ከስድሳ በላይ አባላትን የያዘው የኢትዮጵያ የባህል ቡድን በኤርትራ ሦስት ከተሞች የሙዚቃ ትርዒቱን ለማቅረብ ታኅሣሥ 6 ቀን 2012 ዓ.ም. አስመራ ከተማ ገብቷል፡፡ ልዑካኑ ከውጭ ጉዳይ፣ ከባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴሮች፣ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር፣ ከታዋቂ ድምፃውያንና ከጃኖ ባንድ የተወጣጡ ናቸው፡፡ ለአንድ ሳምንት በኤርትራ የሚቆየው ቡድኑ በአስመራ፣ ከረንና ምፅዋ ከተሞችች የሙዚቃ ዝግጅቱን እንደሚያቀርብ ይጠበቃል። ፎቶዎቹ የአቀባበሉን ከፊል ገጽታ ያሳያሉ፡
- Advertisement -
- Advertisement -
- Advertisement -
ፌርማታ ፅሁፎች
ትኩስ ፅሁፎች
- Advertisement -
- Advertisement -