Wednesday, June 12, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ልናገርስለሳተላይት — “ካወራህ መቼ አነሰህ?"

ስለሳተላይት — “ካወራህ መቼ አነሰህ?”

ቀን:

በአበራ ሳህሌ

ከሳይንስ ጋር ላለመደራረስ ቃለ መሃላ የፈጸምነው ድሮ ነበር። የስፔስ ሳይንስ ማኅበርና ኢንስቲቲዩቱ ምሥጋና ይግባቸውና ጉጉት መፍጠር ብቻ ሳይሆን እንድናወራም ዕድል ሰጥተውናል። በቅርቡ ያመጠቁት ‹‹ETRSS-1›› ሳይንስን በተግባር ያሳዩበት ነው። ሳተላይቱ ሲወነጨፍ መመልከቱ ምን ያህል እንደሚያነሳሳ መገመት ይቻላል። የአገር ውስጥ ባለሙያዎች በመቆጣጠሪያ ጣቢያ ውስጥ ሆነው ሥራቸውን ሲያከናውኑ መመልከት ሕዋ ለአሜሪካኖችና ለሩሲያውያን ብቻ የተተወ አለመሆኑን በግልጽ ያሳያል። ከዘርፉ ምን እናገኛለን የሚለው ወደፊት መነጋገሪያ ይሆናል። ጅማሮው ግን በአገሪቱ የሳይንስ ዘርፍ ትልቅ ምዕራፍ መሆኑ አያጠያይቅም። 

የሰው ልጅ ተራቆ . . .

- Advertisement -

ስለሳተላይት ማውራት መጀመራችን በራሱ ለተቋሙ ስኬት ነው። የህዋው ነገር ብዙ ባይገባንም ችላ ግን አላልነውም። ጥላሁን ገሠሠም በዘፈኑየሰው ልጅ ተራቅቆ ጨረቃ ላይ ወጥቷል…ሲል ጉዳዩን በአርምሞም ቢሆን እየተመለከትነው መሆኑን አሳይቷል። ስለእነ ዩሪ ጋጋሪን፣ ጨረቃ ላይ ስለወጡት አሜሪካውያን እነ ኒል አርምስትሮንግ፣ ስለመንኩራኩሮች ብዙ ሲባል ነበር። እንዲያውም በደርግ ጊዜ ከወዳጅ አገር የሚላኩትበሶቪየት ኅብረት ወፎች በነፃነት ይበራሉየሚሉትጥናታዊፊልሞች ስለህዋ ምርምር ዕድገት፣ ስለእነ ስፑትኒክ የጠፈር መንኩራኩሮች ብዙ ይሉ ነበር። ችግሩ እዚያ ላይ ወጥተው ምን እንደሚሠሩ ለእኛ ጠብ የሚል ነገር ይኑራቸው አይኑራቸው የምናውቅበት፣ ወይም ስለጥቅማቸውበክራርየሚያጫውተን ጠፍቶ ስንባጅ ቆይተናል። ወደኋላ ግን ኢንተርኔት ሲመጣ ወረቱ አለፈ። ድረ ገጽ፣ ማኅበራዊ ግንኙነት፣ ጉግልዩቲዩብ እያሉ የምን ሳተላይት! 

ሰሞኑን ግን ቀልባችን በመሳቡ እንደገና ፊታችንን አዙረናል። ግርግሩን  አስታክኮ ባለሙያዎቹ ከየአቅጣጫው በድጋፍም ሆነ በነቀፌታ ድምፃቸውን እያሰሙ ነው። የመነጋገሪያ ርዕስ መሆኑ ትልቅ ነገር ነው። እኛምእንዲህ ነው እንዴ?ከማለት ባሻገር፣ ስለጉዳዩ ለመጨዋወት ብርታት አግኝተናል፡፡ ካወራህ መች አነሰህ!” ታዲያ አሁን ያለው ሳተላይት ምን ያመጣልናል? በጓሮ ሜዳ በኩል ለሚያልፈው የጋራዥ ሠራተኛ ወይም ለሉማሜው የስድስተኛ ክፍል የሒሳብ መምህር  ምን ይጠቅመዋል? ይህንን ባለሙያዎች ሊያስረዱን ይገባል።

