Thursday, December 1, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - ማስታወቂያ -
  - ማስታወቂያ -

  በመሬትና በምግብ ዋስትና ላይ የአራት ወራት የውይይት መርሐ ግብሮች ተዘጋጁ

  - ማስታወቂያ -

  ተዛማጅ ፅሁፎች

  በሁሉም ክልሎች ከፍተኛ የእርሻ መሬት እጥረት እንዳለ በጥናት ታውቋል

  ‹‹መሬት፣ የመሬት አጠቃቀምና የምግብ ዋስትና በኢትዮጵያ›› በሚል ርዕስ ለአራት ወራት በአዲስ አበባና በሦስት ክልሎች የሚካሄዱ ዘጠኝ የውይይት መርሐ ግብሮች መዘጋጀታቸውን፣ ፎረም ፎር ሶሻል ስተዲስ አስታወቀ፡፡

  ባለፉት ሃያ ዓመታት ሲያደርገው እንደቆየው ሁሉ በዚህ አንገብጋቢ ወቅታዊ ርዕስ ላይ የሚያተኩሩና ሁሉም ባለድርሻ አካላት የሚሳተፉባቸው፣ ለአራት ወራት (ከታኅሳስ 16 እስከ መጋቢት 24 ቀን 2012 ዓ.ም.) የሚዘልቁ ሕዝባዊ የውይይት መድረክ መርሐ ግብሮች አዘጋጅቻለሁ ሲል ፎረም ፎር ሶሻል ስተዲስ ገልጿል።

  በመርሐ ግብሮቹ መሠረት በአገር አቀፍ የመሬትና የምግብ ዋስትና ጉዳዮችን በተመለከተ በስድስት የተመረጡ ርዕሶች ላይ በአዲስ አበባ፣ እንዲሁም አሳሳቢ በሆኑ ክልል ተኮር ተመሳሳይ ጉዳዮች ላይ በሦስት ክልሎች (በኦሮሚያ፣ በትግራይና በአማራ) በአጠቃላይ ዘጠኝ ዝግጅቶች የሚካሄዱ መሆኑን፣ በእያንዳንዱ መድረክ ላይ ለውይይቶቹ መነሻ የሚሆኑ ጥናታዊ ጽሑፎች በየዘርፉ ባለሙያዎች እንደሚቀርቡ ለማወቅ ተችላል፡፡

  ‹‹ኢትዮጵያ ፈርጀ ብዙ የኢኮኖሚና የማኅበራዊ ዕድገትን ለማስመዝገብ የተለያዩ ፖሊሲዎችን ነድፋና ስትራቴጂዎችን ቀይሳ በመንቀሳቀስ ላይ መሆኗ ይታወቃል። በመሆኑም በተለይ ባለፉት ሁለት አሥርት ዓመታት አመርቂ ውጤቶችን ለማስመዝገብ ችላለች። እ.ኤ.አ. ከ2007 እስከ 2017 ባሉት አሥር ዓመታት የአገሪቱ ኢኮኖሚ በአማካይ በዓመት 10.3 በመቶ በማደግ፣ በዓለም በፈጣን ሁኔታ በማደግ ላይ ካሉት አገሮች ተርታ ለመሠለፍ አስችሏታል፤›› ያለው ፎረም ፎር ሶሻል ስተዲስ፣ በተመሳሳይ በመሠረተ ልማት መስፋፋትና የማኅበራዊ አገልግሎቶችን በማዳረስ ረገድም መልካም ውጤቶች መመዝገባቸውን አስታውሷል፡፡

  ይሁን እንጂ እነዚህ መልካም ውጤቶች አንደተጠበቁ ሆነው፣ አገሪቱ ዛሬም በዕድገት ወደ ኋላ ከቀሩ አገሮች ተርታ ለመውጣት አልቻለችም ብሏል።

