Thursday, December 1, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisment -
  - Advertisment -

  ታላቁን የዓድዋ ድል ስንዘክር ለኢትዮጵያ ትንሳዔ ተምሳሌት እናድርገው!

  ኢትዮጵያ በዓለም የተመሰከረላት ታሪካዊ አገር ስለመሆኗዋነኛ ቅርሶቿናታላላቅ ታሪካዊ ክንውኖቿ መካከል አንዱ፣ የዛሬ 124 ዓመት በዘመኑ በአውሮፓ ኃያል ከነበሩት ኮሎኒያሊስቶች ተርታ ከሚታወቀውና እስከ አፍንጫው ድረስ ዘመናዊ የጦር መሣሪያ ከታጠቀው የዘመኑ የጣሊያን ዘመናዊ ወራሪ ጦር ጋር ተዋግታ፣ ዓለምን ጉድ ያሰኘውን የዓድዋ አንፀባራቂ ድል መጎናፀፏ ነው፡፡ የካቲት 23 ቀን 1888 .. የአገር ሉዓላዊነትን በመድፈር ቅኝ ለመግዛት ቆርጦ ከተነሳ ኃይል ለመከላከል በተደረገ በዚያ ታሪካዊ ጦርነት የተገኘው ታላቅ ድል ለፓን አፍሪካኒዝም እንቅስቃሴ መፈጠር ምክንያት ከመሆኑም በላይ፣ የመላው ዓለም ጥቁር ሕዝቦችን አንገት በኩራት ቀና ያደረገ ነበር፡፡ ይህ ታላቅና አንፀባራቂ የዓድዋ ድል የተገኘው ደግሞ፣ እናት አገራቸውን ከራሳቸው በላይ እጅግ በጣም ያፈቅሩ በነበሩ ጀግኖች ኢትዮጵያዊያን ነው፡፡ በዓድዋ ተራሮች ላይ በጀግንነት እየፎከሩ ከፊት ረድፍ ሆነው ወራሪውን ኃይል በታላቅ ተጋድሎ ያንበረከኩትን እነዚያ ኩሩ ኢትዮጵያዊያን፣ ታሪክና ትውልድ ለዘለዓለም ይዘክሩዋቸዋል፡፡ ያንን የመሰለ አኩሪና አንፀባራቂ ታላቅ ድል የተቀዳጁትም፣ አገራቸውን ከምንም ነገር በላይ በምክንያታዊነት ያፈቅሩ ስለነበር ነው፡፡ ይህ በምክንያታዊነት ላይ የተመሠረተ የአገር ፍቅር እናት አገራቸውን ከዘመኑ ኃይለኛ ወራሪ ኮሎኒያሊስት ኃይል ከመታደጉም በተጨማሪ፣ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ስሟ በወርቅ ቀለም እንዲመዘገብ አድርጓል፡፡ ታላቁ የዓድዋ ድል 124ኛ ዓመት መታሰቢያ በሚዘከርበት በዚህ ታሪካዊ ወቅት ላይ፣ ምክንያታዊ ሆኖ አገርን በታላቅ ክብር ማገልገል የእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ኃላፊነት እንደሆነ ማሰብ ተገቢ ነው፡፡ ታላቁን የዓድዋ አንፀባራቂ ድል ለኢትዮጵያ ትንሳዔ ተምሳሌት ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

