Friday, July 19, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየህዳሴ ግድብ የውኃ አሞላልና አለቃቀን ወደ ሕግ ማዕቀፍነት ለመቀየር የተጀመረው ውይይት በአሜሪካ...

የህዳሴ ግድብ የውኃ አሞላልና አለቃቀን ወደ ሕግ ማዕቀፍነት ለመቀየር የተጀመረው ውይይት በአሜሪካ እየተካሄደ ነው

ቀን:

ኢትዮጵያ፣ ግብፅና ሱዳን በታላቁ የህዳሴ ግድብ ውኃ አሞላልና አለቃቀቅ ላይ የተስማሙባቸውን ጉዳዮች ወደ ሕግ ማዕቀፍነት ለመቀየር የጀመሩትን ውይይት ከሰኞ ጥር 18  ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ በአሜሪካ ቀጥለዋል።

ሦስቱ አገሮች በጥር ወር መጀመርያ ላይ በአሜሪካ ባደረጉት የሦስት ቀናት ውይይት በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የውኃ አሞላልና አለቃቅ ላይ የነበሯቸውን መሠረታዊ ልዩነቶች የፈቱ ሲሆን፣ ይህንንም ተከትሎ ስምምነት የደረሱባቸውን ጉዳዮች ወደ ሕግ ማዕቀፍነት የመቀየር ተግባር ውስጥ ገብተዋል።

በዚህ መሠረት የሕግ ማዕቀፍ ዝግጅታቸውን ባለፈው ሳምንት ማጠናቀቅ የሚጠበቅባቸው ቢሆንም፣ በሱዳን ባደረጉት ውይይት ዳግም በመካከላቸው በተፈጠረ ልዩነት የሕግ ማርቀቅ ሒደቱን ማጠናቀቅ አልቻሉም ነበር።

 በመሆኑም ልዩነቶቻቸውን ይዘው በዚህ ሳምንት መጀመርያ ላይ በአሜሪካ ዳግም የተገናኙ ሲሆን፣ በአሜሪካ የገንዘብ ተቋም ኃላፊ አወያይነት ውይይት በማድረግ ላይ ናቸው።

ሦስቱ አገሮች በዋናነት የተወከሉት በውጭ ጉዳይና በውኃ ጉዳይ ሚኒስትሮቻቸው ሲሆን፣ በዚህም መሠረት የኢትዮጵያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸውና የውኃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ስለሺ በቀለ (ዶ/ር) በዚህ ስብሰባ ላይ ከሕግና ከቴክኒክ ባለሙያዎቻቸው ጋር በዋሽንግተን ዲሲ፣ ከግብፅና ከሱዳን አቻዎቻቸው ጋር በመምከር ላይ ይገኛሉ።

በዚህ ውይይት ትኩረት የሚደረግባቸውን ጉዳዮች በተመለከተ ሚኒስትር ስለሺ (ዶ/ር) በትዊተር ገጻቸው ላይ ባጋሩት አጠር ያለ መረጃ መሠረት፣ በቴክኒክ ውይይት ወቅት ስምምነት የተደረሰባቸውን ጉዳዮች ወደ ሕግ ማዕቀፍነት መቀየር በዚህ ውይይትም ትኩረት ይደረግበታል።

ሲካሄዱ በቆዩት በርካታ የቴክኒክ ውይይቶች የስምምነት ውጤት የተገኘባቸው ጉዳዮች የውኃ አሞላል መርሆች፣ የሙሌት ምዕራፎች፣ በግድቡ የሚያዘው የውኃ መጠን፣ የግድቡ የውኃ አለቃቀቅ ሥርዓት፣ የድርቅ ወቅት የአስተዳደር ሁኔታዎችና የመረጃ ማጋራት ጉዳዮችን የተመለከቱ መሆናቸውን ሚኒስትሩ አስረድተዋል።

ሦስቱ አገሮች በታኅሳስ ወር መጀመርያ ላይ በአሜሪካ ባደረጉት ውይይት ከደረሱባቸው ስምምነቶች መካከል ወደ ግድቡ የሚመጣው የውኃ መጠን ምን ያህል ሲሆን፣ የድርቅ ወቅት ሁኔታን ጠቋሚ ነው? እንዲሁም የከፋ የድርቅ ወቅት ጠቋሚ ነው የሚባለው ምን ያህል የውኃ መጠን ወደ ግድቡ ሲመጣ ነው? የሚሉት ጉዳዮች እንደሚገኙበት መዘገባችን ይታወሳል።

በዚህም መሠረት ወደ ግድቡ የሚመጣው የውኃ መጠን 37 ቢሊዮን ሜትሪክ ኪዩብ ከሆነ የድርቅ ወቅት ሁኔታን የሚያመላክት (ድራውት ትረሾልድ) እንደሆነ የተስማሙ ሲሆን፣ ወደ ግድቡ የሚመጣው የውኃ መጠን ከዚህ በታች ከሆነ ኢትዮጵያ በሁለተኛና ዋናው የውኃ ሙሌት ምዕራፍ ወቅት ይኼንን የውኃ መጠን በግድቡ ሳትይዝ ኃይል አመንጭታ ሙሉ በመሉ እንዲለቀቅ ተስማምተዋል።

በመጀመሪያው ዙር ማለትም ከባህር ወለል እስከ 595 ሜትር የግድቡ ከፍታ ድረስ በሚካሄደው የውኃ ሙሌት ወቅት ወደ ግድቡ የሚደርሰው የውኃ መጠን 31 ቢሊዮን ሜትር ኪዩብና ከዚያ በታች በሚሆንበት ጊዜ ደግሞ፣ ሙሌቱ እንዳይካሄድ መስማማታቸውን መዘገባችን አይዘነጋም

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

አቶ ሰብስብ አባፊራ የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ

ከአዋጅና መመሪያ ውጪ ለዓመታት ሳይካሄድ የቆየው የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ...

ቀጣናዊ ገጽታ የያዘው የኢትዮ ሶማሊያ ውዝግብ

ከአሥር ቀናት ቀደም ብሎ በተካሄደው የፓርላማ 36ኛ መደበኛ ስብሰባ፣...

የኢንሹራንስ ኩባንያዎች በዓረቦንና የጉዳት ካሳ ክፍያዎች ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ መጣሉን ተቃወሙ

በአዲሱ ተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ውስጥ የኢንሹራንስ ከባንያዎች ለሚሰበስቡት...