Monday, March 4, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

መንግሥት በድጎማ የሚያቀርበው የምግብ ዘይት የጥራት ደረጃ መሻሻሉን አስታወቀ

ተዛማጅ ፅሁፎች

መንግሥት በድጎማ ከውጭ እያስገባ ለኅብረተሰቡ ሲያሠራጨው የነበረው ፓልም የምግብ ዘይት የጥራት ደረጃ መሻሻሉን፣ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ፓልም የምግብ ዘይት መንግሥት የዋጋ፣ የአቅርቦትና የሥርጭት ቁጥጥር እያደረገባቸው በተመጣጣኝ ዋጋ ለኅብረተሰቡ ከሚቀርቡ መሠረታዊ የፍጆታ ሸቀጦች አንዱ መሆኑን፣ የሚኒስቴሩ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ባወጣው መግለጫ አስታውሷል፡፡

ፓልም ዘይት በውስጡ ካለው የስብ መጠንና ከአስመጪዎች መረጣ ፍትሐዊነት ጋር ተያይዞ ሲነሱ የነበሩ ቅሬታዎችና ውዝግቦችን ለመፍታት፣ ሚኒስቴሩ የምግብ ዘይት አቅርቦትና ሥርጭት ማስፈጸሚያ መመርያ አውጥቶ ተግባራዊ ማድረጉ አይዘነጋም፡፡

መመርያው ከታኅሳስ 2012 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ የተደረገ በመሆኑ ከዚህ በኋላ የሚቀርበው ዘይት በፊት ፓልም የምግብ ዘይት ወይም በተለምዶ የሚረጋው ዘይት ሳይሆን፣ ፓልም ኦሊን የተባለ ፈሳሽ የምግብ ዘይት እንደሆነ በመመርያው መሥፈሩን ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡

በፊት ይቀርብ የነበረው ፓልም የምግብ ዘይት የጥራት ደረጃ “CES138:2015” ተሻሽሎ አሁን የሚቀርበው ፓልም ኦሊን የምግብ ዘይት “CES245” የጥራት ደረጃ መሥፈርቶችን አሟልቶ መመረቱን፣ በቫይታሚን ኤ እና ዲ የበለፀገ መሆን እንዳለበትም መመርያው ያስገድዳል ሲል ሚኒስቴሩ አስረድቷል፡፡

ከጥራት ደረጃም በተጨማሪ የዘይት አስመጪዎች ምልመላ፣ የዋጋ ትመናና የትርፍ ህዳግ ምጣኔ አወሳሰንን የያዘ መሆኑንና አቅራቢዎችን ለመመልመል በወጣው መሥፈርት መሠረት፣ በክልሎችና በከተማ አስተዳደሮች ደረጃ በሚመለከታቸው የዘርፉ አካላት አማካይነት አሳታፊና ግልጽነት ባለው መንገድ 24 የምግብ ዘይት አስመጪዎች ተመርጠው ወደ ሥራ መግባታቸውን ከሚኒስቴሩ መግለጫ ለመረዳት ተችሏል፡፡

 የካፒታል መጠን፣ የአስመጪነት ልምድና ታማኝ የኢኮኖሚ አንቀሳቃሽነት የዘይት አቅራቢዎች መመልመያ መሥፈርቶች እንደሆኑ፣ ውድድሩን አሸንፎ ውል የገባ አስመጪ በገባው ውል መሠረት ሳይፈጽም ቢቀር ከምግብ ዘይት አስመጪነት እንደሚሰረዝም በመመርያው መደንገጉን አስታውቋል፡፡

ቅሬታውን ያቀረቡ በዘርፉ የተሰማሩ ባለሀብቶች ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ዘይት በአገር ውስጥ ለማምረትና ለማቀነባበር በድፍረት መዋዕለ ንዋያቸውን ቢያፈሱም የተፈቀደላቸው የመንግሥትና የግል ድርጅቶች ብቻ ገበያውን ሙሉ በሙሉ እየተቆጣጠሩ ነው፡፡ እነሱ ፋብሪካ ገንብተው ቢያንስ የአገሪቱን 15 በመቶ ገበያ ማግኘት ሲገባቸው፣ እነሱ ግን ጉዳት እየደረሰባቸው መሆኑን መናገራቸው ይታወሳል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች