Sunday, July 14, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትየድሬዳዋ እግር ኳስ ክለብ ቅዱስ ጊዮርጊስን ከሰሰ

የድሬዳዋ እግር ኳስ ክለብ ቅዱስ ጊዮርጊስን ከሰሰ

ቀን:

በውድድር ዓመቱ እየተከናወነ የሚገኘው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ስምንተኛ ሳምንት የጨዋታ መርሐ ግብር ባለፈው ቅዳሜና እሑድ ጥር 2 እና 3 ቀን 2012 ዓ.ም. አዲስ አበባን ጨምሮ በሁሉም ከተሞች ተከናውኗል፡፡ ይሁንና በአዲስ አበባ ስታዲየም በቅዱስ ጊዮርጊስና በድሬዳዋ ከተማ ቡድኖች መካከል የተደረገው ጨዋታ ከተጠናቀቀ በኋላ የድሬዳዋ እግር ኳስ ክለብ በቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች ያልታሰበ ጥቃት ‹‹ደርሶብኛል›› በሚል ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ክስ አቅርቧል፡፡

የድሬዳዋ እግር ኳስ ክለብ ሰኞ ጥቅምት 4 ቀን 2012 ዓ.ም. ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያቀረበው አቤቱታ እንደሚያስረዳው ከሆነ፣ የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ከቅድመ ጨዋታ ስብሰባው ዕለት አንስቶ ጨዋታው ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ ምንም ዓይነት ችግር አልገጠመውም፡፡ ችግሩ የተከሰተው ጨዋታው ከተጠናቀቀ በኋላ የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎችና አስተባባሪዎች የእንግዳው ቡድን አባላት በሚወጡበት በር በኩል መልበሻ ክፍል በመግባት አሠልጣኙንና አመራሮችን እንዲሁም ተጨዋቾችና የካሜራ ባለሙያ ላይ ድብደባና ማንገላታት በማድረሳቸው ነው፡፡

 የድሬዳዋ እግር ኳስ ክለብን ጨምሮ ዓምና እና ከዚያም በፊት ማዘውተሪያዎች የግጭት መንስኤዎች ሆነው ማሳለፋቸው ልብ ሊባል እንደሚገባ የሚናገሩ አሉ፡፡ ‹‹በቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች ተበድያለሁ›› ሲል ክስ ያቀረበው ድሬዳዋ ከክሶቹ መካከል በተለይ የቡድኑ ካሜራ ተቀምቶ በካሜራው ውስጥ የነበሩ ማስረጃዎች እንዲሰረዙ የተደረገበት አጋጣሚ ከስፖርታዊ ጨዋነት የራቀና ያፈነገጠ፣ የግለሰቦችን ሰብአዊ መብት የተጋፋ ድርጊት ለእግር ኳሱ ‹‹በቦሃ ላይ ቆረቆር›› የሚለውን የአበው አባባል ልብ ይሏል ይላሉ፡፡

ባለፈው እሑድ በአዲስ አበባ ስታዲየም የተደረገው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ በቅዱስ ጊዮርጊስ 3 ለ 2 አሸናፊነት መጠናቀቁ ይታወቃል፡፡ በሰባት ነጥብ 15ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ድሬዳዋ በቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች ‹‹ደርሶብኛል›› በሚል ካቀረበው አቤቱታ ውጪ በውድድር ዓመቱ አዲስ አበባን ጨምሮ በሁሉም ከተሞች ሲከናወኑ የቆዩት ጨዋታዎች ምንም ዓይነት የስፖርታዊ ጨዋነት ችግር አልገጠማቸውም፡፡

ካለፉት ዓመታት በተለየ በስፖርት ማዘውተሪያዎች ሰላማዊ የእግር ኳስ እንቅስቃሴውና የደጋፊዎች ሥርዓት ይበል በሚሰኝበት በዚህ ወቅት የድሬዳዋ እግር ኳስ ክለብ ያቀረበው አቤተታ፣ ‹‹ራሱ ቅሬታ አቅራቢው የድሬዳዋ እግር ኳስ ክለብና ቅሬታው የቀረበለት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፈዴሬሽን እንዲሁም ድርጊቱን ፈጽመዋል የተባሉት ደጋፊዎችና የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ አመራሮች ችግሩ እንዴትና ለምን ሊከሰት እንደቻለ ተነጋግረው ለሌሎች አርአያ በሚሆን መልኩ የመፍትሔው አካል ሊሆኑ ይገባል፤›› የሚሉ በርካታ ናቸው፡፡

ወደ ዘጠነኛው ሳምንት የጨዋታ መርሐ ግብር እየተሸጋገረ የሚገኘው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አሁን ላይ ሊጉን በሚመራው በመቐለ 70 እንደርታና በደረጃ ሰንጠረዡ ግርጌ በሚገኘው ወላይታ ድቻ መካከል ያለው የነጥብ ልዩነት 10 ነው፡፡ መሪው መቐለ 70 እንደርታ 16 ነጥብ ሲኖረው፣ ተከታዩ ፋሲል ከተማ 15 ሲሆን፣ ሦስተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ 14 እንዲሁም ቅዱስ ጊዮርጊስ 13 ነጥብ መጨረሻ ደረጃ ላይ የሚገኘው ወላይታ ድቻ በስድስት ነጥብ አንገት ለአንገት ተያይዘው ይገኛሉ፡፡

የድሬዳዋ እግር ኳስ ክለብ በቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች ‹‹ደርሶብኛል›› ስለሚለው ስፖርታዊ ጨዋነት መጓደልና ድርጊትን በተመለከተ የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማኅበር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ሰሎሞን በቀለ በበኩላቸው፣ ‹‹የድሬዳዋ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ክስ ማቅረቡ ሰምተናል፡፡ በጉዳዩ የብሔራዊ ፌዴሬሽኑን ውሳኔ እንጠብቃለን፣ እስከዚያው ግን አሁን ላይ የምንለው ነገር አይኖርም፤›› በማለት ከዝርዝሩ ተቆጥበዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሚዲያው በሕዝብ የህሊና ችሎት ከተዳኘ በቂ ነው!

መሰንበቻውን ድንገት ሳይታሰብ ያለ ማስጠንቀቂያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ...

የባህር በር ጉዳይ

በታምሩ ወንድም አገኘሁ ድሮ ድሮ ገና ልጅ ሆኜ ፊደል እንደቆጠርኩ...

አገሩ ፖለቲካዊ ስክነትና መደማማጥ ያስፈልገዋል

በንጉሥ ወዳጀነው    ኢትዮጵያ የሁላችንም የጋራ ቤት ነች፡፡ ‹‹ጥያቄዬ ተመለሰልኝ››፣...

የመንግሥት የሰብዓዊ መብት ተቋም ለምን የመንግሥት ሚዲያን ማስተማር አቃተው

በገነት ዓለሙ የአገራችን የ2016 የበጀት ዓመት መሰናበቻና የአዲሱ የ2017 በጀት...