Sunday, June 4, 2023
- Advertisment -
- Advertisment -

አጭር የኢትዮጵያ ማኅበራዊ ሥነ ልሳን

በታከለ ታደሰ (/ር፣ተባባሪ ፕሮፌሰር)

በአሁኑ ጊዜ የፖለቲካ ማዕበል ኢትዮጵያን በከፋ ሁኔታ እያመሳት ነው፡፡ ብዙ ሳንመራመር  ከእንግሊዝኛው ቀለል ያለ መዝገበ ቃላት ‹‹OXFORD ADVANCED LEARENER’S Dictionary (7th Edition)››  ፖለቲካ ምን ማለት እንደሆነ ማወቅ እንችላለን፡፡ ይኸው መዝገበ ቃል ከሚገልጸው ከአራቱ ነገረ ነገራት ውስጥ አንደኛውን እንዲህ ሲል ያብራራዋል፡፡በማኅበረ ሰባዊ ኑሮ ውስጥ ሥልጣንን ለማግኘትና ለመጠቀም በመቻል በሚደረጉ ተግባራት የአንድን አገር ወይንም ማኅበረ ሰብ የወደፊት ሕይወትና ኑሮ ለመወሰንና ተፅዕኖ ለማድረግ ነው’ ይላል፡፡

 (እዚህ ላይ ነገረ ነገራት ድምፀ ነገራት ከሚለው ቃል ጋር የተጣመረ ነው፡፡ ሁለቱም ቃላት እኔ የሦተኛ ሪዬን በምሠራበት ጊዜ በጥቅም ላይ እንዲውሉ ያደረኳቸው አዳዲስ ቃላት ናቸው፡፡ ድምፀ ነገር የሚያመለክተው የተሰጠውን ነገር በውስጡ ይዞ በነገሩ ዙሪያም ያለውንም ሳብ  ሰውሮመያዝ የሚችለውን በአፍ የሚነገር ድምፅን ነው፡፡ ስለዚህ ነገረ ነገር ድምፀ ነገር ከሚለው ቃል ጋር የተጣመረ ስለሆነ በድምፀ ነገር  ውስጥ ተሰውሮ የሚያዝ ነው፡፡ ለምሳ ኢትዮጵያ፡፡ አንግዲህ ይህ ድምፀ ነገር በውስጡ ደብቆ የያዛት የምንወዳት ገራችን ምን ያህል ሳብ በዙሪያዋ ላይ ሊገለፅ እንደሚቻል ስለእርሱዋ የተጻፉትን መጻሕት ማወቅና እኛም ዜጎቿ ስለርሷ እንዴት የተለያየ ሳብ መግለፅ  እንደምችል መገመት ነው፡፡)    

በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ ሥልጣን በአንድ ልሳነኛ (ልሳነኛ ማለት ቋንቋን እንደ ጣኦት በማምለክ፣ የተፈጠረው ሰውን በመሣሪያነት ለማገልገል እንጂ ከሰው በልጦ ለመመለክ አለመሆኑን በመዘነጋት፣ አፍ የፈቱበትን ቡድን ይዞ ሥልጣን ለመጨበጥ የሚጥ ፖለቲከኞች ማለት ነው፡፡ ከአሁን በኋላ የአገራችንን ፖለቲከኛ ማኅበረ ሰቦችን ዘረኞች እያሉ መጥራት   ሳይሆን ነኞች እያልን እንድንጠራቸው ሐሳብ አቀርባለሁ፡፡ ምክንያቱም እኛ ኢትዮጵያውያን ነጮች፣ ቻይኖች፣ ረቦች ወይም ጃፓኖች ሳንሆን ሁላችንም ጥቁሮች ስለሆንን ሌላ ዘር የለብንም፡፡ በተጨማሪም ከአሁን በኋላ ልዩ ልዩ ቋንቋ ተናጋሪዎችን አማሮች፣ ማሌዎች፣ አፋሮች እያልን ሳይሆን አፋኖች ብለን እንጠራቸዋ፡፡) አፋን እጅ እንዲገባ ለማድረግ ውድድር ይታያል፡፡ ይህም ማለት ሥልጣን በአንድ አፋን ሥር ካልወደቀና ይህን ማድረግ ካልቻለ ከኢትዮጵያ መሬት ላይ የቻለውን ያህል ቆርሶ የራሱ ልዑላዊ አገር ሊመሠርት ይከጅላል፡፡ ግን ይህንን ሐሳብ ከየት ተማረው? ያሰኛል፡፡ ስለዚህ የዚህ ሁሉ ሥልጣን  የመጨበጥ እንቅስቃሴ  ማዕበል መነሻው  የዘር ሳይሆን የቋንቋ ልዩነት ባከተለው ልነኝነት መሆኑን  እንገነዘባለን፡፡  ቋንቋ  መነሻ ሊሆን የቻለውኢትዮጵያነታቸውን  አውልቀው ጥለው፣ ኢትዮጵያዊ ከመሆን ይልቅ ማንነታቸውን በቋንቋ ላይ መሥርተው የሥልጣን ጥያቄ በሚያነሱ ነኞች ምክንያት ነው፡፡ ቋንቋ ዕውቀትን ለመገንቢያ፣ ለማበሪያና ለማስፋፊያ፣ ሥራን ለማከናወኛና ለመግባቢያ ሳይሆን፣ ሥልጣን የመጨበጫ መሣርያ አድርጎ ለመጠቀም ትልቅ እንቅስቃሴ ውስጥ የገቡ ኢትዮጵያውያን በመፈጠራቸው ምክንያት ነው፡፡ ይህንን ቫይረስ ፈጥሮ ኢትዮጵያን ንዲያዳርስ ያደረገ ደግሞ ቲፒኤልኤፍ (ትሕነግ) ነው፡፡ ሥልጣን ለመጨበጥ የሚያደርጉት ጥረት ኢትዮጵያን በዕውቀት፣ በሠለጠነና በጥራት ለመምራት ቢሆን ጥሩ ነበር፡፡ ከክፋት የጠራ ሆኖ ጥፋትም አይኖረውም ነበር፡፡ የኢትዮጵያ መሪ ለመሆን ልነኛ መሆን ሳይሆን ዋናው መመዘኛ ብቁ ሆኖ መገኘት ብቻ ነው፡፡ የኢትዮጵያ መሪ ለመሆን አማርኛን ልክ እንደ አቶ መለስ ዜናዊ አቀላጥፎ መናገር ብቻ ነው የሚፈለገው፡፡ ልሳነኖች ይህንን ሲሰሙ ኮሬንቲ እንደሚጨብጡ ይታወቃል፡፡ እንዲህ ላሉ የተከበሩ ልሳነኛ ልሒቃን ምራን ተብዬዎች ምክሬ ኮሬንቲ ቢይዙት ያንጨባርራልና ተውት፣ ይቅርባችሁ ነው፡፡   

