በደቡብ ጎንደር የሚገኘውና 1,500 ዓመታት በላይ ያስቆጠረው ገዳም ዙር አባ አቡነ አረጋዊ ጽርሐ አርያም ይባላል፡፡ ገዳሙ በምሥራቅ፣ በምዕራብና በሰሜን 400 ሜትር፣ በደቡብ 300 ሜትር ርዝመት በሆነ ገደል ላይ የተገደመ ነው፡፡ ቦታውን ከዘጠኙ ቅዱሳን አንዱ በሆኑትና ገዳሙ በስማቸው የተሰየመው አቡነ አረጋዊ ከቅዱስ ያሬድ ጋር በመሆን ቀድሰውታል፡፡ ከኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ዐበይት ትምህርቶች አንዱ የቅዱስ ያሬድ ድርሰት የሆነው የዝማሬና መዋሥዕት ትምህርት ማስመስከሪያ ሆኖም እያገለገለ ነው፡፡ ፎቶዎቹ የገዳሙን መልክዐ ምድራዊ ገጽታና ማኅበራዊ ሕይወት ከነንዋየ ቅድሳቱ ጋር በከፊል ያሳያሉ፡፡