Wednesday, February 1, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊ​​​​​​​ለይቶ ማቆያ ማዕከል እንዲገቡ የተወሰነባቸው ከቻይና የሚመጡ መንገደኞች

​​​​​​​ለይቶ ማቆያ ማዕከል እንዲገቡ የተወሰነባቸው ከቻይና የሚመጡ መንገደኞች

ቀን:

ከቻይና ውሃን ከተማ የሚመጡ ማናቸውም መንገደኞች ለይቶ ማቆያ ማዕከል ውስጥ ገብተው አስፈላጊው የሕክምና ክትትል የሚደረግላቸው መሆኑን የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታውቋል፡፡

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ኤባ አባተ (ዶ/ር) ጥር 29 ቀን 2012 ዓ.ም. እንደገለጹት፣ በቦሌ ኤርፖርት ከቻይና የሚመጡ መንገደኞች ከሌላው መንገደኛ ጋር ሳይቀላቀሉ የሙቀት ምርመራ የሚደረግላቸው ሲሆን፣ በተጨማሪም ከቻይና ለሚመጡ መንገደኞች ብቻ አገልግሎት የሚሰጥ የኢሚግሬሽን ልዩ መስኮትም ተዘጋጅቷል።

ከቻይና የሚመጡ መንገደኞችን የጤና ሁኔታ መከታተል እንዲቻል ለባለሙያዎች ሥልጠና ተሰጥቶ አገልግሎቱም መጀመሩን የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ፣ አዲስ አበባ ውስጥ የኖቭል ኮሮና ቫይረስ ምልክቶች ታይቶባቸዋል ተብለው በጥርጣሬ ከተያዙት 29 ሰዎች መካከል በቫይረሱ የመያዝ ምልክት ያሳዩ 14 ሰዎች ወደ ማቆያ ሥፍራ እንዲገቡ ተደርገዋል ብለዋል፡፡

ወደ ማቆያ ሥፍራ ከገቡት መካከል የ11 ሰዎች ከቫይረሱ ነፃ መሆናቸውን የኢንስቲትዩቱ የድንገተኛ አደጋዎች ማዕከል አረጋግጧል፡፡ የሌሎች ሦስት ሰዎች ናሙና ደግሞ ወደ ደቡብ አፍሪካ ተልኮ የምርመራው ውጤት እየተጠበቀ ነው፡፡ በቀጣዩ ቀናትም የቀሩትን ሦስት ሰዎች ናሙናዎች ለምርመራ እንደሚላኩ ነው የተናገሩት፡፡

ከዚህም ሌላ ከቻይና የመጡና የበሽታው ምልክት የታየባቸው ሌሎች ስድስት ሰዎች ከጊዜያዊ ማቆያ እንዲገቡ መደረጉን ገልጸው ከእነዚህም መካከል አምስቱ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ሲሆኑ አንዱ ቻይናዊ ናቸው፡፡

ከኢትዮጵያውያኑም መካከል ሁለቱ ሴቶች የቀሩት ወንዶች መሆናቸውን ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸው የሁሉም ሰዎች ናሙናዎቻቸው ለምርመራ ወደ ደቡብ አፍሪካ መላኩን ከምርመራ የሚገኘውን ውጤት በመንተራስ ቀጣዩ ዕርምጃ የሚወሰድ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በዓለም የጤና ድርጅት ሪፖርት መሠረት፣ እስከ ጥር 28 ቀን 2012 ዓ.ም. ድረስ ያለው በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር፣ 30,852 ሲሆን፣ እስከ ዛሬ ጥር 29 ድረስ 635 ሰዎች በቫይረሱ ምክንያት ሕይወታቸው አልፏል፡፡

ኖቭል ኮሮና ቫይረስ ምንድን ነው?

    የኖቭል ኮሮና ቫይረስ (corona virus) ከቀላል እስከ ከባድ የመተንፈሻ አካል ሕመም የሚያስከትል የቫይረስ ዝርያ ሲሆን በበሽታው የተያዙ ሰዎች ትኩሳት፣ ሳል፣ የትንፋሽ መቆራረጥና የመተንፈስ ችግር ምልክቶች ይታይባቸዋል፡፡

በሽታው በጠናባቸው ታማሚዎች ላይ ደግሞ እንደ ሳንባ ምች (pneumonia) ከባድ የመተንፈሻ አካላት ሕመም የሚያሳይ ሲሆን የኩላሊት ማቆምና ሞትን ሊያስከትል የሚችል በሽታ ነው፡፡

 

 

