Sunday, April 14, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህል‹‹የጋራ ድንበር›› በሥነ ጥበብ ፌስቲቫል

‹‹የጋራ ድንበር›› በሥነ ጥበብ ፌስቲቫል

ቀን:

በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል ያለው ድንበር በተዘጋ በ20 ዓመቱ የተከፈተበት የዓምናው ክስተት የብዙዎችን ቀልብ የገዛ ነበር፡፡ በሁለቱ አገሮች መካከል በ1990ዎቹ መጀመርያ ሰፍኖ የነበረው ጦርነት ከ80,000 በላይ ሰዎችን ሰለባ አድርጎ አልፏል፡፡

ሁለቱ እህትማማች አገሮች የጋራ ታሪክ፣ ባህልና ቋንቋ ያላቸው አሥራ ሦስት ወራትን በዘመን አቆጣጠራቸው በመያዝ የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ ከሁለት አሠርታት በኋላ ለሰፈነው ሰላማዊ አየርና ታሪካዊ ክስተት ይበልታን ለመስጠት በዓለም አቀፋዊ የቪዲዮ ሥነ ጥበብ ፌስቲቫል አጭር ቪዲዮን አካትቷል፡፡

ከታኅሣሥ 16 እስከ 22፣ 2012 ዓ.ም. ድረስ በአዲስ አበባ ከተማ ለሦስተኛ ጊዜ በተለያዩ ቦታዎች የሚካሄደው ዓመታዊው ፌስቲቫል ኢትዮጵያንና የውጭ አገር የሥነ ጥበብ ባለሙያዎች ይሳተፉበታል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

‹‹የጋራ ድንበር›› በሚል ፈትለ ሐሳብ (theme) አሥራ ስድስት ሥነ ጠቢባን መካከል ሦስቱ ኢትዮጵያውያን (ኅሊና መታፈሪያ/ኢትዮ አሜሪካ/፣ ክብሮም ገብረ መድኅንና ቴዎድሮስ ክፍሌ ናቸው፡፡

መክፈቻው ሐሙስ የካቲት 16 ቀን ከምሽቱ 12 ሰዓት በዘመናዊ ሥነ ጥበብ ሙዚየም ገብረ ክርስቶስ ደስታ ማዕከል የሚያደርግ ሲሆን፣ በተከታታይ ስድስት ቀናት ከሚቀርቡት ውስጥ በአለ የሥነ ጥበብና ዲዛይን ትምህርት ቤት ዐውደ ጥናት፣ የግጥምና ዳንስ ቅንብር በምሕረት ከበደ አማካይነት በፈንዲቃ ባህል ማዕከል የሚቀርበው ይገኙበታል፡፡ መዝጊያው ታኅሣሥ 22 ቀን በ12 ሰዓት በጅማ ጠጅ ቤት እንደሚሆን መርሐ ግብሩ ያሳያል፡፡

‹‹የጋራ ድንበር›› በሥነ ጥበብ ፌስቲቫል

 

በፌስቲቫሉ ከመርሐ ግብሩ በትይዩ ከማርሴ (ፈረንሣይ) የኢንተርናሽናል ቪዲዮ አርት ፕሮግራም የሚቀርብ የቪዲዮ መሰናዶ እንደሚኖር ተገልጿል፡፡

‹ዘ ሶሻል ኔትወርክ ዳየሪ›› የሚል ርዕስ ያለውና የአምስት ደቂቃ ግድም አጭር ቪዲዮ በሞባይል ስልክ የተቀረፀ የኢትዮ ኤርትራ ግንኙነት ዳግም ትንሣኤ ያገኘበትን ገጽታ የሚያሳይ ነው፡፡ በቴዎድሮስ ክፍሌ ሸዋ ሞልቶት የቀረበው ሥራ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ከፕሬዚዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ ጋር በአሥመራ የነበራቸው በፍንደቃ የታጀበ ሳቅን የሚያሳይ ነው፡፡

ሌላው ሥራ በክብሮም ገብረ መድኅን የቀረበው አንጥረኛው (Melting Jewels) የተሰኘው ሥራው ነው፡፡ ከግላዊ የሕይወት ገጠመኙ በመነሳት ያዘጋጀው የአምስት ደቂቃ ተኩል ፊልሙ በሕይወት ስለሌሉት አባቱ የሚያወሳ ነው፡፡ ቤተሰቡ አባቱን ብቻ አይደለም ያጣው፣ ከሠላሳ ዓመታት በላይ የወርቅ የብር ጌጣጌጦችን እያመረቱ የሚያገበያዩበትን መደብር ጭምር እንጂ፡፡ እነዚህን ከትዝታ ጓዳ እየጨለፈ ትዝታን ለማኖር በቪዲዮ አቀናብሮታል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ በርካታ ባህልን፣ ማኅበራዊ ሕይወትንና የጋራ የኑሮ ዘይቤ ያቀፉት የተለያዩ ቦታዎች በ‹‹ልማት›› እንዲፈርሱ መደረጉና ቦታዎቹ ለአዳዲስ ሕንፃዎችና መሠረተ ልማቶች መዘጋጀታቸው ሥነ ጠቢቡ ላዘጋጀው አኒሜሽን ግብዓት ሆነውታል፡፡ 

‹‹የጋራ ድንበር›› ፌስቲቫል መርሐ ግብር

ታኅሣሥ 16 ቀን በ12፡00 ሰዓት የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት በዘመናዊ ሥነ ጥበብ ሙዚየም ገብረ ክርስቶስ ደስታ ማዕከል

ታኅሣሥ 17 ቀን በ8፡00 ሰዓት የቪዲዮ ሥነ ጥበብ ዐውደ ጥናት በአለ የሥነ ጥበብና ዲዛይን ትምህርት ቤት፤ ማታ በ1፡00 ሰዓት በእሙዬ ማጀት

ታኅሣሥ 18 ቀን በ12፡00 ሰዓት ግጥምና ዳንስ በምሕረት ከበደ፣ በፈንዲቃ ባህል ማዕከል

ታኅሣሥ 19 ቀን በእንጦጦ በ12፡00 ሰዓት

ታኅሣሥ 20 ቀን በ10፡00 ሰዓትና በ12፡00 ሰዓት በአለ የሥነ ጥበብና ዲዛይን ትምህርት ቤትና በአሊያንስ ኢትዮ ፍራንሴዝ

ታኅሣሥ 21 ቀን ከ6-11 ሰዓት በኧርበን ሴንተር የፓናል ውይይት

ታኅሣሥ 22 ቀን በ12፡00 ሰዓት የመዝጊያ ሥነ ሥርዓት በጅማ ጠጅ ቤት

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ያልተቃናው የልጆች የንባብ ክህሎት

አንብቦና አዳምጦ መረዳት፣ የተረዱትን ከሕይወት ጋር አዋህዶ የተቃና ሕይወት...

እንስተካከል!

ሰላም! ሰላም! ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ እንዲሁም የሰው ዘር በሙሉ፣...

የሙዚቃ ምልክቱ ሙሉቀን መለሰ ስንብት

የኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ በ1950ዎቹ እና በ1960ዎቹ በኪነ ጥበባትም ሆነ...

‹‹ደስታ›› የተባለችው አማርኛ ተናጋሪ ሮቦት በሳይንስ ሙዚየም

‹‹እንደ ሮቦት ዋነኛው አገልግሎቴ ውስብስብ የሆኑ የቴክኖሎጂ ውጤቶችንና አሠራሮችን...