Wednesday, June 12, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ኪንና ባህል“አንትሮሽት” - የእናቶች ቀን  በጉራጌ

“አንትሮሽት” – የእናቶች ቀን  በጉራጌ

ቀን:

በጉራጌ ዞን የሚከበረው የአንትሮሽት በዓል እናቶች እንዲያርፉና እንዲደሰቱ፣ ልጆቻቸው የተለያዩ ስጦታዎች በማበርከት ምርቃት የሚያገኙበት፣ የተጣላ የሚታረቅበት፣ ባል ሚስቱን የሚያከብርበትና በተራው ምግብ ሠርቶ የሚመግብበት ነው፡፡ እንዲሁም ለእናቶች የሚታረድ በሬ እንዳቅሙ የሚገዛበት የጎረቤት እናቶችና ሴቶች ተሰባስበው የተለያዩ የባህል ምግቦች አዘጋጅተው በዓሉን በድምቀት ያከብሩታል፡፡

ማኅበረሰቡ ‹‹አንትሮሽት›› እያለ በየዓመቱ የሚያከብረው የእናቶች ቀን፣ 300 ዓመታት በላይ እንደተካሄደ ይነገርለታል፡፡ በዕለቱ እናቶች ታጥበው፣ ያልተነጠረ ቅቤ ተቀብተው፣ በልዩ የበዓል ልብስና ጌጣ ጌጥ ይዋባሉ፡፡ የእናቲቷ የመጀመርያ ልጅ ወንድ ከሆነ ወይም ሴት ከሆነች የተለያየ ሥርዓት ይከተላሉ፡፡ ለምሳሌ ሴት የበኩር ልጆች እናታቸውን ቅቤ ይቀባሉ፡፡ ልጅ የሌላቸው ሴቶች በዓሉን ከጎረቤቶቻቸው ጋር ያሳልፋሉ፡፡

ከሴቶችና ሕፃናት ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ እንደሚገልጸው፣  የአንትሮሽት የእናቶች ቀን በዓል በጉራጌ ዞን በቸሃ ወረዳ መገናሴ ቀበሌ በዞኑ ሴቶች ሕፃናትና ወጣቶች መምርያ አስተባባሪነት ሰሞኑን ተከብሯል፡፡ በእናቶች ምርቃት የተጀመረውን በዓል ከተለያዩ ቀበሌዎች የመጡ እናቶች በጉራጌኛ ጭፈራና ዘፈን አድምቀውታል፡፡ 

- Advertisement -

የአንትሮሽት በዓል በማኅበረሰቡ ዘንድ ያሉትን የመከባበርና የሰላም እሴቶቻችን ይበልጥ እንዲለሙ የሚደረጉበት፣ ሴቶች መብታቸውን እንዲያስከብሩና ተጠቃሚነታቸውን እንዲያረጋግጡ ትልቅ ፋይዳ ያለው በዓል ነው ሲሉ የተናገሩት የጉራጌ ዞን ሴቶች ሕፃናትና ወጣቶች መመርያ ኃላፊ / ገነት ደምስስ ናቸው፡፡

“አንትሮሽት” - የእናቶች ቀን  በጉራጌ

 

የቁጠባ ባህል መነሻው የአንትሮሽት በዓል ነው ያሉት ኃላፊዋ፣ ከዚህ ልምድ በመነሳት የዞኑ ሴቶች በዚህ ግማሽ ዓመት ብቻ 80 ሚሊዮን ብር በላይ መቆጠብ ችለዋል፡፡ በመጨረሻም በዓሉ ልጆች ከእናቶቻቸው ምርቃት የሚቀበሉበት የተጣሉ ካሉ የሚታረቁበትና ፍቅር የሚሞላበት በዓል በመሆኑ ሁሉም ይህንን አጎልብቶ ሴቶችን ተጠቃሚ ለማድረግ የሚጠበቅበትን መወጣት አለበት ብለዋል፡፡

የቸሃ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ፈለቀ ኃይሌ በበኩላቸው አንትሮሽን በአገር አቀፍ ደረጃ የኢትዮጵያ እናቶች ቀን ሆኖ እንዲከበር የመንግሥት ተቋማት፣ ሚዲያዎችና ምሁራን ትኩረት ሰጥተው ሊሠሩ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

