የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፔዮ በአዲስ አበባ ቆይታቸው ከፕሬዚዳት ሳህለ ወርቅ ዘውዴና ከጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ ጋር በብሔራዊ ቤተመንግሥትና በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት፣ እንዲሁም ከአቻቸው አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ጋር የካቲት 10 ቀን 2012 ዓ.ም. ተወያይተዋል፡፡ ከተለያዩ ማኅበረሰብ ተወካዮችም ጋር በአሜሪካ ኤምባሲ ቆይታ አድርገዋል፡፡ ፎቶዎቹ የቆይታቸውን ከፊል ገጽታ ያሳያሉ፡፡
ፎቶ ዳንኤል ጌታቸውና መስፍን ሰሎሞን