  ኢትዮጵያ አሁን በወሳኝ ታሪካዊ የሽግግር ወቅት ላይ ትገኛለች፡፡ ይኼንን ታላቅና ታሪካዊ ወቅት በብልኃትና በኃላፊነት መንገድ በመምራት አንፀባራቂ ውጤት ለማስመዝገብ፣ ከስሜታዊነት ይልቅ ምክንያታዊነት ያስፈልጋል፡፡ ይህ ታሪካዊ የሽግግር ወቅት በመላ ኢትዮጵያዊያን ሁለገብ ተሳትፎ ወደፊት መራመድ አለበት፡፡ ለዚህ ሽግግር የተቃና ዕርምጃ ደግሞ የብሔር፣ የቋንቋ፣ የእምነት፣ የፖለቲካ አቋምና የመሳሰሉት ልዩነቶች ጠበው ለብሔራዊ ጉዳዮች የጋራ ራዕይ ሊኖር የግድ ይላል፡፡ በስግብግብነትና ከመጠን ባለፈ ራስ ወዳድነት ይህንን መልካም አጋጣሚ ማበላሸትና ማጨናገፍ አይገባም፡፡ ለነፃነት፣ ለእኩልነትና ለፍትሕ የሚደረግ ሽግግር ለኢትዮጵያ ራዕይ በሌላቸው እንዳይጨናገፍ በአንድነት መቆም ተገቢ ነው፡፡ ይህ የሽግግር ወቅት በተለያዩ ምክንያቶች ችግር ሲገጥመው ወይም ተስፋ የሚያስቆርጥ ነገር ሲያጋጥም፣ እንደ ጲላጦስ እጅን እየተጣጠቡ ጣትን ወደ ሌሎች ከመቀሰር ችግርን የጋራ አድርጎ መፍትሔ መፈለግ የዜግነት ግዴታን መወጣት ነው፡፡ ሽግግሩ በስኬት ተጠናቆ በነፃነትና በእኩልነት መኖር የሚቻለው እንደ አየር ፀባይ በሚለዋወጥ ወላዋይ አቋም ሳይሆን፣ መንግሥት ሲሳሳት በመውቀስና የማስተካከያ ሐሳብ በማቅረብ ጭምር ነው፡፡ ሁሉንም ነገር ጽንፍ እያስያዙ ለጭቅጭቅና ለግጭት የሚዳርጉ ችግሮችን ከመኮልኮል ወይም እንደ ነገረኛ ሰው ስህተት ብቻ ከማነፍነፍ ይልቅ፣ የመፍትሔ አካል ሆኖ ለውጤታማነት መታገል ያስከብራል፡፡ ኢትዮጵያ አሁን የምትፈልገው እንደ ዓድዋ ጀግኖች ከፊት ረድፍ ተሠልፈው የሚታገሉላትን እንጂ፣ ወሬ ላይ ተጥደው የአሉባልታ መርዝ እየረጩ የሚያመሳቅሏትን አይደለም፡፡

  ድህነት፣ ሥራ አጥነት፣ ተረጂነት፣ ኋላቀርነት፣ ማይምነትና የመሳሰሉት የዘመናት ልክፍቶች አሁንም የአገር መጠሪያና መዋረጃ ሆነው ሳለ፣ ነጋ ጠባ የማይረቡ አጀንዳዎች እየፈለጉ መነታረክና ሕዝብን ማጋጨት ከኪሳራ በስተቀር ፋይዳ የላቸውም፡፡ ኢትዮጵያ የዴሞክራሲና የፍትሐዊነት አገር መሆን የምትችለው፣ መጀመርያ ለዘመናት ከተዘፈቀችበት የውርደት አረንቋ ውስጥ ስትወጣ ነው፡፡ 110 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ እንዳላት የምትገመት ትልቅ አገር ውስጥ፣ ኢኮኖሚው በፍጥነት አገግሞ በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ ወጣቶች ሥራ መፍጠር ካልተቻለ ቀውስ ይፈጠራል፡፡ ሰላምና መረጋጋት በአስቸኳይ ሰፍኖ ኢኮኖሚው ካለበት አሳሳቢ ሁኔታ ውስጥ መውጣት አለበት፡፡ ሥራ አጥ በበዛበት አገር ውስጥ ሥርዓተ አልበኝነት እንጂ፣ የሕግ የበላይነት ሊሰፍን አይችልም፡፡ በተለይ አገርን ቀውስ ውስጥ የሚከቱ አጀንዳዎችን እየፈበረኩ ሕዝብ የሚያምሱ የግጭት ነጋዴዎች ሰለባ መሆን አይገባም፡፡ ኢትዮጵያ ከፊቷ በርካታ ጉዳዮች የሚጠብቋት አገር መሆኗ እየታወቀ፣ በየሥርቻው በሚፈበረኩ ግጭቶች ስትታመስ የሚጎዳው በስሙ የሚነገድበት ሕዝብ ነው፡፡ ለአገሩ ፍቅርና ቅንነት ያለው እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ማሰብ ያለበት፣ ከኢትዮጵያ ህልውና በላይ ምንም የሚበልጥ ነገር አለመኖሩን ነው፡፡ ይህ ፍቅር ለአገር መስዋዕት መሆን ድረስ መሆኑን ደግሞ የዓድዋ ጀግኖች በሕይወታቸው፣ በደምና በአጥንታቸው አስተምረው በክብር አልፈዋል፡፡

