Wednesday, December 7, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ማኅበራዊደብረ ብርሃን ከተማን ‹‹ስማርት ሲቲ›› ለማድረግ እንቅስቃሴ ተጀመረ

  ደብረ ብርሃን ከተማን ‹‹ስማርት ሲቲ›› ለማድረግ እንቅስቃሴ ተጀመረ

  ቀን:

  በዳግማዊ ምኒልክ ስም ስኮላርሺፕ ሊሰጥ ነው

  በአማራ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና ከተማ ደብረ ብርሃንን ከተፈጥሮ ጋር የተዛመደ፣ ባህላዊ ገጽታውን የጠበቀና በቴክኖሎጂያዊ ይዘቱ የበለፀገ ከተማ (ስማርት ሲቲ) ለማድረግ የሚያስችል የመነሻ ሐሳብ ላይ ከከተማው ነዋሪዎችና ከባለሙያዎች ጋር ውይይት ተደረገ፡፡

  ከባህር ጠለል በላይ 2,800 ሜትር ከፍታ ላይ በምትገኘው ደብረ ብርሃን ዕድገትና ቱሪዝም ላይ ለመምከር ዓርብ ታኅሳስ 3 ቀን 2012 ዓ.ም. በከተማዋ በተደረገ ውይይት ላይ እንደተገለጸው፣ ከተማዋ የመስፋፋቷን ያህል የሕዝቧን አኗኗር፣ ባህልና እሴት የጠበቀ ‹‹ስማርት ሲቲ›› መገንባት አስፈላጊ ሆኗል፡፡

  ለከተማዋ የማስፋፊያ ፕሮጀክት አንዱ በሆነው ‹‹ስማርት ሲቲ›› ግንባታ ላይ ሐሳብ ያቀረቡት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲና በአዳማ ዩኒቨርሲቲ የኪነ ሕንፃና ከተማ ፕላን መምህር የነበሩት አቶ ፋሲካ ገዛኸኝ እንዳሉት፣ ለመገንባት የታሰበው ከተማ እንደ ከዚህ ቀደሙ የኅብረተሰቡን ባህል፣ የአኗኗር ዘይቤና ፍላጎት በመተው፣ ‹‹ይህ ለመኖሪያ፣ ይህ ለንግድ›› እየተባለ መሬት በመሸንሸን ሳይሆን፣ ተፈጥሮን መሠረት አድርጎ የሕዝቡን ባህል፣ ልማድ፣ ማኅበራዊ ትስስር፣ የአካባቢውን ሀብትና የአየር ንብረት መሠረት ያደረገ ነው፡፡

  ‹‹ስማርት ሲቲ›› ማለት በቴክኖሎጂ የሚገነባ ከተማ እንደሆነ በመግለጽም፣ ከተማዋ ከአገር ውስጥ ጀምሮ ለውጭው ማኅበረሰብ ክፍትና ሁሉን በእኩል የምታስተናግድ እንደምትሆን ተናግረዋል፡፡

  በከተማዋ ያሉ መሠረተ ልማቶች የማኅበረሰቡን አብሮ የመኖር ዘይቤ የሚያደፈርሱ ሳይሆኑ አብሮ መኖርን የሚያጠናክሩ መሆን እንደሚገባቸው፣ ለመገንባት የታሰበው ‹‹ስማርት ሲቲ››ም የማኅበረሰቡን ፍላጎት መሠረት ያደረገ እንደሚሆን አክለዋል፡፡

  የ‹‹ስማርት ሲቲ›› አካል በሆነው የሰሜን ሸዋ የቱሪስት መስህብን የማስተዋወቅና የማልማት ሥራም ሰው ሠራሽ ሐይቅ፣ ባለኮከብ ሆቴሎች፣ የበሬሳ ወንዝ ልማትና ፓርኮችን መመሥረት ያካትታል፡፡

  በሌላ ዜና ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ከ1881 ዓ.ም. እስከ 1906 ዓ.ም. በኢትዮጵያ በነገሡት ዳግማዊ አፄ ምኒልክ ስም ስኮላርሺፕ እንደሚጀምር ታወቀ፡፡

  የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ተፈራ ወንድማገኝ እንደተናገሩት፣ ዩኒቨርሲቲው ‹‹ዳግማዊ አጤ ምኒልክ አፍሪካ›› በሚል ስያሜ ስኮላርሺፕ ለመጀመር ዝግጅቱን ያጠናቀቀ ሲሆን፣ ዘንድሮ ወይም በቀጣይ ዓመት ለተማሪዎች ነፃ የትምህርት ዕድል ይሰጣል፡፡

  ዞኑና ዩኒቨርሲቲው በተነጋገሩት መሠረት ለመጀመርያ ጊዜ ለአሥር ኢትዮጵያውያንና ለሦስት አፍሪካውያን ነፃ የትምህርት ዕድል ይሰጣል፡፡

  በዳግማዊ አፄ ምኒልክ ስም ነፃ የትምህርት ዕድል መመቻቸቱ እሳቸው ለኢትዮጵያ የነበራቸውን መልካም አበርክቶ ብቻ ሳይሆን፣ ኢትዮጵያንም በደንብ ለማስተዋወቅ መልካም አጋጣሚን ይፈጥራል ተብሏል፡፡

  ኬንያ፣ ታንዛኒያና የሌሎች የአፍሪካም ሆኑ የሌሎች አኅጉር ዩኒቨርሲቲዎች በታዋቂ ሰዎቻቸውና በመሪዎቻቸው ስም ነፃ የትምህርት ዕድል የሚሰጡ ቢሆንም፣ እንዲህ ዓይነቱ ሥራ በኢትዮጵያ ብዙም አልተለመደም፡፡

  የስድስት ምዕት ዓመት ታሪክ ባላት ደብረ ብርሃን ከተማ የሚገኘው ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የተመሠረተው ከአሥር ዓመት በፊት መሆኑ ይታወሳል፡፡

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  በኦሮሚያ ክልል የተፈጸመው ጭፍጨፋና ሥጋቱ

  ኦሮሚያ ክልል ከቀውስ አዙሪት መላቀቅ ያቃተው ይመስላል፡፡ ከ200 በላይ...

  እናት ባንክ ካፒታሉን ወደ አምስት ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ወሰነ

  መጠባበቂያን ሳይጨምር የባንኩ የተጣራ ትረፍ 182 ሚሊዮን ብር ሆኗል እናት...

  ቡና ባንክ ዓመታዊ ትርፉን ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ማሻገር ቻለ

  ቡና ባንክ በ2014 የሒሳብ ዓመት ዓመታዊ የትርፍ ምጣኔውን ለመጀመርያ...