Friday, June 21, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊ​​​​​​​የእግረኛ መንገድ ወይስ መነገጃ

​​​​​​​የእግረኛ መንገድ ወይስ መነገጃ

ቀን:

በታደሰ ገብረማርያም

አዲስ አበባ ውስጥ ከዋናው አስፋልት ጎዳናዎች ጋር ተያይዘው የተሠሩ የእግረኛ መንገዶች አሉ፡፡ በጣም ጥቂቶቹ ደረጃውን በጠበቀ ሸክላ የተነጠፉ ስለሆነ ለአካባቢው ግርማ ሞገስን አላብሰዋል፡፡ አብዛኞቹ ለማስፋፋት በማይችል መልኩ በጣም ጠባብ ናቸው፡፡ አልፎ አልፎ ለጥላና ለውበት ሲባል የተተከሉትን ዛፎች ደኅንነት ለመጠበቅ ሲባል በብረትና በቆርቆሮ እንዲታጠሩ መደረጉ የጥበቱን መጠን አባብሶታል፡፡

የእግረኛው ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ ደግሞ እግረኛው መተላለፊያ እስከማጣት ድረስ ተጨናንቋል፡፡ የሸቀጣ ሸቀጥ መቸርቸሪያና የልባሽ መነገጃ ሆኖ መዋሉ ደግሞ ለጭንቅንቁ መባባስ አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡ በተለይ መንገዱ በአሁኑ ጊዜ የጀበና ቡና የሚጠጣበት፣ ከግሮሰሪ ጋር ከተያያዙ ልኳንዳ ቤቶች ቁርጥ እየተገዛ የሚበላበትና የተለያዩ የአልኮል መጠጦች የሚጎነጭባቸው ከሆነም ሰነባብቷል፡፡

ለእግረኛ ተብሎ የተሠራው መንገድ መኪና ማቆሚያ መሆኑም በገሃድ እያየን ነው፡፡ ጎሚስታዎች የሚሠሩበት፣ የቆርቆሮ አሸንዳ የሚዘጋጅበት ከሆነም ቆይቷል፡፡ በተለይ በአቡነ ጴጥሮስ አደባባይ፣ በአትክልት ተራና በአሮጌው ፖስታ ቤት ዙሪያ ያሉት የእግረኛ መንገዶች በሽንኩርት ገለባና በሙዝ ልጣጭ እንደቄጠማ ተጎዝጉዞባቸው ማየቱ አዲስ ነገር አይደለም፡፡

በዚህ መልኩ ከተተበተበው የእግረኛ መንገድ ሰዉ መተላለፊያ ፍለጋ ወደ ዋናው አስፋልት ገብቶ መንቀሳቀስን መርጧል፡፡ ይህ ዓይነቱም እንቅስቃሴ ለአስከፊው የትራፊክ አደጋ ይዳርጋል የሚል ሥጋት አሳድሯል፡፡ ይህንንም ሥጋት የአዲስ አበባ ትራፊክ ፖሊስ የትራፊክ ደንብ ቁጥጥር መምርያ ኃላፊ ኮማንደር ሸዋይርጋ ግዛው ይጋሩታል፡፡ እንደ መምርያው ኃላፊ ሥጋት በእግረኛ መንገዶች ላይ የሚታየውን ግዴለሽነትና ዝርክርክነት ከወዲሁ ካልተገታና ሥርዓት የማስያዙ ሥራ ካልተከናወነ በስተቀር ወደኋላ መልሶ ለማቃናት አስቸጋሪ ይሆናል፡፡

‹‹ችግሩ የሚታየው በእግረኛው ጎዳና ላይ ብቻ አይደለም›› ያሉት ኮማንደር ሸዋይርጋ፣ በየሳምንቱ እሑድ አንዳንድ በተመረጡ አስፋልት መንገዶች ላይ ሸቀጣቸውን ዘርግተው እንዲነግዱ በተፈቀደው የሰንበት ገበያ (ሰንደይ ማርኬት) ውስጥ ነጋዴዎቹ ከተፈቀደባቸው ውጪ የእግረኛውን መንገድ እያጠሩ ሲቸረችሩ እንደሚስተዋሉ አስረድተዋል፡፡

ይህ ዓይነቱ ሥርዓት ያጣን እንቅስቃሴ መግታት የሚቻለው ሁሉም የተሰጠውን የሥራ ድርሻ በቅንጅት በአግባቡ ሲሠራ ነው፡፡ ከዚህ አኳያ የመምርያው የሥራ ድርሻ በአደባባዮች፤ በመስቀለኛና ማቋረጫ መንገዶች ላይ ያለውን የትራፊክ ፍሰት ማስተባበር ሲሆን በተረፈ የጎዳና ንግድን ሥርዓት ማስያዝ በአስተዳደር የሚታይ ጉዳይ ነው የሚል እምነት እንዳላቸው ነው የተናገሩት፡፡

የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ጥዑማይ ወልደ ገብርኤል ስለዚህ ጉዳይ በስልክ ተጠይቀው ‹‹በየሳምንቱ አልፎ አልፎ በዘመቻ እንቆጣጠራለን፤›› ብለዋል፡፡ የዘመቻው ውጤት ምንድነው ለተባለው ጥያቄ ሳይመልሱ ቀርተዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅና የሚስተጋቡ ሥጋቶች

ከሰሞኑ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የንብረት ማስመለስ ረቂቅ...

የመጨረሻ የተባለው የንግድ ምክር ቤቱ ምርጫና የሚኒስቴሩ ውሳኔ

በአገር አቀፍ ደረጃ ደረጃ የንግድ ኅብረተሰቡን በመወከል የሚጠቀሰው የኢትዮጵያ...

ሚስጥሩ!

ጉዞ ከካዛንቺስ ወደ ስድስት ኪሎ፡፡ የጥንቶቹ አራዶች መናኸሪያ ወዘናዋ...