Monday, December 5, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ሳይንስና ቴክኖሎጂየመጀመሪያዋ የኢትዮጵያ ኢትረስ-1 ሳተላይት ተወነጨፈች

  የመጀመሪያዋ የኢትዮጵያ ኢትረስ-1 ሳተላይት ተወነጨፈች

  ቀን:

  በቻይና የተሠራችውና 72 ኪሎ ግራም የምትመዝነው ኢትረስ-1 የኢትዮጵያ ሳተላይት ታኅሣሥ 10 ቀን 2012 .. ከጠዋቱ 12፡ 21 ሰዓት ላይ ከቻይና ቤጂንግ 400 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ተወነጨፈች::

  ከመሬት 700 ኪሎ ሜትር ርቃ የተወነጨፈችው ሳተላይት፣ በግብርና በአካባቢ ጥበቃና  በአየር ሁኔታ ዙሪያ መረጃ የምትሰጥ ይሆናል፡፡

  ሳተላይቱ ጥቅም ላይ መዋል ኢትዮጵያ ለሳተላይት ኪራይ በዓመት ትከፍል የነበረውን 350 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪማስቀረት ያስችላል፡፡

  በእንጦጦ ኦብዘርቫቶሪና ምርምር ማዕከል ውስጥ ሲገነባ የቆየው የሳተላይት መቆጣጠሪያና መረጃ መቀበያ ጣቢያም የተጠናቀቀ ሲሆን፣ መረጃዎችን የመሰብሰብ ስራው ሙሉ በሙሉ የሚከናወነው በኢትዮጵያውያን መሃንዲሶች ነው፡፡

  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ጌታሁን መኩሪያ (ዶ/ር) ፣ የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ሰለሞን በላይ (ዶ/ር) ፣ ከተወካዮች ምክር ቤት እና ከጋዜጠኞች የተውጣጣ ልዑካን ቡድን፣ ኢትረስ-1 ከቻይና ቤጂንግ ስትመጥቅ ለማየት ታድመዋል፡፡ ሁነቱም በኢትዮጵያ ብሮድካስት መገናኛ ብዙኃን በቀጥታ ስርጭት ተላልፏል፡፡

  ኢትዮጵያ ሳተላይት ለማልማትና ለማምጠቅ በ2009 ዓ.ም. ከቻይና መንግሥት ጋር ከስምምነት መድረሷ ይታወቃል፡፡

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  ዳግም ነፍስ የዘራው የተማሪዎች ማርች ባንድ

  የሙያው ፍቅር ያደረባቸው ገና በልጅነታቸው ነው፡፡ በ1970ዎቹ መጀመርያ፣ ለቀለም...

  በስንደዶና ሰበዝ የተቃኘው ጥበብ

  በአንዋር አባቢ ተወልዳ ያደገችው መሀል አዲስ አበባ አራት ኪሎ ነው፡፡...

  አዲስ ጥረት የሚጠይቀው  ኤችአይቪ  ኤድስን  የመግታት  ንቅናቄ

  ‹‹ኤችአይቪ በመላው ዓለም  በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን የሚያጠቃ ዋነኛ የሕዝብ...

  የኅትመት ብርሃን ያየው ‹‹የቃቄ ወርድዎት›› ቴአትር

  ከአራት ዓመታት በፊት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር መድረክ ላይ ይታይ...