ገጽ እንዲህ እያሉ ይገልጻሉ። «በሕይወት ግባ በዕልልታ የዚህ ሁሉ አለኝታ በሕይወት ግቢ እምዬ እንድበላ ፈትዬ›› በዓለም አቀፍ የፌስቲቫሎች መድበል የአፍሪካ ኤጲፋኒያ/ጥምቀት (The African Epiphany) እየተባለ የጎንደሩ፣ የላሊበላው፣ የአዲስ አበባውየጥምቀት አከባበር በዓለም የክብረ በዓላት (Festivals) ድርሳን ላይ በየጊዜው የሚተዋወቀው፣ ቱሪስቶችም እየመጡ የሚያደንቁት አንዳንዶችም ‹‹ጥምቀትን ለምን በቅርስነት አላስመዘገባችሁም?›› እያሉ ሠርክ መጠየቃቸው አልቀረም፡፡ ሪፖርተርም ላለፉት በርካታ ዓመታት መዘገቡም ይታወሳል።

የጥምቀት በዓል በዩኔስኮ በግዙፍ ቅርስነት ከተመዘገቡት ከአክሱም፣ ላሊበላ የጎንደሩ ፋሲል ግቢ ጋር በጥብቅ ተሳስሮ የሚከበር የማይዳሰስ ባህላዊ ቅርስ መሆኑ፣ እንዲሁም በዓሉ 1,500 ዓመታት በላይ በተከታታይ የአገሪቱ ትውልዶችና ሥልጣኔዎች እየተከበረ ያለ ሕያው ቅርስ መሆኑ ይታወቃል፡፡

የጥምቀተ ክርስቶስ በዓል በዩኔስኮ መመዝገቡን ተከትሎ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ታኅሣሥ 2 ቀን 2012 .. ባስተላለፉት መልዕክት፣ የበዓለ ጥምቀት በዩኔስኮ መመዝገብ ለዚህ ሃይማኖታዊና ሀገራዊ ተልዕኮ ዕውቅና በመስጠት ረገድ የላቀ ሚና ስላለው በዓሉን፣ ሃይማኖቱን፣ ባህሉንና ሥነ በዓሉን በማስተዋወቅ ሁሉም የበኵሉን እንዲወጣ በዚህ አጋጣሚ ጥሪያችንን ማስተላለፍ እንወዳለን ብለዋል፡፡.

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የፋይናንስ ኢንዱስትሪው ለውጭ ባንኮች መከፈት አገር በቀል ባንኮችን ለምን አስፈራቸው?

የማይረጥቡ ዓሳዎች የፋይናንስ ተቋማት መሪዎች ሙግት ሲሞገት! - በአመሐ...

የምርጫ 97 ትውስታ!

በበቀለ ሹሜ      መሰናዶ ኢሕአዴግ ተሰነጣጥቆ ከመወገድ ከተረፈ በኋላ፣ አገዛዙን ከማሻሻልና...

ሸማቾች የሚሰቃዩት በዋጋ ንረት ብቻ አይደለም!

የሸማች ችግር ብዙ ነው፡፡ ሸማቾች የሚፈተኑት ባልተገባ የዋጋ ጭማሪ...

መንግሥት ከለጋሽ አካላት ሀብት ለማግኘት የጀመረውን ድርድር አጠናክሮ እንዲቀጥል ፓርላማው አሳሰበ

የሦስት ዩኒቨርሲቲዎች ፕሬዚዳንቶች በኦዲት ግኝት ከኃላፊነታቸው መነሳታቸው ተገልጿል አዲስ አበባ...