የሱሉልታውሳተላይት

በድሮው ጊዜ በጥቁርና ነጭ ቴሌቪዥን የዓለም ዋንጫ ሲታይ አስተዋዋቂዎቹከሱሉልታ የምድር ሳተላይት ጣቢያ በቀጥታእያሉ የግዙፉን ሳህን ምሥል በፎቶ አስደግፈው ያሳዩን ነበር። እንግዲህ ሌላው ቢቀር ስፔንም ሆነ አርጀንቲና የነበረውን የዓለም ዋንጫ መቀበያጠልፎእንዳመጣልን እናስታውሳለን። በምን በምን አድርጎ የሚለው አሳስቦን አያውቅም። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በአንድም ሆነ በሌላ ከሳተላይት ግንኙነት ጋር ቅርርብ መፍጠራችን አልቀረም። ላለፉት 15 እና 20 ዓመታት ያህል የመቀበያ ሳህኖች ክብደት የተጫጫናቸው ቤቶች የከተሞቻችን ገጽታ ሆነዋል። ሲጀመር በአብዛኛው ዓረብኛ እንደ ሁኔታው ደግሞ ሲኤንኤን፣ ቢቢሲና ዩሮ ኒውስ እንደዜርፎርሥጋ ወጥ ጣል ጣል የተደረጉባቸው ሥርጭቶች ስንቀበል ቆይተናል። ወደ በኋላ ደግሞ በአገርኛ ቋንቋዎች ከውጭም ሆነ ከአገር ውስጥ መሠራጨት ጀምረዋል። 

የሬዲዮን ውለታ ወሰደው ቲቪው

ከቴሌቪዥኑ በፊት የሳተላይት ሬዲዮ በየቤቱ በአነስተኛ ዋጋ ግን በከፍተኛ ጥራት (በሲዲ እንደሚደመጠው) ለማስፋፋት፣ ትውልደ ኢትዮጵያዊው ኖህ ሳማራ ከፍተኛ ጥረት አድርገው ነበር። የሬዲዮውን ጠቀሜታ ለማስተዋወቅና ባለሀብቶች እንዲሳተፉበት ለማግባባት በታላላቅ ሆቴሎችና በመገናኛ ብዙኃን የተቻላቸውን ጥረት አድርገዋል። ወርልድ ስፔስ የተባለው ከጃፓን ኩባንያዎች ጋር በመተባበር ሲያሠሩት የነበረው ሬዲዮ ዋጋው ትንሽ ወደድ ያለ ቢሆንም፣ በጥራት መቼም ተስተካካይ አልነበረውም። 24 ሰዓት ሙሉ የሚሠሩ በአብዛኛው ወደ ሙዚቃ ያደሉ በርካታ የሬዲዮ ጣቢያዎች ነበሩት። ስምጥ ሸለቆውን ይዞ ወደ አርባ ምንጭ ያሉቱሪስት ተኮርሆቴሎችዲጄ ለምኔብለው የዚያን ሬዲዮ ሙዚቃ  ቀኑን ሙሉ ሲያንቆረቁሩት ይውሉ ነበር። ይሁንና ያንን የሚጠቀሙ የአገር ውስጥ ጣቢያዎች ባለመምጣታቸውበተለይም ደግሞ ትኩረቱን ባደረገው የአፍሪካና የእስያ አገሮች በቂ ደንበኞች መሳብ ባለመቻሉ ወርልድ ስፔስ ከገበያ ሊወጣ ችሏል። ኢሳት እስኪመጣ ድረስ የሳተላይት ሥርጭትን ጥቅም በበቂ አላወቅነውም ማለት ይቻላል። ከዚያ በኋላ ያለው እንግዲህ ታሪክ ነው ይባላል።

ኢትዮሳት

የኢትዮጵያ መንግሥት ይቃወሙኛል የሚላቸውን የሳተላይት ሥርጭቶችን ለማፈን ሳያሰልስ ሠርቷል:: አንዳንዴ ትጋቱ መጠን እያለፈ የራሱንም ቴሌቪዥን ከሥርጭት ሲያወጣው አጥፍቶ ጠፊ፣  አልቃይዳ እየተባለ ሲቀለድበት ነበር:: በኋላ ምናልባትም ለቁጥጥር ይመቻል በሚል ይመስላል የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ (ኢንሳ) የተባለው መሥሪያ ቤት የሳተላይት ሥርጭት ሁሉም በአንድ መስመር ገብቶ፣ እኔ ባቋቋምኩት ኢትዮሳት ሥር ያስተላልፋል ሲል ነበር። ከአስተማማኝነቱ በተጨማሪ የውጭ ምንዛሪን እንደሚያድንና ፈረንሣይ ከሚገኝው ዩቴልሳት ከተባለ ድርጅት ጋር መፈራረሙን በመገናኛ ብዙኃን አስነግሯል። ከለውጡ ጋር ጡንቻው ሲሰልልየውሾን ነገር ያነሳ . . .” ብሎ በዝግታ ቦታውን ለቅቋል። በቅርቡ የተከራይ አከራይ በሚመስል ሁኔታ ዋና ዋና የሚባሉት ቴሌቪዥን ጣቢያዎች ከአንድ የውጭ ኩባንያ ጋር በመተባበር፣ ኢትዮሳት የሚል ድርጅት ፈጥረዋል። ዓረብሳትና ናይልሳት ጉድ ይፈላባቸው እንደሆነ የምናየው ይሆናል።

