Saturday, December 3, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ሳይንስና ቴክኖሎጂ‹‹አቦል›› እና ‹‹ቡና›› ለኤክዞፕላኔትና ለኮከብ ስያሜ ዋሉ

  ‹‹አቦል›› እና ‹‹ቡና›› ለኤክዞፕላኔትና ለኮከብ ስያሜ ዋሉ

  ቀን:

  ‹‹የቫን ጎህ ‹ስታሪ ናይት›፣ የኢትዮጵያ የቡና ሥነ ሥርዓትና የአላስካ ወንዝ በጋራ የሚያገናኛቸው ምንድን ነው?›› ብሎ የጠየቀው የስፔስ ዶት ኮም ዘጋቢ ሜግሃን ባረልስ ምላሹንም አስቀምጧል፡፡ ሁሉንም ያስተሳሰራቸው በምህዋረ ፀሐይ ውስጥ ለተገኙት ከዋክብትና ፕላኔቶች ስያሜ መዋላቸው ነው፡፡

  የዓለም የሥነ ፈለክ ኅብረት (አይኤዩ) ከሁለት ሳምንት በፊት ከፓሪስ ባወጣው መግለጫ ለ112 ኤክዞ ፕላኔት (ከሥርዓተ ፀሐይ ውጭ ያሉ) እና ከዋክብት ከተለያዩ አገሮች ያገኘውን አዳዲስ ስሞች መሰየሙን አስታውቋል፡፡ ከነዚህም መካከል ከኢትዮጵያ ባህላዊ የቡና ሥርዓት የመነጨው ‹‹አቦል›› (በሦስት ዙር ከሚጠጣው የመጀመርያው መጠርያ) “HD 12175” ተብላ ለምትታወቀው ኤክዞፕላኔት ስያሜነት ውሏል፡፡ ኮከቧም ‹‹ቡና›› መባሏ በድረ ገጹ ተዘግቧል፡፡

  ከኔዘርላንድ የተገኘው ስያሜ ከሥነ ሥዕል ቅርስ ሲሆን፣ ይህም የ19ኛው ምዕት ዓመት ታዋቂ ሠዓሊ ቫን ጎህ ከሣለው ‹‹ስታሪ ናይት›› የተገኘ ነው፡፡ እያንዳንዱ አገር ከባህሉ፣ ከትውፊቱና ከእሴቱ ወይም ከመልክዐ ምድር በመነሳት ለኮከብና ለፕላኔት መጠርያ ይሆኑ ዘንድ ለውድድሩ አቅርቦ ነበር፡፡ ከነዚህም መካከል በአሜሪካ ደቡባዊ ምዕራብ የሚገኘው አላስካ ወንዝ ከተመረጡት አንዱ ሆኗል፡፡ ለከዋክብትና ለኤክዞፕላኔት ስም ያሰየሙ የአፍሪካ አገሮች 18 መሆናቸው ታውቋል፡፡

  በምህፃሩ አይኤዩ በመባል የሚታወቀው የዓለም የሥነ ፈለክ ኅብረት፣ ለኤክዞፕላኔትና ለከዋክብቱ ከየአገሩ መጠርያ ለመምረጥ የፈለገው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እ.ኤ.አ. 2019 ኢንተርናሽናል የአገር በቀል ቋንቋዎች ዓመት ብሎ ከመሰየሙ ከ100ኛ ዓመት ምሥረታው ጋር በማያያዙ ነው፡፡

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  [በተቋሙ ሠራተኞች የተወከሉ አንድ ባልደረባ ሚኒስትሩን ለማነጋገር ቀጠሮ ይዘው ወደ ቢሯቸው ገቡ]

  ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም ሰላም ... ተቀመጥ! አመሠግናለሁ ክቡር ሚኒስትር!...

  የጉራጌ ዞን ጥያቄና የክላስተር አደረጃጀት የገጠመው ተቃውሞ

  መንግሥት የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል አካል የነበሩ ዞኖችንና...

  አዋሽ ባንክ ካፒታሉን ወደ 55 ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ያስገደደው ምክንያት ምንድን ነው?

  ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላላ ጉባዔውን ያካሄደው አዋሽ ባንክ የ43 ቢሊዮን...

  አቢሲኒያ ባንክ ካለፈው ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው ትርፍ በማግኘት አዲስ ታሪክ አስመዘገበ

  አቢሲኒያ ባንክ ከቀደሚ የሒሳብ ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው...