Thursday, November 30, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትዋሊያዎቹና የዓለም ዋንጫ የምድብ ድልድል

ዋሊያዎቹና የዓለም ዋንጫ የምድብ ድልድል

ቀን:

የዓለም አቀፍ እግር ኳስ ማኅበር (ፊፋ) እ.ኤ.አ. በ2022 ኳታር ለምታዘጋጀው የዓለም ዋንጫ የተሳታፊ አገሮች ምድብ ድልድልን ይፋ ጥር 11 ቀን 2012 ዓ.ም. አድርጓል፡፡ ኢትዮጵያ ከምዕራብ አፍሪካዊቷ ጠንካራ የእግር ኳስ አገር ጋና፣ ደቡብ አፍሪካና ዚምባቡዌ በሚገኙበት ምድብ መደልደሏ ታውቋል፡፡

ፊፋ በዚሁ ሳምንት ይፋ ባደረገው የየአገራቱ ብሔራዊ ቡድኖች ወርኃዊ የእግር ኳስ ደረጃ ኢትዮጵያን 146ኛ ላይ ማስቀመጡ ይታወሳል፡፡ ከዚህ በመነሳት ብሔራዊ ቡድኑ ጠንካራ ዝግጅት ማድረግ እንደሚጠበቅበት የሚናገሩ ሙያተኞች፣ በተለይ ፊፋ በዓመታዊ ውድድሮች በሚያካትታቸው የወዳጅነት ጨዋታዎች ፕሮግራም ውስጥ መግባት የሚስችል ዕቅድ ይዞ መንቀሳቀስ ግድ እንደሚል ይመክራሉ፡፡

ካሜሮን ለምታስተናግደው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያውን እያደረገ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን፣ እስካሁን ካደረጋቸው ጨዋታዎች አንድ ተሸንፎ አንድ አሸንፎ በተለይ በአፍሪካ በጠንካራነቷ የምትታወቀውን አይቮሪኮስትን በሜዳው ማሸነፉን ተከትሎ የፈጠረለት መነሳሳት ለቀሪዎቹ ጨዋታዎች ትልቅ የሞራል ስንቅ ሆኖለታል፡፡

የዓለም ዋንጫ ምድብ ድልድል ይፋ ከሆነ በኋላ ለተለያየ መገናኛ ብዙኃን አስተያየታቸውን ሲሰጡ የተደመጡት ኢንስትራክተር አብርሃም መብርሃቱ፣ ከምድቡ በመነሳት ኢትዮጵያ ጠንካራ ሥራ እንደሚጠብቃት የሚያመላክት መሆኑን ነው የተናገሩት፡፡

የኢትዮጵያን እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጨምሮ ሁሉም ባለድርሻ አካል ለብሔራዊ ቡድኑ ዝግጅት አስፈላጊውን ሙያዊ ዕገዛ ሊያደርጉ እንደሚገባም ከወዲሁ እየተነገረ ይገኛል፡፡ የቡድኑ ዋና አሠልጣኝ ኢንስትራክተር አብርሃም ዋሊያዎቹ ከወራት በፊት በአፍሪካ በጥንካሬዋ በግንባር ቀደምትነት በምትጠቀሰው የአይቮሪኮስት ብሔራዊ ቡድን ላይ ለወሰደው ብልጫ የባለድርሻ ትብብር ውጤት እንደሆነ መናገራቸው ይታወሳል፡፡ 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመቃወም ነፃነት ውዝግብ በኢትዮጵያ

ስሟ እንዳይገለጽ የጠየቀችው በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ የሾላ አካባቢ...

የሲሚንቶን እጥረትና ችግር ታሪክ ለማድረግ የተጀመረው አጓጊ ጥረት

በኢትዮጵያ በገበያ ውስጥ ለዓመታት ከፍተኛ ተግዳሮት በመሆን ከሚጠቀሱ ምርቶች...

የብሔር ፖለቲካው ጡዘት የእርስ በርስ ግጭት እንዳያባብስ ጥንቃቄ ይደረግ

በያሲን ባህሩ በሪፖርተር የኅዳር 9 ቀን 2016 ዓ.ም. ዕትም “እኔ...