መተላለፊያ መንገዶች

  • በሽታው በሳልና በማስነጠስ ወቅትና ከታማሚ ሰው ጋር በሚደረግ የቅርብ ንክኪ፣ ባልታጠበ እጅና በመሳሰሉት ይተላለፋል፡፡ በሽታውን ሪፖርት ወደ አደረጉገሮች የሚጓዙ መንገደኞች ሊያደረጓቸው የሚገቡ ጥንቃቄዎች፣
  • የትኩሳትና የሳል ምልክት ከሚያሳዩ ሰዎች ጋር ንክኪ አለማድረግ፣
  • እጅን በሳሙናና ውኃ መታጠብ በተለይ ደግሞ ከታመሙ ሰዎች ወይም ከአካባቢያቸው ጋር ንክኪ ካደረጉ፣
  • ያልበሰሉ የእንስሳት ተዋፅኦ የሆኑ ምግቦችን ከመመገብ መቆጠብ፣
  • ምክንያቱ ባልታወቀ በሽታ በታመሙም ሆነ ከሞቱ የቤትና የዱር እንስሳት ጋር ንክኪ አለማድረግ
  • ከኢትዮጵያ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት፣ ጤና ሚኒስቴር፣ ሕክምና ተቋማት፣ ከጉዞ ማኅበራት፣ ከአየር መንገድ፣ ከመዳረሻ ቦታዎች ወይም ከሌሎች የጤና መረጃ ምንጮች ስለ በሽታው በቂ መረጃ በማግኘት ራሳቸውን ከበሽታው መከላከል ይጠበቅባቸዋል፡፡ ለተጨማሪ መረጃ በነፃ የጥሪ መስመር 8335 በመደወል መረጃ ማስተላለፍና ማግኘት ይቻላል ወይም በመደበኛ ስልክ ቁጥር 011-8-33-24-94 መደወል ይቻላል፡፡

በበሽታው መያዛቸውን የጠረጠሩ ሰዎች ማድረግ ያለባቸው ጥንቃቄዎች

  • ወደ ሀገር በተመለሱ 14 ቀናት ጊዜ ውስጥ የመተንፈሻ አካልመም፣ ትኩሳትና እንደ ሳል ያሉ የሕመም ምልክቶች ካሳዩ፣ በተጨማሪ የበሽታው ስሜት ከመፈጠሩ አሥራ አራት ቀናት በፊት በሽታውን ሪፖርት ወዳደረጉ አገሮች ሄደው ከነበረ፣ በሽታውን ሪፖርት ወደ አደረጉ አገሮች ሄዶ የበሽታውን ምልከቶች ማሳየት የጀመረ ሰውን የሚያውቅ ማንኛውም ግለሰብ እንዲሁም የበሽታውን ምልክት ማሳየት የጀመረ ሰውን የሚያውቅ በአስቸኳይ 8335 ነጻ የስልክ መስመር በመደወል ሪፖርት ያድርጉ፡፡
  • በሚያስሉበትና በሚያስነጥሱበት ጊዜ በሽታው ወደ ጤነኛ ሰው እንዳይተላለፍ አፍና አፍንጫን በክንድ ወይም በሶፍት መሽፈን፣
  • አፍና አፍንጫን ለመሽፈን የተጠቀምንበትን ሶፍት በአግባቡ በቆሻሻ መጣያ ውስጥ ማስወገድና እጅን ሁልጊዜ በውኃና በሳሙና መታጠብ ያስፈልጋል፡፡

 

 

 

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ በወቅታዊ ፀጥታና ደህንነት ጉዳዮች ላይ የቀረበላቸውን ምክረ ሐሳብ እያደመጡ ነው]

ችግሩ ምን እንደሆነ በትክልል ለይተነዋል ግን ግን ምን? በይፋ መናገር አልነበረብንም። ለምን? ችግሩን...

የ12ኛ ክፍል የብሔራዊ ፈተና ውጤትና እንደምታው

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (UNESCO) የትምህርትን...

ንግድ ባንክ ከቪዛና ማስተር ካርድ ጋር ተደራድሮ ያስጀመረው የገንዘብ ማስተላለፊያ ቴክኖሎጂና ፋይዳው

ከውጭ ወደ አገር በሕጋዊ መንገድ የሚላክ ገንዘብ (ሬሚታንስ) መጠን...

ይኼ አመላችን የት ያደርሰን ይሆን?

እነሆ ከፒያሳ ወደ ካዛንቺስ። ‹‹አዳም ሆይ በግንባር ወዝ ትበላለህ››...