እናት በወለደችው ልጅና በባለቤቷ የምትከበርበት አንትሮሽት፣ በማኅበረሰቡ ዘንድ ያሉትን የመከባበርና የሰላም እሴቶች እንዲለሙ የሚደረግበትና ሴቶች መብቶቻቸውን እንዲያስከብሩ፣ ተጠቃሚነታቸውን እንዲያረጋግጡና ባህላዊ እሴቶቻቸውን የሚያጠናክሩበት ዕለት ነው።

እንደ ኃላፊዋ አገላለጽ አንትሮሽት ወይም የእናቶች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃማርች 8” በማለት የሴቶች የመሪነት ተሟጋች ውጤታማነት ቀን ከመከበሩ አስቀድሞ የጉራጌ እናቶች ቀድመው ሴቶች ከወንዶች ጋር እኩል መብት የጠየቁበት፣ ዕረፍት እንደሚያስፈልግባቸው ያወጁበት ቀን መሆኑም መረጃዎች ያመላክታሉ።

 የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የጥናትና ምርምር ክፍል ወደ ቸሀ ወረዳ ድረስ በመግባት ጥናት እንዳደረገበት የተናገሩት ኃላፊዋ፣ ይህ የሴቶች ቀን 250 እስከ 300 ዓመታት በፊት በእናቶች የተጀመረ በዓል እንደሆነም አስረድተዋል።

በዚህ የበዓል ቀን እናቶች ዘወትር ከጠዋቱ 12 ሰዓት እስከ ምሽት ድረስ እንጨት ሲለቅሙ፣ ውኃ ሲቀዱ፣ ቆጮ ሲጋግሩ፣ አካባቢያቸውን ሲያጸዱና መሰል ተግባራት ሲከውኑ ከርመውአንድ ቀን ልናርፍና ልንከበር ይገባል” በማለት በጥር ወር መጨረሻ በዓሉን ያከብሩታል ብለዋል።

ከጉራጌ ዞን አስተዳደር የሕዝብ ግንኙነት ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ እንደሚገልጸው፣ እናቶች በአንትሮሽት ደስታቸው ወደር የሌለውና እናት ከምንም ነገር በላይ የሚያስደስታት ሆዷ ማራስና ቅቤ መቀባት እንደሆነ የሚቀርቡትም የሥጋ ክትፎ፣ አይቤ፣ የጎመን ክትፎ፣ ዝማሙጃት ሌሎች ምግቦች ለሚታደሙ እናቶች ይቀርባል፡፡ ከተበላና ከተጠጣ በኋላ፣ በቀዬው ውብ ድምፅ ያላት ሴት ተመርጣ ለተከበሩ እናቶች ታዜማለች፡፡ እናቶች ከቤተሰባቸው ባሻገር ለኅብረተሰቡ ያበረከቱት ነገር እየተጠቀሰም ይሞገሳሉ፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ በመንግሥት የሚታወጁ ንቅናቄዎችን በተመለከተ ባለቤታቸው ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየሞከሩ ነው]

እኔ ምልህ? እ... ዛሬ ደግሞ ምን ልትይ ነው? ንቅናቄዎችን አላበዙባችሁም? የምን ንቅናቄ? በመንግሥት...

የመንግሥት የ2017 ዓ.ም በጀትና የሚነሱ ጥያቄዎች

የ2017 ዓመት የመንግሥት ረቂቅ በጀት ባለፈው ሳምንት መገባደጃ ለሚኒስትሮች...

ከፖለቲካ አባልነትና ከባንክ ድርሻ ነፃ የሆኑ ቦርድ ዳይሬክተሮችን ያካተተው ብሔራዊ ባንክ ያዘጋጃቸው ረቂቅ አዋጅና መመርያዎች

የኢትዮጵያ የብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ ተቋማትን የተመለከቱት ድንጋጌዎችንና የባንክ ማቋቋሚያ...

የልምድ ልውውጥ!

እነሆ መንገድ ከቦሌ ሜክሲኮ። አንዱ እኮ ነው፣ ‹‹እንደ ሰሞኑ...