Sunday, March 26, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ኢትዮ ቴሌኮም በስድስት ወራት ውስጥ 22.04 ቢሊዮን ብር ገቢ አገኘ

- ማስታወቂያ -

ተዛማጅ ፅሁፎች

ኢትዮ ቴሌኮም በበጀት ዓመቱ የመጀመርያ ስድስት ወራት (ከሐምሌ 2011 ዓ.ም. እስከ ታኅሳስ 2012 ዓ.ም.) 22. 04 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ ገቢ እንዳገኘ አስታወቀ፡፡

ኩባንያው በ126 ዓመት ታሪኩ ለመጀመርያ ጊዜ የዕቅዱን 104 በመቶ ማሳካት መቻሉን፣ እንዲሁም ገቢው ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ32 በመቶ ዕድገት ማሳየቱ ተገልጿል፡፡

የውጭ ምንዛሪ ከሚያስገኙ አገልግሎቶች 73 ሚሊዮን ዶላር የተገኘ መሆኑን፣ በዚህም የዕቅዱን 111 በመቶ ማሳካት መቻሉ ተጠቁሟል፡፡ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ116 በመቶ ዕድገት አሳይቷል፡፡

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ት ፍሬሕይወት ታምሩ ረቡዕ ጥር 6 ቀን 2012 ዓ.ም. በጽሕፈት ቤታቸው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ ኩባንያው በስድስት ወራት ውስጥ 3.89 ቢሊዮን ብር ታክስ፣ ሁለት ቢሊዮን ብር ዲቪደንድ ለመንግሥት እንደከፈለ ተናግረዋል፡፡ በቬንደር ፋይናንሲንግ ሞዳሊቲ ለተከናወኑ ፕሮጀክቶች ብድር 148.15 ሚሊዮን ዶላር (4.4 ቢሊዮን ብር) እንደተከፈለ ወ/ት ፍሬሕይወት አስረድተዋል፡፡

የኩባንያው የደንበኞች ብዛት 45.6 ሚሊዮን መድረሱና አጠቃላይ የቴሌኮም ስርፀት 45.4 በመቶ እንደ ደረሰ ተገልጿል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች