Thursday, February 9, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትእግር ኳስ ፌዴሬሽን የተጫዋቾች የዝውውር ቀነ ገደብ አሳወቀ

እግር ኳስ ፌዴሬሽን የተጫዋቾች የዝውውር ቀነ ገደብ አሳወቀ

ቀን:

ከወርኃዊ ክፍያ ጋር ጥያቄ ያላቸው ተጨዋቾች አጋጣሚውን እንዳይጠቀሙ ተሰግቷል

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ2012 ውድድር ዓመት የአንደኛ ዙር መርሐ ግብር መጠናቀቁን ተከትሎ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የተጫዋቾችን የዝውውር ቀነ ገደብ ይፋ አደረገ፡፡ የውድድር ዓመቱ የአንደኛ ዙር የጨዋታ መርሐ ግብር መጠናቀቁን ተከትሎ በርካታ ተጨዋቾች ከደመወዝ ክፍያ ጋር ተያይዞ ከነበሩበት ክለብ ለመልቀቅ ውሳኔ ላይ እየደረሱ መሆኑ እየተነገረ ይገኛል፡፡

ፕሪሚየር ሊጉ ከሁለት አሠርታት በላይ ባስቆጠረው ዕድሜው፣ ዘመኑን የሚመጥን እንቅስቃሴና ደረጃ ላይ መድረስ እንደተሳነው ይወሳል፡፡ እግር ኳሱ ይባስ ብሎ በፋይናንስ ቀውስ እየተመታ መሆኑ ችግሩን አሳሳቢ አድርጎበት መነጋገሪያ ሆኖ ይገኛል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እ.ኤ.አ በ2012/13 ለአፍሪካ ዋንጫና ለአፍሪካ አገሮች ዋንጫ (ቻን) ተሳትፎ መብቃቱን ተከትሎ የተጫዋቾች የደመወዝ ጣሪያና የዝውውር ክፍያ ማሻቀቡ ይታወሳል፡፡ ይህም ከቅዱስ ጊዮርጊስና ኢትዮጵያ ቡና ውጪ የተቀሩት በከነማ ስም በመንግሥት በጀት የሚንቀሳቀሱ ናቸው፡፡ ይህም ሆኖ ኦዲት በማይደረግ ፋይናንስ የሚንቀሳቀሱ እንዳሉም ይነገራል፡፡

ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ከሰሞኑ በማኅበራዊ ድረ ገጹ እንዳስነበበው ከሆነ፣ የዘንድሮ የአንደኛ ዙር ጨዋታ መጠናቀቁን ተከትሎ ተጨዋቾች ከየካቲት 16 እስከ መጋቢት 16 ቀን 2012 ዓ.ም. ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ ከክለብ ወደ ክለብ መዘዋወር እንደሚችሉ ይፋ አድርጓል፡፡ ይህ ጉዳይ ለተጨዋቾች መብት ቢሆንም እንደ ጅማ አባ ጅፋር፣ አዳማ ከተማና ሌሎችም ለተጨዋቾች ወርኃዊ ክፍያ ለመክፈል እየተንገዳገዱ ለሚገኙ ቡድኖች አደጋ ይዞ መምጣቱ አልቀረም፡፡

የዝውውር ቀነ ገደብ ከታወቀበት ዕለት ጀምሮ የሁለቱ ክለቦች ተጨዋቾች የቆዩበትን ክለብ ለመልቀቅ ወደ ሌላ ክለብ ለመሄድ መዘጋጀታቸው እየተነገረ ነው፡፡ ከሁለቱ ክለቦች በተጨማሪ ባህር ዳር ከተማ፣ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ፣ ድሬዳዋ ከተማና ሌሎችም የፕሪሚየር ሊጉ ክለቦች በተመሳሳይ ችግር ውስጥ መቆየታቸው ይታወሳል፡፡

በዚህ ጉዳይ ሪፖርተር ያነጋገራቸው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አመራሮች ከሆነ፣ ተቋሙ በዓለም አቀፍ እግር ኳስ ማኅበር (ፊፋ) ደንብ መሠረት የተጫዋቾችን የዝውውር ቀነ ገደብ ይፋ አድርጓል፡፡ በተለይ በፋይናንስ ቀውስ ውስጥ የሚገኙ ክለቦች በዚህ ውሳኔ በርካታ ተጫዋቾቻቸውን እንደሚያጡ ቢታወቅም፣ ነገር ግን ምንም ማድረግ እንደማይችሉ ያስረዳሉ፡፡

ወርኃዊ ክፍያ ያልተፈጸመላቸው በርካታ ተጫዋቾች ጉዳያቸው በፌዴሬሽኑ በኩል እልባት እንዲያገኝ ሲጠይቁ የቆዩ መኖራቸውን የሚናገሩት እነዚሁ አመራሮች፣ ለእነዚህ ተጨዋቾች ይህን አጋጣሚ የሚጠቀሙ ሊኖሩ እንደሚችሉ ይጠብቃሉ፡፡

የውድድር ዓመቱ ከመጀመሩ አስቀድሞ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው የክለብ አመራሮችና ባለቤቶች ጋር መምከሩን የሚያወሳው ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ፣ በወቅቱ የተጫዋቾች ወርኃዊ ክፍያ 50,000 ብር እንዲሆን፣ ከዚህ ውጪ ከተጫዋች ጋር ውል አድርጎ የተገኘ የክለብ አመራር ሕጋዊ ዕርምጃ እንዲወሰድበት ከውሳኔ ተደርሶ ነበር፡፡ ይሁንና የስምምነቱ ፊርማ ሳይደርቅ አንዳንዶቹ ክለቦች ከተጫዋች ጋር በሕገወጥ መንገድ ሲዋዋሉ የነበሩበት አጋጣሚ መታየቱን ያስረዳሉ፡፡

“እነዚህ ክለቦች አሁንም ማድረግ የሚጠበቅባቸው ቀደም ሲል ከዝውውር ጋር ተያይዞ ለወጣው ሕግ ተገዥ እንዲሆኑ ነው፡፡ ይህን ሳያደርጉ ተጨዋቾች ያገኙትን አጋጣሚ እንጠቀማለን ቢሉ ከልካይ አይኖራቸውም፤” የሚሉት አመራሮቹ እየገጠማቸው ያለውን በፋይናንስ ቀውስ ሊያካክስ የገቢ አማራጭ ማፈላለግ ግድ እንደሚል ያስረዳሉ፡፡         

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ጥቁር የመልበስ ውዝግብና የእምነት ነፃነት በኢትዮጵያ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ኅዳር ወር ላይ በፓርላማ...

የኢንሹራንስ ዘርፉን የሚቆጠጠር ገለልተኛ ተቋም ለመመሥረት እንቅስቃሴ ተጀመረ

ከ70 በላይ አዳዲስ የፋይናንስ ተቋማት ዘርፉን ሊቀላቀሉ ነው የኢትዮጵያ ብሔራዊ...

እስቲ አንገፋፋ!

እነሆ መንገድ። ጊዜና ሥፍራ ተጋግዘው በውስንነት ይዘውናል። መፍጠን ያቃተው...