ነገሩን ለማጉላትና ለማጠንከር ያህል፣ በየትኛው የአገራችን ብሔራዊ ቋንቋ ነው አፌን  የፈታሁት ሳይሆን ብቁ ነኝ ወይ ነው ዋና መመዘኛው፡፡ ጥፋቱ የሚጀምረው ያንን ሥልጣን ሊጨብጡ የሚጥሩ ሰዎችአገራችንን  ቆራረሰው፣ የራሳቸው የብቻ የሆነ ብሔር ከልለው፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚነገሩ 75 ቋንቋዎች ውስጥ የተለየ  ቋንቋ የምንናግር፣ ብዙ ሕዝብ ያለን  እኛ ነን ብሎ በመመካት ለብቻ በመሰባሰብ፣ ከኢትዮጵያ የተቆረሰ ሌሎች ሉዑላዊ አገሮች  ለመፍጠር ሲሹ ብቻ ነው፡፡ ይህ ማለት እንደዚህ ያሉ ሰዎች ኢትዮጵያዊነታቸውን ካዱ  ማለት ነው፡፡ እንዲህ ያሉ ልሳነኞች ኢትዮጵያን ቆራርሰው ሌሎች ትንንሽ አገሮች ለመፍጠር መሞከር ጠንቁና ጣጣው ብዙ እንደሆነና ጥልቀቱ ምን ያህል እንደሆነ በሚገባ አለማወቅና አለመረዳት ነው፡፡ ጥያቄው፣ ይህንን ሁሉ ኃይልና ጉልበት መጨረስ ለምን አስፈለገ? ነው፡፡

በአንዳንድ የኢትዮጵያ የቋንቋ ምሁራን እምነት፣ ይህ ችግር ሊፈጠር የቻለው ቋንቋዎቻችንን እንዳንጽፍና በጽሑፍ እንዳንጠቀምባቸው ተከለከልን በሚሉ ብሶተኞች ብቻ ሳይሆን እንደነዚህ ያሉ ብሶቶች የተጠነሰሱት በሌሎች የቋንቋ ምሁራንና ልሳነኞች አስተሳሰቦች የመነጨ ነው ብለን እናምናለን፡፡ ይበልጥ ለማብራራት ችግሩ በአብዛኛው የሚናፈሰው የቋንቋም የፖለቲካም አዋቂዎች እኛ ብቻ ነን በሚሉ ምሁራን ነው ለማለትም ይቻላል፡፡ ችግር ፈጣሪዎቹም የተወሰኑ ግለሰቦች ናቸው ብሎ መቀበልም ይቻላል፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ግን  ከደሙ ንፁህ ነው፡፡ አዋቂ ነን በሚሉ ምሁራን የሚፈጠረውን ችግር ሕዝቡ ትኩረት የሚሰጠው በትክክልም የሚያውቀው አይመስልም፡፡ ቋንቋ ራሱ በባህርዩ የተወሳሰበ ነው፡፡ ይህንን ባለመረዳት ልሳነኛ ምሁራን ነን ባዮቹ የበለጠ  በተወሳሰበ ግንዛቤ  ምክንያት ተጨማሪ የተወሳሰበ ችግር ይፈጥራሉ፡፡ ፈጥረውም በኢትዮጵያውያን ዘንድ የመለያየት ማዕበልን  ያስነሳሉ፡፡

ከዚህ ቀጥሎ ስለኢትዮጵያ፣ ስለሕዝቧ፣ ስለቋንቋ ምንነትና ባህሪ፣ በልሳነ ብዙ አገሮች  ውስጥ ስለቋንቋ አጠቃቀም ዝርዝር ሐሳቦችን ምክንያታዊ በሆነ ሥልት እናቀርባለን፡፡ ይህ አስተሳሰብ ለሌሎችም ልሳነ ብዙ አገሮች ምሳሌ እንዲሆን ተስፋ እናደርጋለን፡፡

(ሀ) ከሁሉ በፊት ግን እዚህ ላይ ለማስገባት የምፈልገው ከአሁን ጀምሮ እጅግ በጣም የተከበሩ መሪያችን ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) የተናገሩትን ነው፡፡፡ እኛ ልዩ ልዩ ቋንቋ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያን ሁላችንም እንደመር፡፡ አንድ ኢትዮጵያ ተብላ በዓለም ዙሪያ የታወቀችውን  ብሔራችንን ከውጪ ወራሪ እንጠብቅ፡፡ ሁላችንም አንድ ኢትዮጵያውያን መሆናችንን ተቀብለን ስለቋንቋዎቻችን በእኩልነትና በቅንነት ተወያይተን፣ መፍትሔዎችን ፈልገን፣ በአንድነት ተባብረን መኖር እንድንችል እናድርግ፡፡ ይህ የመደመር አርኪ ሐሳብ በእውነተኛ ምሁራን እየተደገፈ ነው፡፡ እንደነ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፣ እንደ አቶ ንጉሡና አቶ ገለታ ዘለቀ፣ እንደ  ዮናስ ብሩ (ዶ/ር) እና እንደ ራሳቸው እንደ ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ያሉ ምሁራን ተስፋ ሰጪ ናቸው፡፡ የኢትዮጵያውያንም የወደፊት ኑሮና ሰላም መድኅን ናቸው ብዬ አምናለሁ፡፡

