Friday, December 1, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየሕፃናት የጉልበት ሥራን የማስቀረት ተግባር እንዲከናወን ማሳሰቢያ ተሰጠ

የሕፃናት የጉልበት ሥራን የማስቀረት ተግባር እንዲከናወን ማሳሰቢያ ተሰጠ

ቀን:

43 በመቶ ኢትዮጵያውን ሕፃናት በጉልበት ሥራ ተሰማርተዋል

በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በመላው ዓለም አሳሳቢ እየሆነ የመጣውን የሕፃናት ጉልበት ሥራ፣ ሕገወጥ የሰዎች ዝውውርና የግዴታ ሥራን ለማስወገድ በተግባር የሚታይ ሥራ እንዲከናወን፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን አሳሰቡ፡፡

ከዘላቂ ልማት ግብ አንድ ክፍል የሆነውና የሕፃናት የጉልበት ሥራን፣ ሕገወጥ የሰዎች ዝውውርንና የግዴታ ሥራን እ.ኤ.አ. በ2030 ለማስወገድ የተቀመጠውን 8.7 ዒላማ ጥምረት ለመተግበር በሚያስችለው የዕቅድ ዝግጅት መክፈቻ ላይ የተገኙት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ፣ መጪው ዘመን ሕፃናትን ማዕከል ያደረገ ሥራ የሚከናወንበትና ኢትዮጵያም የገባችውን ቃል ኪዳን የምትተገብርበት ነው ብለዋል፡፡

እንደ ዘላቂ ልማት ግቡ ሁሉ የአፍሪካ የልማት አጀንዳ 2063 የሕፃናት ጉልበት ሥራን ለማጥፋት ዕቅድ ማስቀመጡን በማስታወስ፣ ኢትዮጵያ የዘላቂ ልማት ግብንና የአፍሪካ ልማት አጀንዳ 2063 አጣምራ ችግሩን ለመቅረፍ እንደምትሠራ ተናግረዋል፡፡

‹‹የብልፅግና ዘመን በእጅጉ ሰው ተኮር ነው፤›› ያሉት አቶ ደመቀ፣ ‹‹መንግሥት ሰው በልቶ እንዲያድርና ውሎ እንዲገባ ብቻ ሳይሆን፣ ክብሩና መብቱ እንዲጠበቅ ሰውን ማዕከል አድርጎ ይሠራል፤›› ብለዋል፡፡

መንግሥት ሰውን መሠረት ባደረገ የለውጥ እንቅስቃሴ ውስጥ እንደሚገኝና ሳተላይት የማምጠቁ ዋና ዓላማም የተፈጥሮ ሚስጥርን በማወቅ ኢትዮጵያውያንን ውጤታማና ስኬታማ ማድረግ መሆኑን በመግለጽ፣ የሚዘጋጀው ዕቅድ ሰው ተኮር፣ ሕፃናት ተኮርና የሕፃናትን ክብር የሚጠብቅ በመሆኑ፣ ሥራው ወደ ተግባር እንዲለወጥና ሕፃናትን መታደግ እንዲቻል ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር)፣ በኢትዮጵያ 43 በመቶ ያህል በትምህርትም ሆነ ከትምህርት ውጪ ያሉ ሕፃናት በጉልበት ሥራ መሰማራታቸውን የቅርብ ጥናቶች እንደሚያሳዩ ጠቁመው፣ ይህንን ችግር ለመቅረፍ የሚያስችለውንና አገሮች በትብብር የሚሠሩበት የዘላቂ ልማት ግብ ጥምረት (አልያንስ) ግብ ለመድረስ እየተሠራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የሕፃናት የጉልበት ሥራ፣ ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር፣ የግዴታ ሥራና ዘመናዊ ባርነትን ለማጥፋትም ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የተለያዩ ስምምነቶችን መፈረሟን፣ ሆኖም ተቀናጅቶ መሥራት ላይ ክፍተት እንደነበር ገልጸው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመሩት የሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ምክር ቤት ጤና ሚኒስቴር፣ የአሠሪዎች ማኅበራት ፌዴሬሽኖችና ኮንፌዴሬሽኖች፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና ከድንበር ውጭ ያሉም ጥምረት ፈጥረው በጋራ የሚሠራበት ሥርዓት እየተዘረጋ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

እ.ኤ.አ. በ2017 በታተመ ጥናት በዓለም አቀፍ ደረጃ ከአምስት እስከ 17 የዕድሜ ክልል ያሉ 152 ሚሊዮን ሕፃናትና ታዳጊ ሕፃናት በጉልበት ሥራ ተሰማርተዋል፡፡ በአፍሪካ ከአምስት ሕፃናት አንዱ በጉልበት ሥራ የተሰማራ ሲሆን፣ ይህ ከሌሎች አገሮች ሲነፃፀር ከሁለት ዕጥፍ በላይ ነው፡፡ በአፍሪካ ዘጠኝ በመቶ ሴቶችና ወንዶች ሕፃናት አደገኛ በሚባሉ የሥራ ዘርፎች ተሰማርተው ይገኛሉ፡፡

በዓለም 25 ሚሊዮን ሰዎች በግዳጅ ሥራ፣ 15 ሚሊዮን ሰዎች በግዳጅ ጋብቻ፣ በአጠቃላይ 40 ሚሊዮን ሰዎች በዘመናዊ ባርነት ውስጥ ይገኛሉ፡፡ የዘመናዊ ባርነት ሥርጭት በአፍሪካ በ1,000 ሰው 7.6 ሲሆን፣ ይህም ከየትኛውም አኅጉር ትልቁ ነው፡፡ በኢትዮጵያ በጉልበት ሥራ ከተሰማሩ 43 በመቶ ሕፃናት፣ በአማራና በአፋር ክልሎች የተመዘገበው ከፍተኛውን ቁጥር ይይዛል፡፡   

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመቃወም ነፃነት ውዝግብ በኢትዮጵያ

ስሟ እንዳይገለጽ የጠየቀችው በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ የሾላ አካባቢ...

የሲሚንቶን እጥረትና ችግር ታሪክ ለማድረግ የተጀመረው አጓጊ ጥረት

በኢትዮጵያ በገበያ ውስጥ ለዓመታት ከፍተኛ ተግዳሮት በመሆን ከሚጠቀሱ ምርቶች...

የብሔር ፖለቲካው ጡዘት የእርስ በርስ ግጭት እንዳያባብስ ጥንቃቄ ይደረግ

በያሲን ባህሩ በሪፖርተር የኅዳር 9 ቀን 2016 ዓ.ም. ዕትም “እኔ...