Saturday, December 2, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትበኡጋንዳው የሴካፋ ምርጫ የኢትዮጵያ ሚና

በኡጋንዳው የሴካፋ ምርጫ የኢትዮጵያ ሚና

ቀን:

ደካማ የእግር ኳስ እንቅስቃሴ ከሚስተዋልባቸው የአፍሪካ አገሮች ምሥራቅና መካከለኛው አፍሪካ አገሮች (ሴካፋ) በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳል፡፡ ዞን አምስት በሚል መጠሪያ የሚታወቀው የምሥራቅ አፍሪካ እግር ኳስ ታኅሣሥ 8 ቀን 2012 ዓ.ም. በኡጋንዳ ካምፓላ በሚያደርገው ዓመታዊ ጉባዔ አዲስ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ምርጫ ያከናውናል፡፡ ኢትዮጵያ ዞኑን በምክትል ፕሬዚዳትነት መምራት የሚያስችላትን ቦታ ለማግኘት ለምርጫ እንደምትቀርብ ታውቋል፡፡

በአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) አምስት ዞኖች አንዱ የሆነው ሴካፋ፣ ደካማነቱ በእግር ኳሱ ብቻ ሳይሆን በተቋማዊ ቅርጹ ጭምር እንደሆነ በኡጋንዳ አስተናጋጅነት በመካሄድ ላይ የሚገኘው የሴካፋ ዋንጫ አንዱ ማሳያ መሆኑ ይነገራል፡፡ በጉባዔው የሚታደሙት የኢትዮጵያና የሩዋንዳ ብሔራዊ ቡድኖች የበጀት እጥረት ምክንያት አድርገው በሴካፋ ዋንጫ እንደማይሳተፉ ያስታወቁት ቀደም ብለው ነው፡፡

የምሥራቅ አፍሪካ ብቻም ሳይሆን የአፍሪካ እግር ኳስ መሥራች ከሚባሉት አራት አገሮች አንዷ እንደሆነች የሚነገርላት ኢትዮጵያ፣ ሴካፋን የምክትል ፕሬዚዳንትነቱን ቦታ ለማግኘት በዕጩነት እንደሚቀርቡ የሚነገርላቸው የብሔራዊ ፌዴሬሽኑ የወቅቱ ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ ወደ ስፍራው ማምራታቸው ታውቋል፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በሴካፋ ዋንጫ ላይ እንደማይሳተፍ ማስታወቁን ተከትሎ፣ ኢትዮጵያ እንዳሰበችው ዞኑን በምክትል ፕሬዚዳንትነት መምራት የሚስችላትን የመራጮች ይሁንታ ለማግኘት ችግር ሊሆንባት እንደሚችል ሥጋት ያደረባቸው ነበሩ፡፡

በሱዳናዊ ሙታዚም ጋፋር (ዶ/ር) የሚመራው ሴካፋ እንደ ተቋም ራሱን ሊፈትሽ እንደሚገባው ከሚናገሩት አስተያየት ሰጪዎች መካከል አቶ ኢሳያስ ጅራ አንዱ ናቸው፡፡ እንደ አቶ ኢሳያስ ከሆነ፣ ሴካፋን በፕሬዚዳንትነት በማስተዳደር ላይ ከሚገኙት ሱዳናዊ ሙታዚም ጋር በምንም ጉዳይ ተገናኝተው አያውቁም፡፡ በቅርቡ በኤርትራ አስተናጋጅነት በተካሄደው ዕድሜያቸው ከ15 ዓመት በታች የምሥራቅና መካከለኛ አፍሪካ ታዳጊዎች ዋንጫ ላይ በትክክለኛ ዕድሜ የተሳተፉት ኢትዮጵያና ሩዋንዳ ሲሆኑ፣ አስተናጋጇ ኤርትራን ጨምሮ የተቀሩት ከፍተኛ የዕድሜ ችግር የነበረባቸው እንደነበሩ የሚያስታውሱት አቶ ኢሳያስ፣ በጉዳዩ ከፕሬዚዳንቱ ጋር ተገናኝተው ለመወያየት እንኳ ሊያገኟቸው እንዳልቻሉ ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በኡጋንዳ አስተናጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው የሴካፋ ዋንጫ ላይ እንደማይሳተፍ ያስታወቀው በዚህ ተከፍቶ ይሆን ለሚለው የሪፖርተር ጥያቄ አቶ ኢሳያስ፣ ‹‹በፍጹም ቡድናችን ከሴካፋ ዋንጫ ውጪ የሆነው በበጀት እጥረት ነው፡፡ የፌዴሬሽናችን የሥራ አመራር ቦርድ ከበጀት ጋር ተያይዞ ውይይት አድርገናል፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ሁሉም እንደሚያውቀው ውክልናው ለኢትዮጵያ ነው፡፡ እስከ ሴካፋው ድረስ የብሔራዊ ቡድኑ ሁሉም ወጪ ሲሸፈን የቆየው በፌዴሬሽኑ ነው፡፡ ተቋሙ አሁን ላይ ከፍተኛ በሆነ የፋይናንስ እጥረት ውስጥ ነው፣ ሁኔታው በሒደት አንድ የመፍትሔ አቅጣጫ እስካልተቀመጠለት ድረስ ችግሩ ቀጣይነት ይኖረዋል ብለን እንጠብቃለን፤›› በማለት ብሔራዊ ቡድኑ ከሴካፋ ውጪ የሆነበት ምክንያት ከሴካፋ ተሳትፎ ጋር  ግንኙነት እንደሌለው አስተድተዋል፡፡

ኢትዮጵያ በሴካፋ የሚኖራትን ሚና በተመለከተ ይህን ቃለ መጠይቅ እስካደረጉበት ድረስ በኡጋንዳው የሴካፋ ጉባዔ እንደሚሳተፉ እንጂ ለምርጫ ዕጩ ሆነው እንደሚቀርቡ አልገለጹም፡፡ ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ዘግይቶ እንደገለጸው፣ አቶ ኢሳያስ በኡጋንዳ ካምፓላ በሚደረገው የሴካፋ ምርጫ የምክትል ፕሬዚዳንቱን ቦታ ለመያዝ ዕጩ ሆነው እንደሚቀርቡ ይፋ አድርጓል፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመቃወም ነፃነት ውዝግብ በኢትዮጵያ

ስሟ እንዳይገለጽ የጠየቀችው በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ የሾላ አካባቢ...

የሲሚንቶን እጥረትና ችግር ታሪክ ለማድረግ የተጀመረው አጓጊ ጥረት

በኢትዮጵያ በገበያ ውስጥ ለዓመታት ከፍተኛ ተግዳሮት በመሆን ከሚጠቀሱ ምርቶች...

የብሔር ፖለቲካው ጡዘት የእርስ በርስ ግጭት እንዳያባብስ ጥንቃቄ ይደረግ

በያሲን ባህሩ በሪፖርተር የኅዳር 9 ቀን 2016 ዓ.ም. ዕትም “እኔ...