አሁን በቅርቡም የጥንቱ የጧቱ፣ ከለብለብ ምሁርነት የፀዱ፣ እውነተኛው ምሁር፣ ግርማ ሙሊሣ (ፕሮፌሰር) ‘የመማር ማስተማር ዓመታት ትውስታዎቼ’ በሚለውና በ2012 በታተመው መጽሐፋቸው መጨረሻው ገጽ ላይ የመደመሩንም የፍልስፍናውንም፣ በዕውቀት ላይ ያልተመሠረተ የዕውር ድንብር ቸፍቸፍ እንቅስቃሴ የማይጠቅም መሆኑን፣ እንደሚከተለው ያብራሩታል፡፡ ‘ወጣቶች ተስፋ አትቁረጡ፣ አገራችሁን ለማሳደግ ወደ ኋላ አትበሉ፣ መቼስ ማንም አገር አልፎ አልፎ ችግር ላይ መውደቁ አይቀርም፣ በተለዩ ምክንያቶች፣ በደካማ አመራር፣ በአየር ንብረት መቃወስ፣ በፖለቲካ አለመረጋጋት ወዘተ፡፡ ያ ሁሉ ያልፋል፣ በቀላሉ አትወናበዱ፣ ስንት የሚሠራ አለ፣ ለመታገል ወኔ ይኑራችሁ፣ ለመማር፣ ለማወቅ ራሳችሁን አሰናዱ፡፡ ያልሠለጠነ፣ ያለተገራ አንጎል ከሞራ አይለይም! አንጎላችሁን አሠሩት፣ አነቃቁት፣ እንዲገነባ፣ እንዲያለማ፣ እንዲፈጥር አድርጉ! መልካም የፈጠራ ዓመታት!’

እኔ የፕሮፌሰሩን ቁልፍ ሐሳብ በአጭሩ ለማጉላትና ለማጠናከር የምፈልገው አምላካችን ከ’ሞራ አንጎል’ የተግባራት ውጤትና ኢሰብዓዊ ዕርምጃዎች ይጠብቀን ነው፡፡

ቀጥሎ የዓብይ (ዶ/ር) የመደመር ጽንሰ ሐሳብ ምን እንደሆነ ለማወቅ ትኩረት እንዲሰጠው እፈልጋለሁ፡፡ መደመር ምን እንደሆነ ለማወቅም ‘ክሱትነት’ በሚሉት ድምፀ ነገር ውስጥ የታጨቀውን ጽንሰ ሐሳብ በሚገባ ለመረዳት በመሞከር መጀመር ነው፡፡ ክሱትነትን በገጽ 40 ላይ እንደሚከተለው ይገልጹታል፡፡ “የእያንዳንዱ ነገር አፈጣጠር ከትንንሽ ነገሮች መሰባሰብ የመጣ ነው፡፡ ተፈጥሮ ዕውን የሆነችው ትንንሽ ነገሮች ተሰባስበው ትልልቅ ነገሮችን እየፈጠሩ ነው፡፡ የሰው ልጅ አሁን የመሠረታቸው ትልልቅ ኅብረቶች ከቤተሰብና ከጎሳ አደረጃጀቶች ተነስተው እዚህ የደረሱ ናቸው፡፡ ሥርዓቶች ያላቸው ምርጫ ወይ እያደጉ ህልውናቸውን እያረጋገጡ መሄድ ወይም እያነሱ ጥፋታቸውን እያረጋገጡ መሄድ ነው፡፡ እያደጉና ህልውናቸውን እያረጋገጡ ወደ ምልዓት መጓዛቸውንና በትልቅ ምንነት ውስጥ መገለጣቸውን ነው ‘ክሱትነት’ የምንለው፡፡ ክሱትነት በዕድገት ውስጥ ህልውናን እያረጋገጡ የመምጣት ሒደት ነው፡፡ ህልውና የሚረጋገጠው በዕድገት ውስጥ ብቻ ነውና፡፡ ክሱትነት የሚመጣው ነገሮች እየተሰባሰቡ፣ እየተከማቹና እየካበቱ ሲመጡ ነው፡፡ ይህንን ሒደት ነው እንግዲህ መደመር የምንለው፡፡”

ዓብይ (ዶ/ር) ‘እያንዳንዱ ነገር’ የሚሉት አንባቢዎችንም ይጨምራል፡፡ እስቲ እያንዳንዱ አንባቢ ራሱን ስንት ነገሮች ተጠራቅመው ቆሞ እንዲሄድ ያደረጉትን ይመርምር፡፡ ከእግር ጥፍሩ እስከ ራስ ፀጉሩ ያሉትን መቁጠር ነው፡፡ ሁሉም ተደምረው ሰውየውን አደረጉት፡፡ ሰውየው በምሉዕነት ተአምር ሊሠራ ይችላል፡፡

ኢትዮጵያም ከመሬታችን አንዷ ትንሽ ክፍል ናት፡፡ እንደ ሩሲያ፣ እንደ ቻይናና እንደ ካናዳ ያሉ አገሮች ደግሞ ትልልቆች ክፍሎች ናቸው፡፡ መሬት ራሷ ከአፈር፣ ከቋጥኞች፣ ከአሸዋዎች፣ ከውኃዎችና ከተራሮች የተገነባች ናት፡፡ የኢትዮጵያም ትንሽ የመሬት ክፍል በሕዝብ ብዛትም ከቻይኖች፣ ከሩሲያዎችና ከአሜሪካውያን ያነስን ነን፡፡ በዕድገት ደረጃም ከነሱ  በጣም ዝቅ ያል ነን፡፡

እኛ ኢትዮጵያውያን ከ75 በላይ አፋኖች በአንድ የመንግሥት ጥላ ሥር ተሰባስበን የምንኖር ነን፡፡ አፋኖችም በጎሳ የተከፋፈሉ ናቸው፡፡ በትንንሽና በትልልቅ አካባቢዎችም የተሰባሰቡ ናቸው፡፡ እንደ ዓብይ አስተሳሰብ አነዚህ ትንንሽና ትልልቅ አፋኖችና አካባቢዎች ተደምረው ትልቋን ኢትዮጵያን እንፍጠር ነው፡፡ የዚህን ተቃራኒ የሚያደርጉ አፋኖች ትንንሽ ፈጥረው ኢትዮጵያን ለመገንባት ሳይሆን ታላቁን የህዳሴ ግድብ ለግብፅ ለማስረከብ የሚጥሩ ከሃዲዎች ናቸው ማለት ይቻላል፡፡ (ይቅርታ በተግባራቸው ስለሚያናድዱኝ ነው፡፡) አለበለዚያ ግን ትንንሽ ሆኖ ዕድገት ለማምጣት መጣር ዕድገትን ሳይሆን ከዓብይ የመደመር ሐሳብ በመውሰድ ‘እያነሱ ጥፋታቸውን እያረጋገጡ መሄድ ነው፡፡’    

(ለ) የኢትዮጵያ መሬት የኢትዮጵያውያን  ሁሉ አንጡራ ሀብት ናት፡፡ ከውጭ ወራሪ ይከላከሏታል፡፡ እኛ በኢትዮጵያ ላይ የሰፈርነው ሕዝቧ  የብዙ ቋንቋዎች ባለቤቶች ነን፡፡ አፋኖች ነን እንጂ አማሮች፣ ኦሮሞች፣ ትግራዋዮች፣ ሶማሌዎች ወዘተ ነን እያልን ራሳችንን ከሌላው የተለየን ፍጡራን አድርገን ማየት አጉል አስተሳሰብ ነው፡፡ ይህ ማለት ግን እኔ የጠራሁ አማራ ነኝ፡፡ እኔ የጠራሁ ኦሮሞ ነኝ፣ እኔ የጠራሁ ትግራዋይ ነኝ፣ እኔ የጠራሁ ሶማሌ ነኝ ማለትና መሆንን ኢትዮጵያነትን በምንም ዓይነት አስተሳሰብም ሆነ መንገድ የሚያግደው፣ የሚያስቀረው፣ የሚያሳፍረው፣ የሚያሸማቅቀው ነገር የለም፡፡ የሚያስፈልገው ይህ ሁኔታ ሊፈጥረው የሚችለው ከሞራ በፀዳ አንጎል በማሰብ እንጂ በለመ ጣሩ (በኦሮምኛ አያዳግሜ የሚል ስም የተሰጠው ዱላ) የሰውን አንጎል በመፈጥፈጥ አይደለም፡፡ ማወቅ ያለብን ሁሉም ቋንቋዎች የሁላችንም ቋንቋዎች ናቸው፡፡ ሁሉም ብሔራዊ ቋንቋዎቻችን ናቸው፡፡ ከዚህ አስተሳሰብ ከወጣን ከሰርን ማለት ነው፡፡ አልተደመርንም ማለት ነው፡፡ ሌላው ማወቅ ያለብን፣ በዘርም የጥቁር ሕዝብ ዘር ነን ብለናል፡፡ ባለማወቅ እርስ በርሳችንም ብናናቅ ይህ ድርጊት ወይ በጅራፍ ወይ በእውነተኛ ምሁራዊ ዕውቀት መጥፋት አለበት፡፡ ለኔ በዕውቀት ቢጠፋ ይሻለኛል፡፡

ስለዚህ የኢትዮጵያውያን ልሒቃን ተብዬዎች የተማሩት እውነተኛ ትምህርት ከሆነ በስሜታዊ ቅዠት ተወናብደው እስከዛሬ ድረስ ተምረንባት የተከበርንበትን አገር ቆራርሰው ለመካፈል በሚያደርጉት ጥረት ለሚያደርሱት ችግር ከኢትዮጵያ ሕዝብ የሚመጣባቸውን የስቃይ እርግማን፣ ጥላቻና ትዝብት ከዓለም ሕዝብ የሚመጣባቸውን ወቀሳ ለመቀበል ይዘጋጁ እንላለን፡፡ በሕይወት ከቆዩ፡፡

(ሐ) ከዚህ ቀጥሎ የሚቀርበው ሁላችንም ከተስማማን ኢትዮጵያ ለዓለም የምታበረክተው ዕውቀት ይሆናል፡፡ ይህም ዕውቀት ስለቋንቋ ባህሪይና ምንነት ዝርዝር ሁኔታዎችን ማሳወቂያና ማስረጃዎች ጋር የተያያዘ ነው፡፡ እነዚህ አስተሳሰቦች ከዚህ በፊት በማንም ሰው የቀረቡ አይመስለኝም፡፡ በልሳነ ብዙ አገሮች ስለቋንቋ ምንነትና አጠቃቀም ሚዛናዊ ዕይታ ይፈጥራሉ ብዬ በማሰብ እንደሚከተለው አቀርባቸዋለሁ፡፡

