Friday, December 1, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዓለምየጄኔቭ የስደተኞች ሸንጎ

የጄኔቭ የስደተኞች ሸንጎ

ቀን:

በዓለም አቀፍ ደረጃ ጫና እየፈጠረ የሚገኘው የስደተኞች ጉዳይ በጄኔቭ ስዊዘርላንድ መነጋገሪያ አጀንዳ ሆኗል፡፡ 71 ሚሊዮን ያህል ስደተኞች በዓለም አቀፍ ደረጃ ሲገኙ፣ ከእነዚህ ውስጥ 26 ሚሊዮን ያህሉ ዕውቅና ያገኙና በጦርነትና በማንነታቸው ከሚደርስባቸው ግድያ ለማምለጥ ከሶሪያ፣ ኢራቅና ማይናማር የተሰደዱ ናቸው፡፡

እነዚህን ጨምሮ አብዛኞቹ ስደተኞች የተጠለሉት ደግሞ ዝቅተኛ ኢኮኖሚ ባላቸው አገሮች ነው፡፡ ይህም ስደተኛ ተቀባይ አገሮችን ችግር ውስጥ ከቷል፡፡ በመሆኑም በስደተኞችና ስደተኞችን በሚቀበሉ አገሮች ላይ ለሚደርሱ ችግሮች መፍትሔ ለማፈላለግ የዘርፉ ተዋናዮች በጄኔቭ ለሦስት ቀናት ሸንጎ ተቀምጠዋል፡፡

ስዊዝኢንፎ በድረ ገጹ እንዳሰፈረው፣ ከታኅሣሥ 6 እስከ 8 ቀን 2012 ዓ.ም. በጄኔቭ ‹‹ግሎባል ሪፊውጂ ፎረም›› የተካሄደ ሲሆን፣ በዚህም ሁለት ሺሕ ያህል የመንግሥታት ልዑካን ቡድን አባላት፣ ዓለም አቀፍና አገር በቀል ድርጅቶችና 60 ያህል የስደተኞች ተወካዮች ተሳትፈዋል፡፡

በግጭት ምክንያት ተገደው ከአካባቢያቸው የሚሰድዱት ቁጥር ባየለበት ወቅት በተካሄደው ሸንጎ፣ አስገዳጅ ስደትን መከላከል በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ተመክሯል፡፡

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ኬሊ ካልመንትስ እንደሚሉት፣ ወቅቱ የግዳጅ ስደትን ለማስቆም ምላሽ የሚሰጥበት ነው፡፡ ስደትን ለማስቆም የተሻለ መፍትሔ እንደሚያስፈልግም አክለዋል፡፡

ኮሚሽኑ ስደተኞች የሥራና የትምህርት ዕድል እንዲያገኙ፣ በየመጠለያዎች መሠረተ ልማቶች እንዲሟሉ፣ ጥበቃ እንዲደረግላቸውና በትብብርና ኃላፊነትን በመካፈል የስደተኞች ችግር እንዲፈታ ፍላጎቱ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

የጄኔቭ የስደተኞች ሸንጎ

 

የስደተኛ ተቀባይ አገሮችን ጫና መካፈል

በአብዛኛው ስደተኞች ተጠልለው የሚገኙት በዝቅተኛ ወይም መካከለኛ ገቢ ባላቸው አገሮች ውስጥ ነው፡፡ 85 በመቶ ስደተኞች ዝቅተኛ ወይም መካከለኛ ገቢ ባላቸው አገሮች ተጠልለው መገኘታቸው ደግሞ ስደተኛ ተቀባይ አገሮችን ፈተና ውስጥ ከቷል፡፡ አንዳንዶቹ አገሮች ለዜጎቻቸው እንኳን የሚበቃ መሬት የሌላቸው ሲሆኑ፣ አንዳንዶቹ ደግሞ መሠረተ ልማት ያልተዳረሳቸው፣ የጤና ተደራሽነቱም ያልተሟላላቸው ናቸው፡፡

በአንዳንዶቹ አገሮች ደግሞ ስደተኞች እንዲሰፍሩ ሲባል ብቻ ጥቅጥቅ ደኖች ወድመዋል፡፡ ስደተኞችም ከተቀባይ አገሮች ዜጎች ጋርም ሆነ እርስ በርስ መጋጨት፣ በሴቶችና ሕፃናት ላይ የሚደርስ ፆታዊ ጥቃትና በደል መባባስም ሌላው ችግር ነው፡፡ በመሆኑም ሌሎች አገሮች በራቸውን ለስደተኞች ክፍት በማድረግ የተወሰኑ አገሮች ብቻ የተሸከሙትን ጫና ለመቀነስ እንዲሠሩም ተጠይቋል፡፡

በአምነስቲ ኢንተርናሽናል የስደተኞች መብት ኤክስፐርት ጄኒፈር ፎስተር፣ የተሻለ የኃላፊነት ክፍፍልና በሰብዓዊ መብት ላይ መሠረት ያደረገ ዕገዛ እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል፡፡

በዓለም አቀፍ ደረጃ ስደተኛ ለተቀበሉ አገሮች የገንዘብና የቁሳቁስ ልገሳ ማግኘታቸውና ስደተኞች ሕጋዊ ሆነው እንዲንቀሳቀሱ የሚሠሩ ሥራዎች መልካም ቢሆኑም፣ በአንዳንድ አገሮች የሚገኙ ስደተኛ ሕፃናት ትምህርት የማያገኙ መሆኑ፣ ተጨማሪ የገንዘብ ዕገዛ እንደሚያስፈልግ ያሳያልም ብለዋል፡፡ የሮሃኒንጋ ስደተኞችን ካስጠለሉት አገሮች አንዷ ለሆነችው ባንግላዴሽና የሶሪያንና ሌሎች ስደተኞችን ለሚደግፈው የቱርክ መንግሥት የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያስፈልግም አክለዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመቃወም ነፃነት ውዝግብ በኢትዮጵያ

ስሟ እንዳይገለጽ የጠየቀችው በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ የሾላ አካባቢ...

የሲሚንቶን እጥረትና ችግር ታሪክ ለማድረግ የተጀመረው አጓጊ ጥረት

በኢትዮጵያ በገበያ ውስጥ ለዓመታት ከፍተኛ ተግዳሮት በመሆን ከሚጠቀሱ ምርቶች...

የብሔር ፖለቲካው ጡዘት የእርስ በርስ ግጭት እንዳያባብስ ጥንቃቄ ይደረግ

በያሲን ባህሩ በሪፖርተር የኅዳር 9 ቀን 2016 ዓ.ም. ዕትም “እኔ...