Friday, December 8, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊዘንድሮ 10.6 ሚሊዮን ዜጎች አስቸኳይ ሰብዓዊ ድጋፍ ይሻሉ

ዘንድሮ 10.6 ሚሊዮን ዜጎች አስቸኳይ ሰብዓዊ ድጋፍ ይሻሉ

ቀን:

በየአካባቢው በሚከሰቱ ግጭቶችና ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር ተያይዘው በሚከሰቱ የድርቅ አደጋዎች ዘንድሮ 10.6 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን አስቸኳይ ሰብዓዊ ዕርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮችን አስተባባሪ ቢሮ (ኦቻ) አስታወቀ፡፡

ድርጅቱ ይፋ ያደረገው ሪፖርት እንደሚያሳየው፣ የሰብዓዊ ዕርዳታ ከሚያስፈልጋቸው 10.6 ሚሊዮን ዜጎች መካከል 6.2 ሚሊዮን ያህሉ አፋጣኝ ዕርዳታ የሚሹና በአስከፊ ሁኔታ ላይ የሚገኙ ናቸው፡፡ አብዛኞቹ ሰብዓዊ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው 3.3 ሚሊዮን ወይም ዘጠኝ በመቶ የኦሮሚያ ክልል ነዋሪዎች ናቸው፡፡ ሁለተኛው ሰፊ ተጠቂ ዜጎች የሚኖሩበት ክልል ሶማሌ ሲሆን፣ 2.4 ሚሊዮን ወይም 39 በመቶ የሚሆኑ የክልሉ ነዋሪዎች ለዚህ ችግር ተጋላጭ እንደሚሆኑ ሪፖርት ተደርጓል፡፡ በአማራ ክልል የሚገኙ አንድ ሚሊዮን ሰዎችም ሰብዓዊ ድጋፉ እንደሚያስፈልጋቸው ሪፖርቱ ያትታል፡፡

አብዛኞቹ ዜጎች ለሰብዓዊ ቀውስ የሚዳረጉት የአየር ንብረት ለውጥ በሚፈጥረው ተፅዕኖ እንደሆነ ተገልጿል፡፡ ባለፉት ወራት የጣለው ወቅቱን ያልጠበቀና ዝቅተኛ ዝናብ ለውኃ እጥረትና ለግጦሽ እጥረት መዳረጉን፣ ይህም በቆላማ አካባቢዎች የምግብ ዋስትናን አደጋ ላይ እንደጣለው ተመልክቷል፡፡ ዝናብ ወቅቱን ጠብቆ ባለመዝነቡ ያልታረሱ ማሳዎች ብዙ እንደሆኑም ሪፖርቱ ያሳያል፡፡

በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ግጭት መኖር የምግብ ዋስትና ጉዳዩን አሳሳቢ ደረጃ ላይ እያደረሰ እንደሚገኝም በሪፖርቱ ተካቷል፡፡ በየአካባቢው የሚፈጠሩ ግጭቶች አርሶ አደሩ ወቅቱን ጠብቆ ማረስ እንዳይችል፣ በግርግር ያዘጋጀውን ዘርና የማረሻ ቁሳቁስ እንደሚያጣ እንዳዳረገም ተገልጿል፡፡

በአየር ንብረት ለውጥና በግጭት ምክንያት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች በየዓመቱ አፋጣኝ የሰብዓዊ ዕርዳታ ይፈልጋሉ፡፡ የምግብ ዋስትና ጉዳይ ቁልፍ ችግር ሆኖ የቆየ አገራዊ አጀንዳ ሲሆን፣ አርብቶ አደሩና ከፊል አርብቶ አደሩን በስፋት እያጠቃ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡ 44 በመቶ የሚሆኑ የምግብ አቅርቦት ችግር ያለባቸው ዜጎች የሚኖሩት በኦሮሚያ ክልል መሆኑንም ሪፖርቱ ያሳያል፡፡

ሁለት ሚሊዮን የአገር ውስጥ ተፈናቃዮችም ተመሳሳይ ዕርዳታ እንደሚፈልጉ ተጠቁሟል፡፡ መንግሥት 2.1 ሚሊዮን የአገር ውስጥ ተፈናቃዮችን ወደ ቀዬአቸው መመለሱን ሪፖርት ቢያደርግም፣ እስካለፈው ኅዳር ወር ድረስ ሁለት ሚሊዮን ዜጎች በግጭትና በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ከቀዬአቸው ተፈናቅለው እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡

በየአካባቢው የሚቀሰቀሱ ግጭቶች፣ ውጥረቶችና አለመረጋጋቶች ለዕርዳታ ሠራተኞች ፈተና መሆናቸውን፣ በምዕራብና በደቡብ ኦሮሚያ ተንቀሳቅሶ ለመሥራት ይበልጥ ችግር መሆኑንም ኦቻ በሪፖርቱ አካቷል፡፡ በጋምቤላ ክልል የተገደሉት የዕርዳታ ሠራተኞች ጉዳይ እስካሁን እንዳልተጣራለትም አስታውቋል፡፡ ለተጎጂዎች የሰብዓዊ ዕርዳታዎችን ለማቅረብ የተደራሽነት ችግር መኖሩን፣ አንዳንድ የተደራሽነት ችግሮች ከመሠረተ ልማት በዘለለም እንደሆኑ ተንትኗል፡፡ በአማራ ክልል አዊ ዞን፣ በደቡብ ክልል ጌዴኦ ዞን፣ ‹‹የአገር ውስጥ ተፈናቃዮች መኖራቸውን የሚክዱ ባለሥልጣናት›› የዜጎችን ሰብዓዊ ድጋፍ የማግኘት መሠረታዊ መብት የሚጥሱበትን ሁኔታ በማሳያነት ተወስቷል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ታዋቂው የኤሌክትሮኒክስ ብራንድ አይቴል የስትራቴጂ ለውጥ አካል የሆነውን አዲስ አርማ እና መለዮ ይፋ አደረገ።

በአለማችን ታዋቂ ከሆኑት የኤሌክትሮኒክስ ብራንዶች መካከል አንዱ የሆነው እና...

የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ጥሪ ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ

ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ የሸገር አነስተኛ የፋይናንስ...

[የክቡር ሚኒስትሩ ጸሐፊ፣ የሌላ ሚኒስትር ጸሐፊ ከሆነችው የቅርብ ወዳጇ ጋር በስልክ እየተጨዋወቱ ነው]

አንቺ ግን ምን ሆነሽ ነው? ጠፋሁ አይደል? ጠፋሁ ብቻ?! ምን ላድርግ ብለሽ...

በሱዳን ላይ ያጠላው የመከፋፈል ዕጣና ቀጣናዊ ተፅዕኖው

የሱዳን ጦርነት ስምንተኛ ወሩን እያገባደደ ይገኛል፡፡ ጄኔራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን...