Monday, October 2, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትካፍ የዓመቱ ምርጥ ተጨዋቾችና አሠልጣኞች ዝርዝር ይፋ አደረገ

ካፍ የዓመቱ ምርጥ ተጨዋቾችና አሠልጣኞች ዝርዝር ይፋ አደረገ

ቀን:

የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) በአፍሪካ የውስጥ ሊግ የሚጫወቱ ተጫዋቾችን ለማበረታታት በሚል ራሱን የቻለ የውስጥ ሻምፒዮና ማድረግ ከጀመረ ሰነባብቷል፡፡ ይሁንና ከሰሞኑ በአውሮፓ በተለይም በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በመጫወት ላይ የሚገኙት የሊቨርፑሎቹ ግብፃዊው ሞሐመድ ሳላህና ሴኔጋላዊ ሴዲዮ ማኔ እንዲሁም የማንችስተር ሲቲው አልጀሪያዊ ሪያድ ማህሬዝን የመጨረሻዎቹ ዕጩዎች ሆነው ቀርበዋል፡፡

በአራት ዓመቱ አንድ ጊዜ ከሚከናወነው የዓለም ዋንጫ ውጭ አፍሪካን ጨምሮ የአውሮፓ፣ የእስያ፣ የደቡብና የሰሜን አሜሪካ አኅጉራት ሁሉም የየራሳቸውን የውስጥ ሻምፒዮና እንደሚያደርጉ ይታወቃል፡፡ ሁሉም የየራሳቸው የዓመቱ ምርጥ ተጫዋቾችን ምርጫም ያደርጋሉ፡፡ የካፍን ምርጫ ከእነዚህ አገሮች ምርጫ የሚለየው በአውሮፓ ለሚጫወቱ ተጫዋቾች ቅድሚያ መስጠቱ ነው፡፡ ካፍ የአፍሪካ አገሮች ዋንጫ (ቻን) ብሎ በየሁለት ዓመቱ የሚያደርገው ሻምፒዮና ኮከቦችስ ማስባሉ የማይቀር ነው፡፡

ካፍ ለ2019 የአፍሪካ አገሮች ምርጫ ዕጩ አድርጎ ካቀረባቸው ውስጥ የመጨረሻዎቹን ሦስት ዕጩዎች ዝርዝር ይፋ አድርጓል፡፡ እንደ ድረ ገጹ መረጃ ከሆነ፣ የማንችስተር ሲቲው አልጀሪያዊ ሪያድ ማህሬዝ እንዲሁም ለሊቨርፑላውያን እንደ ልዩ ገጸ በረከት የሚታዩት ግብፃዊ ሞሐመድ ሳላህና ሴኔጋላዊ ሴዲዮ ማኔ መሆናቸው ታውቋል፡፡

ለሊቨርፑል የሚጫወቱት ከሁለቱ አፍሪካውያን መካከል፣ ሴዲዮ ማኔ ባለፈው የአፍሪካ ዋንጫ አገሩ ሴኔጋልን ለፍጻሜ ሲያደርስ፣ ሞሐመድ ሳላህ ለፈርኦኖቹ ግብፃውያን በጉዳት ምክንያት አለመሠለፉ ይታወቃል፡፡ ለሊቨርፑል ግን የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ ያጣው በአንድ ነጥብ ልዩነት በማንችስተር ሲቲ ሲሆን፣ በአውሮፓ ዋንጫ ላይ በመጀመሪያው አሠላለፍ ቢገባም በሪያል ማድሪዱ ሰርጂዮ ራሞስ ጉዳት ደርሶበት ጨዋታውን ሳያጠናቅቅ መቅረቱ አይዘነጋም፡፡

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የዓምና ሻምፒዮን ማንችስተር ሲቲ ኮከቡ ሪያድ ማህሬዝ፣ አገሩ አልጀሪያን ለአፍሪካ ዋንጫ ድል አብቅቷል፡፡ ከዚህ አንጻር የካፍ ምርጫ ማህሬዝንና ማኔን ለአፍሪካ ምርጥ ዕጩ አድርጎ ማቅረቡ ተጠባቂ ያደርገዋል የሚሉ አሉ፡፡ ካፍ በተመሳሳይ በሴቶች ዕጩ አድርጎ ያቀረባቸው ተጫዋቾችን ዝርዝር ይፋ አድርጓል፡፡

ካሜሮናዊቷ ባሴ ሬንጋ፣ ናይጀሪያዊቷ አሲሳት ኦሾአል እና ደቡብ አፍሪካዊቷ ቴምቢ ጋትላና የመጨረሻዎቹ ሆነው ቀርበዋል፡፡ ከዚህ ውጭ የሴኔጋል ብሔራዊ ቡድን አሠልጣኝ አልዬ ሲሴ፣ የአልጀሪያ ብሔራዊ ቡድን አሠልጣኝ ጃሚል ቤልማዲ ዕጩዎች ሲሆኑ፣ በክለብ ደረጃ ደግሞ የቱኒዝያው ኤስፔራንስ ሞኢን ቻባኒ ከምርጦቹ ተካተዋል፡፡

የምርጫው ውጤት የሚወሰነው የካፍ አባል አገሮች፣ የብሔራዊ ቡድን አሠልጣኞች፣ ቴክኒካል ዳይሬክተሮችና የብሔራዊ ቡድን አምበሎች በሚሰጡት ድምፅ መሠረት ይሆናል፡፡ አሸናፊዎቹ ታኅሣሥ 28 ቀን 2012 ዓ.ም. በግብፅ በሚደረገው ሥነ ሥርዓት እንደሚሆንም ድረ ገጹ አክሏል፡፡    

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ተመድንና ዓለም አቀፋዊ ሕግን ከእነ አሜሪካ አድራጊ ፈጣሪነት እናድን!

በገነት ዓለሙ በእኔ የተማሪነት፣ የመጀመርያ ደረጃ ተማሪነት ጊዜ፣ የመዝሙር ትምህርት...

የሰላም ዕጦትና የኢኮኖሚው መንገራገጭ አንድምታ

በንጉሥ ወዳጅነው ፍራንክ ቲስትልዌይት የተባሉ አሜሪካዊ ጸሐፊ ‹‹The Great Experiment...

ድህነት የሀብት ዕጦት ሳይሆን ያለውን በአግባቡ ለመጠቀም አለመቻል ነው

በአንድነት ኃይሉ ድህነት ላይ አልተግባባንም፡፡ ብንግባባ ኖሮ ትናንትም ምክንያት ዛሬም...