ኢትዮ ቴሌኮም በብሮድባንድ ኢንተርኔት ላይ የዋጋ እና የፍጥነት ማሻሻያ ማድረጉን የካቲት 19 ቀን 2012 ዓ.ም. ባዘጋጀው መድረክ ላይ ገልጿል፡፡ የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሪት ፍሬሕይወት ታምሩ ይፋ እንዳደረጉት፣ በብሮድባንድ ኢንተርኔት አገልግሎት ላይ ከ65 በመቶ እስከ 72 በመቶ ቅናሽ ተደርጓል፡፡ የኢንተርኔት ፍጥነቱን እስከ ሦስት እጥፍም አድጓል፡፡ ፎቶዎቹ የዕለቱን ሁነት ከፊል ገጽታ ያሳያሉ፡፡