Saturday, June 10, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊበሦስት ክልሎች የኮሌራ ወረርሽኝ 25 ሰዎች ገደለ

በሦስት ክልሎች የኮሌራ ወረርሽኝ 25 ሰዎች ገደለ

ቀን:

ከታኅሳስ አጋማሽ እስካለፈው ሳምንት ድረስ በደቡብ፣ በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች በኮሌራ ወረርሽኝ የ25 ሰዎች ሕይወት ማለፉን፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ ማክሰኞ ጥር 12 ቀን 2012 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ አስታወቀ፡፡ ከ1,040 በላይ ሰዎች በወረርሽኙ መጠቃታቸውን አክሏል፡፡

በኮሌራ ወረርሽኙ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው በደቡብ ክልል የደቡብ ኦሞና የጎፋ ዞኖች መሆናቸውን፣ 970 ያህል ሰዎች ሲጠቁ 12 ያህሉ ሕይወታቸው ማለፉ ተመልክቷል፡፡

በሶማሌ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች በወረርሽኑ የተጠቁት ሰዎች ቁጥር 75 መሆኑንና በሕክምና ተቋማት መታወቁን፣ እስካለፈው ሳምንትም ስድስት ሰዎች መሞታቸው በመግለጫው ተካቷል፡፡

በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን በአዶላ ረዴና በኦዶ ሻኪሶ ወረዳዎች በአሥር ቀበሌዎች ውስጥ 100 ያህል ሰዎች መጠቃታቸውና ሰባት ሰዎች መሞታቸውን ቢሮው አስታውቋል፡፡

ከዓለም አቀፍ አጋሮች ጋር በመተባበር በክልሎችና በታችኛው እርከን የመንግሥት መዋቅሮች፣ የአስቸኳይ ጊዜ ግብረ ኃይሎች ተቋቁመው ለወረርሽኙ አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት ቡድኖች መሰማራታቸው ተገልጿል፡፡ ለዚህም የምላሽ ጥረት የጤና አገልግሎት ሰጪ ተቋማትም ክፍተት እንዲሞሉ እየተደረገ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

ተመድ እንደሚለው የኮሌራ ወረርሽኝ በኢትዮጵያ ለሕዝብ ጤና ከፍተኛ ሥጋት ነው፡፡ ዝቅተኛ የኑሮ ሁኔታ፣ በቂ የውኃና የሳኒቴሽን አገልግሎቶች አለመኖርና ደካማ የጤና አጠባበቅና የግል ንፅህና አያያዝ ምክንያት መሆናቸውን አክሏል፡፡

ባለፈው ዓመት ከጋምቤላና ከቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልሎች በስተቀር፣ በመላ አገሪቱ 2,074 ሰዎች በኮሌራ ወረርሽኝ ተይዘው የተወሰኑ መሞታቸው አይዘነጋም፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

አያሌ የውኃ “ጠርሙሶች”ን በጫንቃ

መሰንበቻውን በአይቮሪ ኮስት መዲና አቢጃን የምትኖር አንዲት ሴት፣ በሚደንቅ...

ወልቃይትን ማዕከል ያደረገው የምዕራባዊያን ጫና

በትግራይ ክልል የተከሰተው የዕርዳታ እህል ዘረፋ የዓለም አቀፍ ተቋማት...

ከቀጣዩ ዓመት በጀት ውስጥ 281 ቢሊዮን ብሩ የበጀት ጉደለት ነው ተባለ

ለቀጣዩ በጀት ዓመት ከቀረበው 801.65 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ በጀት...