Saturday, December 2, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትየኦሊምፒክ ኮሚቴ ጽሕፈት ቤት በተመራጭ እንዲመራ ተወሰነ

የኦሊምፒክ ኮሚቴ ጽሕፈት ቤት በተመራጭ እንዲመራ ተወሰነ

ቀን:

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ሰሞኑን ባደረገው አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ ጽሕፈት ቤቱ በተመራጭ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ እንዲመራ የሚደነግግ ደንብ ማፅደቁ ታወቀ፡፡ የብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴው ጽሕፈት ቤት ዋና ጸሐፊ በመሆን ሲያስተዳድሩ የቆዩት አቶ ታምራት በቀለ ከነበሩበት ደረጃ ዝቅ ብለው በምክትል ኃላፊነት እንዲያገለግሉ መወሰኑ ተነግሯል፡፡

ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴው ባለፈው ቅዳሜ ጥር 2 ቀን 2012 ዓ.ም. በቢሾፍቱ (ደብረ ዘይት) በአዱላላ ሪዞርት ባካሔደው አስቸኳይ ጉባዔ ከጽሕፈት ቤቱ አደረጃጀት በተጨማሪ የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ቅድመ ዝግጅት በሚመለከት በቀረበው ዕቅድ ላይ መወያየቱን የሪፖርተር ምንጮች ገልጸዋል፡፡

የብሔራዊ አሊምፒክ ኮሚቴን አደረጃጀት በሚመለከት በስፋት ለውይይት ቀርቦ ሲነጋገርበት የነበረው የኦሊምፒክ ቻርተርን መነሻ በማድረግ ጭምር መሆኑ ተነግሯል፡፡ በተለይ ጽሕፈት ቤቱ በተመራጭ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል እንዲመራ ጉባዔው ውሳኔ ላይ ለመድረስ የተለያዩ አገሮች ተሞክሮ መውሰዱ ታውቋል፡፡ በማሳያነትም የዓለም አቀፍ ኦሊምፒክ ኮሚቴ (አይኦሲ) አባል አገሮች 53 በመቶ የሚሆኑት ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴዎች ጽሕፈት ቤቶቻቸውን የሚመሩት ዋና ጸሐፊዎች በአራት ዓመት አንድ ጊዜ በብሔራዊ ፌዴሬሽኖች በሚሰየሙ ተመራጮች ሲሆን፣ 47 በመቶ ደግሞ ላለፉት ስምንት ዓመታት የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ይተዳደርበት በነበረው በተቀጣሪ ዋና ፀሐፊ መሆኑ ተመልክቷል፡፡ በዋና ጸሐፊነት ሲያገለግሉ የቆዩትን አቶ ታምራት በቀለ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመቃወም ነፃነት ውዝግብ በኢትዮጵያ

ስሟ እንዳይገለጽ የጠየቀችው በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ የሾላ አካባቢ...

የሲሚንቶን እጥረትና ችግር ታሪክ ለማድረግ የተጀመረው አጓጊ ጥረት

በኢትዮጵያ በገበያ ውስጥ ለዓመታት ከፍተኛ ተግዳሮት በመሆን ከሚጠቀሱ ምርቶች...

የብሔር ፖለቲካው ጡዘት የእርስ በርስ ግጭት እንዳያባብስ ጥንቃቄ ይደረግ

በያሲን ባህሩ በሪፖርተር የኅዳር 9 ቀን 2016 ዓ.ም. ዕትም “እኔ...