ማንኛውም ቋንቋ በሕግም ሆነ በተፈጥሮ የማንም ሕዝብ የብቻ ንብረት ዕውቀትና ችሎታ ሊሆን አይችልም፡፡ ለምሳሌ አማርኛ የአማሮች ቋንቋ ነው ብሎ ማመን የተሳሳተ እምነት ነው፡፡ ይህ እውነታ ለሁሉም ቋንቋዎች ይሠራል፡፡ ለዚህ ማስረጃው ብዙ ኢትዮጵያውያን አማርኛን ይናገሩታል፡፡ ከ40 ዓመት በላይ የሆኑ የተማሩ ኢትዮጵያውያን ደግሞ ተምረውበታል፡፡ እንዲህ በመሆኑ ምንም ዓይነት ውርደትም ሆነ ጉዳት የደረሰባቸው አይመስልም፡፡ በተጨማሪም በመጀመሪያ አፋችንን የፈታነው በአፋን ኦሮሞ ወይንም በሌላ ቋንቋ ስለሆነ አዕምሯችን ሌላ ቋንቋ ማወቅ አይችልም ብሎ ማሳመን አይቻልም፡፡ ይህ ለሁሉም ቋንቋ ተናጋሪች ይሠራል፡፡ ለተጨማሪ መረጃ ቋንቋ የማነው?ውን (ታክለ፡ 1995) ይመልከቱ፡፡

ከላይ የተመለከተው በዝርዝር ሲቀርብ ቋንቋ ከሁለት ነገሮች የተሠራ ነው፡፡ እነዚህም ሁለት ነገሮች ነገረ ነገሮችና ድምፀ ነገሮች ናችው፡፡ ለምሳሌ  ስልቻ ቀልቀሎና skin bag፡፡ ስልቻ ቀልቀሎና skin bag ድምፀ ነገሮች ናቸው፡፡ እነዚህ ድምፀ ነገሮች በጆሮ ይሰማሉ፡፡ በውስጣቸው የተቀበረው ነገረ ነገር ግን አይሰማም፣ አይታይምም፡፡ ድምፀ ነገሮቹ ውስጥ የተቀበሩት በመጀመሪያ ቋንቋዎቹን በተናገሩት ሰዎች ነው፡፡ ኦሮሞኛ የሚናገሩ ኢትዮጵያውያን ቀልቀሎ የሚለው ድምፀ ነገር ውሰጥ የተቀበረውን ነገረ ነገር ወዲያው ያውቁታል፡፡ የእንግሊዝኛ ተናጋሪዎችም skin bag በሚለው ድምፀ ነገር ውስጥ ያለውን ነገረ ነገር ያውቁታል፡፡ የአማርኛ ተናጋሪዎችም እንዲሁ ስልቻ ውስጥ የተቀበረውን ነገረ ነገር ያውቁታል፡፡ የቋንቋ ምስጢር ይኸው ነው፡፡ እንግዲህ ቀልቀሎ ቀልቀሎ ነው እንጂ በምንም  ዓይነት ስልቻ ወይንም skin bag ሊሆን አይችልም ቢባል ባለ ስልቻዎቹም የለም ስልቻ እያልን ኖረናልና በምንም ዓይነት ስልቻ ቀልቀሎ ወይንም skin bag ሊሆን አይችልምና በኢትዮጵያ ውስጥ ስልቻ የሚለው ድምፀ ነገር ብቻ ነው መሰማት ያለበት ብለው አስበዋል ብሎ ማመን አይቻልም፡፡ እንዲህ እያሉ ያልተባለ ነገር ይዘው በመነታረክና በመበጣበጥ አገር ማመሳቀልና መበታተን በሰው ዘር ሁሉ አዕምሮ ተቀባይነት እይኖረውም፡፡ ሁሉም ቋንቋዎች ይኑሩና በየተናጋጋሪዎቻቸው ይነገሩ፡፡ ዘላለም እንደተደረገውና ወደፊትም እንደሚደረገው ይቀጥል፡፡ እስከ 1983 ዓ.ም. ድረስ ማንም የኢትዮጵያ መንግሥት በቋንቋዎቻችሁ አትናገሩ አላለም፡፡ ቢባልም ወፈገዝት ይሆናል፡፡ አይሆንምም አይሠራምም፡፡ የማይካደው እውነታ ግን ከአማርኛ ሌላ ሌሎቹ ቋንቋዎች በጽሑፍ አለመዋላቸው ነው፡፡ ቅሬታው ይህ ብቻ ነው ሊሆን የሚችለው፡፡ ታዲያ ይህ ጉዳይ በመነጋገር ለማስተካከል ሲቻል እኛ ኢትዮጵያውያን አይደለንም ብሎ ጎጆ ለመውጣት አገር መቆራረስ ይገባል? የኢትዮጵያ ችግር በዚህ ሐሳብ ዙሪያ ስለሆነ ከዚች አዙረት ለመውጣት ዘዴ እንፈልግ፡፡ ከብት ካልዋለበት ኩበት ለቀማ ይቁም፡፡

በኢትዮጵያ ውስጥ የኢትዮጵያ ብሔረሰቦች ጥናት ኢንስቲቲዩት፣ አጭር የኢትዮጵያ ብሔረሰቦች ማሳወቂያ በተባለው ሪፖርት እንደተገለጸው 75 ቋንቋዎች አሉ፡፡

ከነዚህ ቋንቋዎች ውስጥ ሁሉ ለብዙ ዘመናት በጽሑፍ የዋለውና በመደበኛ ትምህርትና  በመንግሥት ሥራ ጥቅም ላይ የዋለው አማርኛ ብቻ ስለሆነ የማስተማርያ፣ የመንግሥት ሥራ ማከናወኛና ብሔራዊ ቋንቋ ሆኖ አገልግሏል፡፡ ይኼ ማንንም ኢትዮጵያዊ አልጎዳም ጠቀመው  እንጂ፡፡ ከስሜት ፀድቶ ሊጎዳ የሚችለው ስለቋንቋ ምንነትና አጠቃቀም አለማወቅ ብቻ መሆኑን ማወቅ ነው፡፡

