ከአዲስ አበባ 560 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ጊዶሌ ከተማ ሁለተኛው የባህልና ፊላ ፌስቲቫል ከጥር 9 እስከ ጥር 15 ቀን 2012 ዓ.ም. ተካሂዷል፡፡ ቀድሞ በጋርዱላ አውራጃነት በሚታወቀው አካባቢ ካሉት ብሔረሰቦች ዲራሼ፣ ማሾሌ፣ ሞሶዬ፣ ኩስሜ ፊላ የሚባለው ታዋቂው የትንፋሽ መሣሪያ የክብረ በዓሉ ድምቀት ነበር፡፡ ባህላዊ ምግቦችና መጠጦችም የፌስቲቫሉ አካል ነበሩ፡፡ ፎቶዎቹ የፌስቲቫሉን ከፊል ገጽታ ያሳያሉ፡፡