  የኢንዱስትሪና የአገልግሎት ዘርፎችን በማሳደግ ሥራ አጥነትን ለመቀነስ የሚደረገው ጥረት የተሳካ ነበር ለማለት እንደማያስደፍር፣ ዛሬም የአገሪቱ ኢኮኖሚ በግብርናው ክፍለ ኢኮኖሚ ላይ ጥገኛ እንደሆነ፣ የግብርና ኢኮኖሚው ከወጪ ምርቶች (Export Items) ውስጥ 84 በመቶ የሚሸፍን መሆኑንና በሥራ ላይ ከተሠማራው የሰው ኃይል ውስጥም የ80 በመቶ ያህል ድርሻ እንዳለው ጠቁሟል።

  ‹‹በዝናብ ላይ በእጅጉ ጥገኛ የሆነው የግብርናው ክፍለ ኢኮኖሚ የተለያዩ የተፈጥሮ፣ አካባቢያዊ፣ የቴክኖሎጂና መዋቅራዊ ችግሮች በስፋት ይስተዋሉበታል። የዝናብ እጥረትና ወቅቱን አለመጠበቅ፣ የአየር ንብረት ለውጥ አሉታዊ ተፅዕኖዎች፣ የመሬት መራቆትና የአፈር መሸርሸር ዋና ዋናዎቹ የተፈጥሮ ተግዳሮቶች ሲሆኑ፣ አነስተኛ አርሶ አደሮችን በሚገባ ያማከለ የመሬት ሥሪት ጥያቄዎች፣ ወጥ የሆነና የተፈጥሮ ሀብትን ሥርጭት ያገናዘበ የመሬት አጠቃቀም ፖሊሲ አለመኖር፣ እንዲሁም ለአነስተኛ ገበሬዎች የሚሰጡ ድጋፎች መጠንና ጥራት ማነስ ክፍለ ኢኮኖሚውን አንቀው ከያዙት መዋቅራዊ ችግሮች መካከል ይጠቀሳሉ፤›› ሲልም ያለውን ችግር አመላክቷል፡፡

  በአሁኑ ጊዜ በሁሉም ክልሎች የእርሻ መሬት እጥረት በከፍተኛ ደረጃ እንደሚስተዋልና የነፍስ ወከፍ የእርሻ መሬት መጠን ከዓመት ወደ ዓመት እየቀነሰ እንደመጣ ጥናቶች ያመለክታሉ ያለው ፎረም ፎር ሶሻል ስተዲስ፣ የዚህ ችግር ዋና ሰለባዎች ደግሞ ወደ ሥራ ዓለም የሚቀላቀሉ አዳዲስ ወጣቶች እንደሆኑ የታወቀ መሆኑን አስረድቷል፡፡

  ‹‹ለዚህ በውስብስብ ችግሮች ለተሞላ ክፍለ ኢኮኖሚ መፍትሔ መስጠትና ምርታማነቱን ማሳደግ ለምናልመው የተሻለ አገር የመፍጠር ጥረት ወሳኝ መሆኑ አያጠያይቅም። በዚህ ረገድ ክፍለ ኢኮኖሚው በሚመራባቸው ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች ላይ በመወያየት ከወቅቱ ተጨባጭ ሁኔታዎች ጋር የተገናዘቡ አማራጮችን ማቅረብ አስፈላጊነቱ እጅግ ከፍተኛ ነው፤›› ሲልም የውይይቶቹን አስፈላጊነት አስገንዝቧል።

  በዚህም መሠረት የመጀመርያው የውይይት መርሐ ግብር ሐሙስ ታኅሳስ 16 ቀን 2012 ዓ.ም. በአዲስ አበባ በአዝማን ሆቴል የተዘጋጀ ሲሆን፣ የመወያያ ርዕሱም ‹‹የመሬት ሥሪትና ተግዳሮቱ በኢትዮጵያ›› ነው፡፡ በርዕሰ ጉዳዩ ላይ ጥናታዊ ጽሑፍ አቅራቢው የፎረም ፎር ሶሻል ስተዲስ ከፍተኛ የምርምር ፌሎ አቶ ደሳለኝ ራህመቶ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡

  spot_img
  - Advertisement -spot_img

  የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

  - ማስታወቂያ -

  በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች