Tuesday, February 27, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትቅዱስ ጊዮርጊስና ኢትዮጵያ ቡና ከባለቤትነት ሰነድ ማረጋገጫ ባለፈ ድጋፍ ይደረግላቸዋል

ቅዱስ ጊዮርጊስና ኢትዮጵያ ቡና ከባለቤትነት ሰነድ ማረጋገጫ ባለፈ ድጋፍ ይደረግላቸዋል

ቀን:

በኢትዮጵያ እግር ኳስም ሆነ በሌሎች ስፖርቶች የመንግሥት በጀትና ድጎማ ካላገኙ የማይላወሱ፣ በጀት ያቆመ ጊዜ የሚፈርሱ ክለቦች ለመኖራቸው በርካታ ማሳያዎችን መመልከት ይቻላል፡፡ በመንግሥት ድጎማና ፋይናንስ እየተንቀሳቀሱም ተገቢውን ውጤት ማምጣት ቀርቶ ተፎካካሪነታቸውን እንኳ አስጠብቀው መቆየት የተሳናቸው በርካታ ናቸው፡፡

በአንጻሩ ከደጋፊዎቻቸውና በሌሎችም የተለያዩ አማራጮች በሚያሰባስቡት መዋጮ ውጤታማ መሆን የቻሉ ሁለት ክለቦች በአርአያነት ይጠቀሳሉ፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስና ኢትዮጵያ ቡና ከተመሠረተ ከሁለት አሠርታት በላይ ዕድሜ ባለው በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ያላቸውን ተሳትፎና ውጤት መጥቀስ ይቻላል፡፡

በራሳቸው በጀት እንደሚንቀሳቀሱ የሚነገርላቸው ሁለቱ ክለቦች የየራሳቸውን ስታዲየም መገንባት ይችሉ ዘንድ ከአዲስ አበባ ከተማ የመሬት አስተዳደር መሬት ቢረከቡም ግንባታውን እስካሁን አልጀመሩም፡፡ በተለይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሲኤምሲ አካባቢ መሬቱን ከተረከበ ዓመታትን አስቆጥሯል፡፡ ስፖርት ማኅበሩ ከወራት በፊት ይፋ ባደረገው መግለጫው፣ ክለቡን በአክሲዮን ማደራጀት የሚያስችል ቅድመ ሁኔታ ተጠናቋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከሰሞኑ እንዳስታወቀው ሁለቱ ክለቦች ቀደም ሲል በተረከቡት ቦታ ለሚያደርጓቸው አንዳንድ ቅድመ ሁኔታዎች አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግላቸው፣ በዋናነትም ከባለቤትነት ማረጋገጫ ደብተር በተጨማሪም የወጣት ማዕከልና ለዚያ አገልግሎት የሚውሉ ቢሮ መሰል ድጋፎችን እንደሚያደርግላቸው ቃል ገብቶላቸዋል፡፡

የአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሸነር አቶ ዮናስ አረጋይ ለሁለቱ ክለቦች ሊደረግላቸው የታሰበውን እገዛ አስመልክቶ ለተለያዩ መገናኛ ብዙኃን እንደተናገሩት፣ ቅዱስ ጊዮርጊስና ኢትዮጵያ ቡና የከተማዋ ብቸኛ ተወካይ መሆናቸው ብቻ ሳይሆን፣ የክለቦቹ መዋቅራዊ ተክለ ሰውነት ከመንግሥት የበጀት ድጎማ ነፃ ናቸው፡፡ አገር አቀፉ የስፖርት ፖሊሲም ይህ ዓይነት አካሄድና አደረጃጀት እንዲኖር ያበረታታል፣ አስፈላጊው ድጋፍም ያደርጋል፡፡ ‹‹በኢትዮጵያ ባለው ነባራዊ ሁኔታ ከቅዱስ ጊዮርጊስና ኢትዮጵያ ቡና ውጪ የአገሪቱ ክለቦች በአጠቃላይ የሚንቀሳቀሱት ከመንግሥት በሚበጀትላቸው ፋይናንስ ነው፤›› ያሉት ኮሚሽነሩ፣ ፖሊሲው ግን የእግር ኳስ ክለቦችን ጨምሮ የስፖርት ማኅበራት ከመንግሥት በጀት እየተላቀቁ በሒደት ራሳቸውን በራሳቸው ማስተዳደር መቻል እንደሚኖርባቸው አሳስበዋል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ የከተማ አስተዳደሩ ስፖርት ኮሚሽን ተጠሪነት ከአገር አቀፉ ለየት ባለ መልኩ እንዲዋቀር ስለመደረጉ ጭምር አቶ ዮናስ ተናግረዋል፡፡ ተጠሪነቱ ለከተማ አስተዳደሩ እንዲሆን ተደርጓል ብለዋል፣ አገር አቀፉን ስንመለከት ግን ተጠሪነቱ ለባህልና ቱሪዝም መሆኑ ልብ ይሏል፡፡

የሁለቱ ክለቦች የቆየው የባላንጣነት (ደርቢ) ስሜትም አሁን አሁን የማዘውተሪያዎች የቀን ተቀን መግለጫ ከሆነው አጉራ ዘለል የአደጋገፍ ሥርዓት በተለየ መልኩ በአርአያነት የሚጠቀስ ሆኗል፡፡ ሁለቱ ክለቦች ባለፈው ረቡዕ ጥር 20 ቀን 2012 ዓ.ም. በተመልካቾች ዘንድ በጉጉት ሲጠበቅ የሰነበተውን የፕሪሚየር ሊጉን 11ኛ ሳምንት ጨዋታ በአዲስ አበባ ስታዲየም አድርገዋል፡፡ ጨዋታው በቅዱስ ጊዮርጊስ 1 ለ 0 አሸናፊነት የተጠናቀቀ መሆኑ ይታወሳል፡፡

በዕለቱ በአዲስ አበባ ስታዲየም የሁለቱን ቡድኖች ጨዋታ የተከታተሉት የአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽነር አቶ ዮናስ ከጨዋታው በፊት ለሁለቱ ክለብ አመራሮች ዕውቅና ሰጥተዋል፡፡

በአርአያነቱ የሚጠቀሰው “ሸገር ደርቢ”

ባለፉት ዓመታት የኢትዮጵያን ፕሪሚየር ሊግ ጨምሮ በየደረጃው የሚገኙ ቡድኖች የሚያደርጓቸው ጨዋታዎች በሰላም ተጀምረው በረብሻና በብጥብጥ የሚጠናቀቁበት አጋጣሚ የበዛ ነበር፡፡ ይህ ክስተት ቅዱስ ጊዮረጊስና ኢትዮጵያ ቡናን ጨምሮ የሁሉም ቡድኖች መለያ ሆኖ መቆየቱ የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው፡፡

የዘንድሮ ውድድር ከመጀመሩ በፊት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከክልል ከፍተኛ ኃላፊዎችና ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር የነበረውን ችግር ለመፍታት ያደረገው ጥረት እንደተጠበቀ ዘንድሮ በአንዳንድ የክልል ከተሞች ከሚስተዋሉ የስፖርታዊ ጨዋነት መጓደሎች ውጪ በአብዛኛው ሰላማዊ የእግር ኳስ እንቅስቃሴዎች መታየት ጀምረዋል፡፡

የሸገሮቹ ቅዱስ ጊዮርጊስና ኢትዮጵያ ቡና በሜዳቸው ማናቸውንም ኃላፊነት እንደሚወስዱ፣ ሌሎች ክልሎችም በተመሳሳይ መውሰድ እንደሚጠበቅባቸው ከመነሻው የወሰዱት ቁርጠኝነት ለዚህ ትልቁን ድርሻ መያዙ የሚጠቀስ ነው፡፡ ይሁንና ከሰሞኑ በአንዳንድ ክልሎች የሚታዩ የስፖርታዊ ጨዋነት መጓደል ክስተቶች ከወዲሁ አፋጣኝ መፍትሔ የሚሹ መሆናቸው እየተነገረ ይገኛል፡፡ በ10ኛው ሳምንት አዳማ ከተማ ላይ በአዳማ ከተማና በሀድያ ሆሳዕና እንዲሁም በ11ኛው ሳምንት በሀድያ ሆሳዕናና በወልቂጤ ከተማ ቡድኖች መካከል የታዩት ግጭቶች ተጠቃሽ ናቸው፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...