ለብር ወይስ ለማሊያ ፍቅር? 

ባለፈው ሰሞን የቴሌዋ ኃላፊ ሲናገሩ ኢትዮጵያ ለሳተላይት ኪራይ በዓመት ወደ አራት ሚሊየን የሚጠጋ ዶላር ትከፍላለች ብለዋል። በቅርብ ዓመታት የተከፈቱት ቴሌቪዥኖችም ለአገልግሎቱ  ክፍያ ይፈጸማሉ። የናሁ ቴሌቪዥን ኃላፊ አቶ ቴዎድሮስ ሽፈራው ሰሞኑን እንደገለጹት፣ በየወሩ ለሳተላይት ኪራይ ከሁለት እስከ ሦስት ሚሊዮን ብር ይከፍላሉ። ፋና ቴሌቪዥን ግምቱን ከየት እንዳመጣው ባይታወቅም አገሪቱ በዓመት ወደ 12 ሚሊዮን ዶላር ለዚሁ አገልግሎት  እንደምትከፍል ገልጿል።ETRSS-1” ከዚህ ወጪ ምን ያህሉን እንደምታድን ባናውቅም፣ ፈርጇ ለየት ያለና ሥርጭት ከሚያገለግሉት እንደማትመደብ የስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ሰለሞን በላይ (ዶ/ር) አርድተውናል። ሆኖም ተቋማቸው በሦስትመት ውስጥ ለግንኙነት አገልግሎት የሚውለውን ለመላክ ዝግጅት መጀመሩን አስረድተዋል። የዋጋው ነገር አይነሳ! 400 ሚሊዮን ዶላር። የናይልሳት ባለቤት ግብፅ  ምንኛ ቢተርፋት ነው ላለፉት 20 ዓመታት ከአንድም ሁለት ሦስቱን የላከችው?!

በዛም አለ በዚህ የጠፈር ምርምሩ ዘላቂነት የሚወሰነው በሚያስወጣው ወጪ ሳይሆን ኑሮን በማሻሻል በኩል በሚያበረክተው አስተዋጽኦ ነው። ከአዲስነቱ አንፃር ገና በበቂው የተፈተሸ ዘርፍ ባይሆንም መጪውን ጊዜ  መቀላቀሉ ግን እርግጥ ነው።

ከአዘጋጁ፡- ጽሑፉ የጸሐፊውን አመለካከት ብቻ የሚያንፀባርቅ ሲሆን፣ በኢሜይል አድራሻቸው  [email protected] ማግኘት ይቻላል፡፡ 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ በመንግሥት የሚታወጁ ንቅናቄዎችን በተመለከተ ባለቤታቸው ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየሞከሩ ነው]

እኔ ምልህ? እ... ዛሬ ደግሞ ምን ልትይ ነው? ንቅናቄዎችን አላበዙባችሁም? የምን ንቅናቄ? በመንግሥት...

የመንግሥት የ2017 ዓ.ም በጀትና የሚነሱ ጥያቄዎች

የ2017 ዓመት የመንግሥት ረቂቅ በጀት ባለፈው ሳምንት መገባደጃ ለሚኒስትሮች...

ከፖለቲካ አባልነትና ከባንክ ድርሻ ነፃ የሆኑ ቦርድ ዳይሬክተሮችን ያካተተው ብሔራዊ ባንክ ያዘጋጃቸው ረቂቅ አዋጅና መመርያዎች

የኢትዮጵያ የብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ ተቋማትን የተመለከቱት ድንጋጌዎችንና የባንክ ማቋቋሚያ...

የልምድ ልውውጥ!

እነሆ መንገድ ከቦሌ ሜክሲኮ። አንዱ እኮ ነው፣ ‹‹እንደ ሰሞኑ...