ባለፈው ዘመን አማርኛን በብሔራዊ ቋንቋነት እንድንጠቀምበት የተደረገበት ምክንያት በጊዜው በተደረሰበት የዕውቀትና የኢኮኖሚን (Economy) ደረጃ የኢትዮጵያን አንድነትና ዕድገት ለመጠበቅ እንጂ ኢትዮጵያውያን እኛ ኢትዮጵያውያን አይደለንም የሚሉ ኢትዮጵያውያን እንዲበቅሉና አገር ለማፍረስ እንዲችሉ ድርጊታቸውን ለማፋጠን ዕውቀታቸውን ለማዳበር አልነበረም፡፡ ያ ሁሉ ጥረት አሁን ኢትዮጵያውያን ለደረሱበት የዕውቀትና የዕድገት ደረጃ ደርሰው ኢትዮጵያን ለማፈራረስ በሚጥሩ ዜጎች ለመሙላት አልነበረም፡፡ ይህ ሁኔታም በመፈጠሩም ያሳርራል፡፡

አሁን ለደረስንበት ሁኔታ ዋናው መነሻ የኢትዮጵያ ጽንስ በተፈጠረበትና በጎለበተበት ማሕፀን ውስጥ በቅለው ያደጉ ዘመናውያን ምሁራን ናቸው፡፡ ቲፒኤልኤፎች፡፡ የሚገርመው ዋናዋ የአክሱም ጽዮን ቤተ ክርሰቲያን ባለችበት ቦታና የኦርቶዶክስ ሃይማኖት በሰፈነበት አካባቢ የበቀሉ ሰዎች፣ እግዚአብሔርን የካዱና ሃይማኖተቢስ ወጣቶች ፋፍተው አንድን ለዘመናዊ ዕድገት የምትጥር አገርን አቅጣጫ ለውጠው ለዚህ ሁሉ ብጥብጥ በሩን ከፍተው ለውጥረት የዳርጉንን ልጆች ራሱ የትግራይ ሕዝብ በቃችሁ፣ ተው አለማለቱ ነው፡፡ ግን እነርሱም አይፈረድባቸውም፡፡ በምን ዕውቀታቸውና አቅማቸው ይቋቋሟቸው?

እግዚአብሔር ፊቱን ወደኛ ሲመልስ ዓብይ (ዶ/ር) እና አቶ ለማን እንዲሁም አጋሮቻቸውን ለመሪነት ሰጥቶናል፡፡ የዓብይ መመርያዎችና ራዕይዮች ገንቢ ናቸው፡፡ እጅግ ዕውቀት የገባቸው ልሳነኞች ሰሚ ጆሮ ካገኙ ዓብይ ምን አሉ? እንደመር፡ ይህም ማለት አማራ ሲደመር ትግራዋይ ሲደመር ኦሮሞ ሲደመር ሶማሌ ሲደመር ሲዳማ ሲደመር ወዘተ ይሆናሉ ኢትዮጵያዊ ማለት ነው፡፡ ይኸው ነው፡፡ ይህ ሲሆን ችግሩ ተፈታ ማለት ነው፡፡

ሌላው እጅግ ጠቃሚ ነገር የነገሩን ነገር አለ፡፡ ይኸውም ቀንዳቸውን አሹለው አጠገባችን አትድረሱ ብትደርሱ ወዮላቸሁ? ለሚሉና ለውጊያ የሚዘጋጁትን ኮርማዎች የሚያስጠነቅቁበት ነገር ነው፡፡ ምን አሉ? ሐሳቤን በጉልበት (በዱላ በታንክና በመድፍ) ሌሎች እንዲቀበሉት አደርጋለሁ ብሎ መነሳት ፋሽኑ ያለፈበት ኋላቀር አስተሳሰብ ነው፡፡ ለማንም አይበጅም ብለዋል፡፡ ግን ሰሚ አግኝቶ ይሆን? ካልሰሙ እንዲሰሙ ይደረጋል የሚሉም ይመስላል፡፡ ታዲያ ይህ ሁሉ ትርምስ ለምን አስፈለገ?

ሌላው ጉዳይ ዕለት ዕለት ለማስተማርያነትም ሆነ ለመቀስቀሻነት በብዙኃን መገናኛ አማካይነት በአማርኛ ቋንቋ በምንጠቀምበት ጊዜ የሚመጣው ያልተስተካከለ አስተሳሰብና ዕውቀት ነው፡፡ ችግሩም የሚፈጠረው ከአገር ምሁራን አዕምሮ በፈለቁ አስተሳሰቦች በሚመነጩ ቃላትና ከአገር ውጭ የሆኑ አስተሳሰቦችን ባዘሉ ቃላት አስተሳሰቦችና አዕምሮ ውስጥ ግልጽ ያልሆኑ ወይንም ያልተስተካከሉ አስተሳሰቦች የሚረጩ ቃላት በሚፈጠሩ ነገረ ነገራት ነው፡፡ ቃላቱ የሚመነጩት ከሦስት ርዕዮተ ዓለም ነው፡፡ አንደኛው የአገር ውስጥ ምሁራን ከሆኑ ምንጮች ነው፡፡ ሁለተኛው ከምዕራቡ ዓለም የተቃረሙ ናቸው፡፡ ሦስተኛው ምንጭ በኮሚዩኒስቱ ርዕዮተ ዓለም ተፅዕኖ የገቡ ናቸው፡፡

