ኦክስፋም ኢንተርናሽናል በዳቮስ በመካሄድ ላይ ላለው የዓለም ኢኮኖሚ ፎረም ካቀረበው ሪፖርት የተወሰደ፡፡ ኦክስፋም በሪፖርቱ እንዳመለከተው ይህ ከፍተኛ ትኩረት የሚያስፈልገው ጉዳይ ቀውስ ይፈጥራል፡፡ የዓለም መንግሥታት ሴቶችን ማዕከል ያደረገ ሰብዓዊ ኢኮኖሚ መፍጠር እንደሚችሉ አስታውቆ፣ በሠርቶ አዳሪዎችና በባለፀጎች መካከል ያለው የሀብት ልዩነት መጥበብ አለበት ብሏል፡፡ ይህም አንድ በመቶዎችን ብቻ ሳይሆን 99 በመቶ የሚሆኑትን ተጠቃሚ ያደርጋል ሲልም አክሏል፡፡ ለዚህም ስድስት ምክረ ሐሳቦችን አቅርቧል፡፡ አንድ በመቶ የዓለም ባለፀጎች ቁጥራቸው 2,153 ቢሊየነሮች መሆናቸውን አስታውቋል፡፡