Thursday, December 1, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ዜናጠቅላይ ሚኒስትሩና የመከላከያ ሚኒስትሩ ልዩነታቸውን መፍታታቸው ተሰማ

  ጠቅላይ ሚኒስትሩና የመከላከያ ሚኒስትሩ ልዩነታቸውን መፍታታቸው ተሰማ

  ቀን:

  የለውጥ መሪዎች በመባል የሚታወቁት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) እና የአገር መከላከያ ሚኒስትሩ አቶ ለማ መገርሳ፣ የሐሳብ ልዩነታቸውን በመፍታት የጀመሩትን አገራዊ ለውጥ አብረው እንደሚያስቀጥሉ ተገለጸ፡፡

  አቶ ለማ በቅርቡ ለአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ ጣቢያ (ቪኦኤ) በሰጡት አጭር መግለጫ በአዲሱ ውህድ ፓርቲ ምሥረታ፣ በመደመር ጽንሰ ሐሳብናሌሎች ጉዳዮች ላይ ልዩነት እንዳላቸው መናገራቸው ይታወሳል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መደመጥ አለመቻላቸውንም መናገራቸው አይዘነጋም፡፡ በዚህም ሳቢያ በሁለቱ አመራሮች መካከል የተፈጠረው ልዩነት ወደ አላስፈላጊ ግጭት እንዳያመራ ሥጋት ተፈጥሮ ነበር፡፡  

  ነገር ግን ሰሞኑን በገዥው ፓርቲ ኢሕአዴግ ይፋዊ ድረ ገጽና በተለያዩ የመንግሥትና የፓርቲ አመራሮች ልዩነቱ ሰክኖ፣ አብረው ለመሥራት መስማማታቸው ይፋ ተደርጓል፡፡ ‹‹የግል ሐሳብን በነፃነት ማራመድን የሚያመላክት ዴሞክራሲያዊ መብት የተንፀባረቀበት እንጂ የተካረረ የግለሰቦች ፀብ አልነበረም፤›› ተብሎም በኢሕአዴግ ድረ ገጽ ላይ ሠፍሯል።

  ለውጡ ዘለቄታ እንዲኖረው እንዴት እንምራው የሚል የተወሰነ የአካሄድ ልዩነት እንጂ በሚወራው ደረጃ አልነበረም። በመሆኑም አሁንም የሐሳብ ልዩነታቸው ላይ በሰለጠነ አካሄድ ቁጭ ብለው ከተከራከሩበት በኋላ፣ የሐሳብ ልዩነታቸውን ፈተው ለውጡን አብረው ለመሥራት ተስማምተዋል። የሐሳብ ልዩነት፣ ክርክር፣ በሐሳብ ብቻ መጋጨት፣ ብሎም የሚሰማንን በነፃነት መግለጽ ዴሞክራሲያዊ ባህል ነው፤›› ሲል ኢሕአዴግ አክሏል።

  አቶ ለማ በመደመር ዕሳቤና በፓርቲዎች ውህደት ላይ የነበረቸውን ልዩነት አጥብበው የሕዝቡን ትግል ወደ ቀጣይ ምዕራፍ ለማሻገር መስማማታቸው ቢገለጽም፣ አሁንም ልዩነታቸው ምን ላይ እንደሆነ በዝርዝር አልታወቀም፡፡

  ከዚህ ቀደም በመደመርና በፓርቲዎች ውህደት ላይ ያላቸውን ልዩነት በኦሮሞ ባህል መሠረት ስምምነት ከተደረገ በኋላ ልዩነታቸውን አጥበው፣ ከዚህ በኋላ በጠንካራ አንድነት በጋራ በመሥራት የሕዝቡን ድል ወደ አዲስ ምዕራፍ ለማሸጋገር ከስምምነት መደረሱ ብቻ ነው የተነገረው፡፡ ስምምነቱ እንዴት እንደተካሄደና ምን ዓይነት የሐሳብ ልውውጥ እንደተደረገ አልታወቀም፡፡

  ነገር ግን ስምምነት የተደረሰው የቀድሞ ኦዴፓ ሥራ አስፈጻሚዎችና ነባር አመራሮች በጋራ ባደረጉት ውይይት እንደሆነ፣ ፓርቲው የዴሞክራሲርዓትንና በኦሮሞ ባህል መሠረት ውስጣዊ ችግሩንና የሕዝቡን ጥያቄ ለመመለስ ጠንክሮ እንደሚሠራ ተገልጿል፡፡

  ‹‹በፖለቲካ ሒደት ውስጥ በተለይ ደግሞ ሪፎርም በሚደረግበት ወቅት የሐሳብ ልዩነቶች መኖራቸው የተለመደ መሆኑ ነው የተጠቆመው፡፡ የሐሳብ ልዩነት መኖር በራሱ ችግር እንዳልሆነ የተገለጸ ሲሆን፣ ትልቁ ነገር የሐሳብ ልዩነትን በዴሞክራሲያዊ መንገድ ለመፍታት ዝግጁ መሆኑ ተገልጿል፤›› ሲል ኢሕአዴግ ጠቁማል፡፡

  ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይና አቶ ለማ የኦዴፓ ዋናና ምክትል ሊቀመናብርት ሲሆኑ፣ በ2010 ዓ.ም. በመጋቢት ወር የተካሄደው የኢሕአዴግ ምክር ቤት ስብሰባ ሊቀመንበር ለመምረጥ ሲዘጋጅ አቶ ለማ በቀድሞው ኦሕዴድ ጉባዔ ሊቀመንበርነታቸውን ለጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ በምርጫ እንዲተላለፍ ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡ ሊቀመንበሩ ሥልጣናቸውን በገዛ ፈቃዳቸው በለቀቁት የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ምትክ በፓርላማ ስለሚሰየም፣ አቶ ለማ ደግሞ የፓርላማ አባል ስላልነበሩና ሕጉ ስለማይፈቅድላቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም. ሥልጣኑን ለመረከብ ችለዋል፡፡ በዚህም ምክንያት የሁለቱ ወዳጅነትና መተሳሰብ ለሥልጣን የማይበገር ተብሎ ሲወደስ እንደነበር አይዘነጋም፡፡

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  [በተቋሙ ሠራተኞች የተወከሉ አንድ ባልደረባ ሚኒስትሩን ለማነጋገር ቀጠሮ ይዘው ወደ ቢሯቸው ገቡ]

  ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም ሰላም ... ተቀመጥ! አመሠግናለሁ ክቡር ሚኒስትር!...

  የጉራጌ ዞን ጥያቄና የክላስተር አደረጃጀት የገጠመው ተቃውሞ

  መንግሥት የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል አካል የነበሩ ዞኖችንና...

  አዋሽ ባንክ ካፒታሉን ወደ 55 ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ያስገደደው ምክንያት ምንድን ነው?

  ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላላ ጉባዔውን ያካሄደው አዋሽ ባንክ የ43 ቢሊዮን...

  አቢሲኒያ ባንክ ካለፈው ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው ትርፍ በማግኘት አዲስ ታሪክ አስመዘገበ

  አቢሲኒያ ባንክ ከቀደሚ የሒሳብ ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው...