Tuesday, July 16, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትበለንደን ማራቶን የሚጠበቀው የቀነኒሳ በቀለና የኤሊዩድ ኪፕቾጌ ፍጥጫ

በለንደን ማራቶን የሚጠበቀው የቀነኒሳ በቀለና የኤሊዩድ ኪፕቾጌ ፍጥጫ

ቀን:

ለሽልማት 313,000 ዶላር ተዘጋጅቷል

ወርልድ አትሌቲክስ በወርቅ ደረጃ ዕውቅና ከሚሰጣቸው አምስት የጎዳና ውድድሮች አንዱ እንደሆነ የሚነገርለት ለንደን ማራቶን ከሁለት ወር በኋላ እንደሚካሄድ ይጠበቃል፡፡ ባለፈው ሳምንት የለንደን ማራቶን አዘጋጆች የውድድሩን መካሄድ አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ፣ በማራቶን የዓለም ክብረ ወሰን ባለቤቱ ኬንያዊው ኤሊዩድ ኪፕቾጌና ጠንካራ ተፎካካሪው ይሆናል ተብሎ የሚጠበቀው ቀነኒሳ በቀለ ይሳተፋሉ፡፡ 313,000 ዶላር ለሽልማት መዘጋጀቱም ተነግሯል፡፡

ለቶኪዮ ኦሊምፒክ ተሳትፎ የሚያበቃ ሰዓት (ሚኒማ) ማሟያ ጭምር ከፍተኛ ግምት የሚሰጠው ለንደን ማራቶን፣ ከሁለቱ ታላላቅ አትሌቶች በተጨማሪ በማራቶን ምርጥና ፈጣን ሰዓት ያላቸው አትሌቶች ከሁሉም ክፍለ ዓለማት የሚሳተፉበት ሲሆን፣ በሁለቱም ፆታ አሸናፊዎች 150,000፣ ሁለተኛና ሦስተኛ የሚወጡት 75,000 እና 40,000 ዶላር ተሸላሚ ይሆናሉ፡፡

ከ40,000 በላይ ተሳታፊዎች ይካፈሉበታል ተብሎ በሚጠበቀው ለንደን ማራቶን ከሁለቱ ታላላቅ አትሌቶች በተጨማሪ በርቀቱ ፈጣንና ምርጥ ሰዓት ያላቸው አትሌቶች አሸናፊ በመሆን ከሚያገኙት ሽልማት በተጨማሪ በውድድሩ በመሳተፋቸው ብቻ ክፍያ የሚከፈላቸው ስለመሆኑም ጭምር ተነግሯል፡፡

ከሚጠበቁት አትሌቶች መካከል በማራቶን የዓለም ክብረ ወሰን ባለቤቱ ኬንያዊው ኤሊዩድ ኪፕቾጌ (2፡ 01፡ 39)፣ ቀነኒሳ በቀለ (2፡ 01፡ 41)፣ ሙስነት ገረመው (2፡ 02፡ 55) ሙሌ ዋሲሁን (2፡ 03፡ 10) እና በሕመም ምክንያት ከውድድር ርቆ የቆየው ታምራት ቶላ (2፡ 04፡ 06) የአሸናፊነት ቅድመ ግምት የተሰጣቸው ናቸው፡፡

ከሴቶች በማራቶን ክብረ ወሰኑ በዚሁ ለንደን ማራቶን ለረዥም ዓመታት ማለትም ከ2003 እስከ 2019 ድረስ በእንግሊዛዊቷ ፓውላ ራድክሊፍ ተይዞ የቆየውን 2፡ 15፡ 25 በ2019 በችካጎ ማራቶን ኬንያዊቷ ብሪግድ ኮስጌይ 2፡ 14፡ 04 አዲስ የዓለም ክብረ ወሰን ተመዝግቧል፡፡ በዘንድሮው ውድድር ክብሯን ታስጠብቃለች ተብሎም ይጠበቃል፡፡

በለንደን ማራቶን የአትሌቷ የቅርብ ተፎካካሪ ይሆናሉ ተብለው ከሚጠበቁት አትሌቶች መካከል፣ የአገሯ ልጆች ሩት ቸፕንጌቲች (2፡ 17፡ 08) እና ግላዲስ ቼሮኖ (2፡ 18፡ 11) ይጠበቃሉ፡፡ ከኬንያውያኑ ባልተናነሰ ለብሪግድ ኮስጌይ ጠንካራ ተፎካካሪ እንደሚሆኑ ቅድመ ግምት የተሰጣቸው ኢትዮጵያውያኑ ሮዛ ደረጀ (2፡ 18፡ 30) ደጊቱ አዝመራው (2፡ 19፡ 25)፣ እሸቴ በከሪ (2፡ 20፡ 14) እና ዓለም መጋርቱ (2፡ 21፡ 10)  መሆናቸው ታውቋል፡፡ 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሚዲያው በሕዝብ የህሊና ችሎት ከተዳኘ በቂ ነው!

መሰንበቻውን ድንገት ሳይታሰብ ያለ ማስጠንቀቂያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ...

የባህር በር ጉዳይ

በታምሩ ወንድም አገኘሁ ድሮ ድሮ ገና ልጅ ሆኜ ፊደል እንደቆጠርኩ...

አገሩ ፖለቲካዊ ስክነትና መደማማጥ ያስፈልገዋል

በንጉሥ ወዳጀነው    ኢትዮጵያ የሁላችንም የጋራ ቤት ነች፡፡ ‹‹ጥያቄዬ ተመለሰልኝ››፣...

የመንግሥት የሰብዓዊ መብት ተቋም ለምን የመንግሥት ሚዲያን ማስተማር አቃተው

በገነት ዓለሙ የአገራችን የ2016 የበጀት ዓመት መሰናበቻና የአዲሱ የ2017 በጀት...