ይህንንም ለማሳየት ብሔር ብሐረሰብ ሕዝቦች በተባሉ ግልጽነት በጎደላቸው ቃላት በመጀመር ነው፡፡ በነዚህ ቃላት ዙሪያ የተገኙት ነገረ ነገሮች ከነዚህ ሦስት ርዕዮተ ዓለም የተጋጩ ምንጮች ነው፡፡ ይህንንም በሚገባ ለማስረዳት በአገር ምሁራን አስተሳሰብ ብሔር የሚለው ቃል በውስጡ ያዘለው መሬት ወይንም ቦታን ነው፡፡ ብሔር ከአንድ ትንሽ ቦታስከ ጠቅላላው ዓለም ድረስ ያለውን ያጠቃልላል፡፡ ትንሿን ቦታ ለማሳየት ተስፋ ገብረሥላሴ  ዘብሔረ ቡልጋ ሲል፣ አፈወርቅ ገብረኢየሱስ ዘብሔረ ዘጌ ይላል፡፡ በአለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ በተጻፈው የግዕዝና የአማርኛ መዝገበ ቃለት ውስጥ እንደ ተገለጸው እግዚእ ማለት ታላቁ ጌታ ማለት ነው፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔር ማለት የጠቅላላው የፍጥረት ሁሉ ጌታ ማለት ነው፡፡ በመሆኑም ኢትዮጵያ አንድ ብሔር ናት፡፡ ስለዚህ የአማራ ብሔር፣ የትግራዋይ ብሔር፣ የኦሮሞ ብሔር ወዘተ የሚባል ነገር የለም፡፡ እነዚህ አፋኖች ብሔሮች ሊሆኑ የሚችሉት ከኢትዮጵያ ብሔር ላይ የቻሉትን ያህል መሬት ወስደው የራሳቸውን መንግሥታት አቋቁመው የተባበሩት መንግሥታት አባል ሲሆኑ ብቻ ነው፡፡

ስለዚህ በአገራዊ አስተሳሰባችን መሠረት ብሔር ሕዝብን አያመለክትም መሬትን እንጂ፡፡ ስለዚህ አፅንኦት ለመስጠት ያህል የአማራ ብሔር፣ የኦሮሞ ብሔር፣ የትግራዋይ ብሔር ወዘተ የሚባል ነገር በኢትዮጵያ ውስጥ የለም፡፡ ኢትዮጵያ ግን እንደ አንድ ብሔር አለች፡፡ ሕዝቡም የልዩ ልዩ ቋንቋዎች ተናጋሪ ሕዝብ ነው፡፡ በግዕዙ ብሔረሰብ ማለት የሰው አገር ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ኢትዮጵያ የኢትዮጵያውያን ሰዎች ብሔር ናት፡፡ ዘመናዊ የኮሚዩኒስት ርዕዮተ ዓለምን የሚከተሉ ምሁራን ግን አንድን ቋንቋ የሚናገር ማኅበረሰብን ለማመልከት ከስታሊን ገልብጠው ብሔረሰብ እያሉ ያደናግሩበታል፡፡ ቀጥሎ የሚመጣው ከምዕራቡ ርዕዮተ ዓለም ነው፡፡ የዚህን ርዕዮተ ዓለም ለሚከተሉ ምሁራን ኢትዮጵያ ያለጥርጥር ብሔር (NATION) ናት፡፡ አሜሪካ ብሔር (NATION) እንደሆነች ሁሉ፡፡

ሕዝቦች የሚለውን ቃል ኮሚኒዩኒስቶቹ የሚጠቀሙት ልዩ ልዩ ቋንቋዎች ተናጋሪ ኢትዮጵያውያንን ለማመልከት ነው (nationalities ከሚለው ያገኙት ነው)፡፡ ነገር ግን በአንድ ብሔራዊ (ጠቅላላ አገሩን የሚያቅፍ) አገር ውስጥ ልዩ ልዩ ቋንቋዎች የሚናገሩ ማኅበረሰቦች መኖር ሸክምም ችግርም አይደለም፡፡ እኛ ኢትዮጵያውያን ለሌላው ጥሩ ምሳሌ ለመሆንና ለሌላው ዓለም ትምህርት መስጠት እንችላለን፡፡ ጉሬላ (Guerrilla Warfare) የተባለውን የውጊያ ጥበብ እንዳስተማርነው ሁሉ፡፡ ይህንን ለማድረግ ይህ አሁን የጀመርነው እንደ የምሁራን መድረክ ተቆጥሮ ቋንቋዎቻችንን እንዴት አድርገን እንደምንጠቀምባቸው? ብለን ጠይቀን የሚያስፈልገውን ያህል ተመራምረን የሚፈለገውን ጥናት አጥንተን መፍትሔውን ማግኘት ከቻልን የምሁር ተግባራችንን መወጣት ችለናል ማለት ነው፡፡ ከመበጣበጥም ራሳችንን እናተርፋለን፡፡

ሌላው ትልቁን አለመግባባት ሊፈጥር የሚችለው የመጻፊያ ፊደል ጉዳይ ነው፡፡ እንደሚታውቀው እስከዛሬ ድረስ በኢትዮጵያ የምንጠቀምበት በግዕዙ ፊደል ነው፡፡ ይህ ፊደል እያለ የአውሮፓ ቅኝ ገዢዎችን የላቲን ፊደል መጠቀም ለኢትዮጵያ አይስማማም፡፡ ይህንን የሚያደርጉ ልሳነኞች ተነጥሎ ከላይ እንደተመለከተው ሌላ አገር ከኢትዮጵያ ብሔር ላይ ቆርሶ ሌላ ነፃ ብሔር ለመፍጠር የታለመ ድርጊት ያስመስለዋል፡፡ ይህ ችግር ሊፈታ የሚችለው ማንነታችንን ለመግለጽ የምንችለው ከዚህ በፊት ቋንቋችንን እንዳንጽፍ ያደረጉንን ለማሸማቀቅ በላቲን ፊደል መጻፍ አለብን ብለው ቂም በቀል አዝለው በተነሱ ምርጥ ምሁራንና ረዳቶቻቸው የተጠነሰሰ ይመስላል፡፡ ይህ የምሁራን መድረክ ለዚህ ችግር መፍትሔ ማግኘት አለበት እንላለን፡፡

ሌላው ትልቅ ችግር በማንነት ጥያቄ ዙሪያ የሚነሱ የምሁራን ጥያቄዎች ናቸው፡፡ ይህን ሁሉ ችግር በኢትዮጵያ የሚያሠራጩት ምን እንደሚያደርጉ ያወቁ፣ ዓላማም ያላቸው ናቸው ብሎ መገመት ይቻላል፡፡ የሚገርመው ምንም ሳያስቡ የነዚህን መሰሪ ዓላማ ለማስፈጸም የሚሯሯጡት ናቸው፡፡ሰሪዎቹ ማን እንደሆኑ ራሳቸውን መርምረው ማንነታቸውን አውቀው የሚሠሩ ናቸው፡፡ ነገር ግን የነሱን ፈለግ ለመከተል የሚፈልጉት አጥብቀው ማወቅ ያለባቸው ከኢትዮጵያዊነት የሚበልጥ ምንም ዓይነት ማንነት ሊኖር አይችልም፡፡ መታወቅ ያለበት ልሳነኞች ኢትዮጵያውያን አፋኖች መሆንን በምንም መንገድ አይከለክልም አያግድምም፡፡

ሌላው ከቋንቋ አጠቃቀም ጋርና ከፊደል አመራረጥ ጋር የተያያዘው ጉዳይ ነው፡፡ ቋንቋ በመጀመሪያ በጽሑፍ ውሎ መደበኛ ቋንቋ መሆን መቻል አለበት፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ በጽሑፍ የዋለው ግዕዝ ብቻ ነበር፡፡ ከዚያ በኋላ በጽሑፍ የዋለው አማርኛ ነው፡፡ የተጻፈውም በግዕዝ ፊደል ነው፡፡ ይህ ፊደል የኢትዮጵያ ፊደል ሆኗል ለማለት ይቻላል፡፡ ይህንን ፊደል የማይቀበል ኢትዮጵያዊ ኢትዮጵያዊነቱ የሚያጠራጥር ይሆናል፡፡ እንዲህ ማለት መብት  መጋፋት ነው ሊባል ይችላል፡፡ ግን ለዚህ መፍትሔው ጉዳዩ ለሕግ ምክር ቤት ወይንም ለውሳኔ ሕዝብ ቀርቦ ይወሰናል እንጂ አንድ የምሁራን ወገን ብቻ መወሰን የለበትም፡፡

ከዚህ ቀጥሎ የማቀርብላችሁ ደግሞ ቅኔ ሲባል በሰማሁት መሠረት የራሴን ሰም ለበስ ኅብር ቅኔ ነው ብዬ ያሰብሁትን ቅኔ ነው፡፡ እኔ ነኝ ቅኔ አዋቂ የሚል ሰው ቅኔውን እንዲፈታው እጠይቃለሁ፡፡ ቅኔው የቋንቋ አጠቃቀም በኢትዮጵያ በሚለው መጽሐፌ ውስጥ 60 ላይ ይገኛል፡፡

ቅኔውም እንዲህ ይላል፡

                    ግንባር ተለቀና ከመላ አካላችን

                    በብጉር ተመላ ጠቅላላ ፊታችን

                    ግንባር ከሰውነት ካልተስተካከለ

                    ብጉር ያጠፋናል ካደረ ከዋለ፡፡

ለነገሩ ግንባርሚወክለው የትግራይ ሕዝብ ነፃ አውጪ ግንባርን ነው፡፡ ብጉር ድግሞ ወያኔ የፈጠራቸውን ክልሎች ያመለክታል፡፡ ግንባር ከኢትዮጵያና ከኢትዮጵያን ሁሉ በለጠና በሥልጣን ገዝፎ ሥልጣኑን ለማስጠበቅ ሕዝቡን በአፋን ላይ በተመሠረተ ክልል ሸንሽኖና ከፋፍሎ ኢትዮጵያን ለማጥፋት የዘረጋው ሥርዓት ጠፍቶ ብጉሮች ጠፍተው ወያኔ ራሱን ከኢትዮጵያ ጋር ካልተስተካከለ ኢትዮጵያ ትጠፋለች ነው፡፡    

የአሁኑ ቅኔዬ ደግሞ

ብጉርሽ ሊከስም ነው እልል በይ ኢትዮጵያ

ዓብይ ደምሮናል እያለሽ ሃሌ ሉያ!                         

እሰቲ ሁላችሁም ይህንን ጽሑፍ አንብባችሁ ተወያዩበት፡፡ ይህንን ጽሑፍ ቋንቋ የማነው? ከሚለው እና የቋንቋ አጠቃቀም በኢትዮጵያ ከተባለው ከጻፍኋቸው መጻሕፍት ጋርና በሪፖርተር ጋዜጣ ጥቅምት 14 ቀን 2011 ዓ.ም. ባሳተምኩት ጽሑፍ ጋር ደምራችሁ አንብቧቸው፡፡ ጥያቄ ካላችሁ በ 0911 160975 ደውላችሁ ጠይቁኝ፡፡ ብዙ ሆናችሁ ለውይይት ከጋበዛችሁኝ እገኛለሁ፡፡ የቋንቋ አጠቃቀም በኢትዮጵያ አራት ኪሎ በሚገኙት ዩኒቨርሳል መጻሕፍት፣ አንከቦት መጻሕፍት ቤትና አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መጻሕፍት ማዕከል ይገኛል፡፡ ቋንቋ የማነው? የሚለውን ከፈለጋችሁ ደውሉልኛና ጠይቁኝ ታገኛላችሁ፡፡

ከአዘጋጁ፡- ጽሑፉ የጸሐፊውን አመለካከት ብቻ የሚያንፀባርቅ ሲሆን፣ በኢሜይል አድራሻቸው  [email protected] ማግኘት ይቻላል፡፡

spot_imgspot_img
- Advertisment -

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

Related Articles