  ኢትዮጵያ የሕግ የበላይነት የሰፈነበት ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እንድትገነባ የሚመኝ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ፣ የግልና የቡድን ጥቅም ከአገር በላይ እንዳይሆን መታገል አለበት፡፡ በዚህ ዘመን አገር እያመሱ ያሉ ግለሰቦችና ቡድኖች ዋና ችግራቸው ከአገር በላይ እንሁን ማለታቸው ነው፡፡ የአገር ክብርና ታሪክ ምንም የማይመስላቸው፣ ሌላው ቀርቶ የዓለም ጥቁሮች መመኪያ የሆነውን ታላቁን የዓድዋ ድል ጭምር ያንቋሽሻሉ፡፡ ለአገር ክብርና ታሪክ ደንታ ቢስ የሆኑ ግለሰቦችና ስብስቦች፣ የአገርን ራዕይ ከማጨናገፍ ወደኋላ አይሉም፡፡ ኢትዮጵያ ለዘመናት መጫወቻ ካደረጋት አምባገነንነት ወደ ዴሞክራሲ ለመሸጋገር ያስችላታል የተባለውን ምርጫ ለማካሄድ ስትዘጋጅ፣ በየቦታው ግጭት በማስነሳት የንፁኃን ሕይወት መቅጠፍ፣ የአገር አንጡራ ሀብት ማውደም፣ ዜጎችን ከቀዬአቸው ማፈናቀልና በአጠቃላይ አገርን ተስፋ ቢስ ማድረግ መወገዝ አለበት፡፡ ለአገር ደንታ የሌላቸው ስግብግቦችና የአቋራጭ ሥልጣን ፈላጊዎች፣ ሕዝቡን እርስ በርስ እያጋጩ አገር እንዲያተራምሱ መፍቀድ አይገባም፡፡ እነዚህን ኃይሎች በሕግ አደብ አስገዝቶ አገርን ወደ ታላቅነት መመለስ ታሪካዊ ግዴታ ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከዳር እስከ ዳር በአንድነት መቆም ይኖርበታል፡፡ የዓድዋ ጀግኖች በመስዋዕትነታቸው ያስተማሩት ይኼንን ታላቅ ኃላፊነት ጭምር ነው፡፡

  የወቅቱን የኢትዮጵያ ሁኔታ በአንክሮ የሚከታተሉ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያንም ሆኑ የውጭ ሰዎች፣ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ተስፋ ከሚጣልባቸው አገሮች አንዷ መሆኗን ቢያምኑም ሥጋት ግን አላቸው፡፡ ኢትዮጵያ ልጆቿ ተባብረው ጠንክረው ከሠሩ ትንሳዔዋ ቅርብ መሆኑን የሚናገሩትን ያህል፣ ወጥረው የያዙዋት ችግሮች ደግሞ ለህልውናዋ ጭምር አሥጊ መሆናቸውን ያሳስባሉ፡፡ እንደ ምሳሌ ከሚነሱ መሠረታዊ ጉዳዮች መካከል በአገሪቱ የተለያዩ ሥፍራዎች የሚከሰቱ ግጭቶችን ማስቆም አለመቻል፣ ምርጫ 2012 እየተቃረበ መሆኑና የተዳከመው ኢኮኖሚ ዋነኞቹ ናቸው፡፡ ግጭትን በተባበረ ጥረት ማስቆም ከተቻለ ሌላው ዕዳው ገብስ ነበር፡፡ ኃላፊነት የማይሰማቸው ፖለቲከኞችም ሆኑ በዙሪያቸው የተኮለኮሉ ሥርዓተ አልበኞች በየቦታው ግጭት እየቀሰቀሱ አገር ከሚያምሱ ለአገር ውለታ ይዋሉ፡፡ እነሱ ሲሰክኑ በመተባበር ምርጫውን ነፃ፣ ፍትሐዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ በማድረግ ታሪክ መሥራት ይቻላል፡፡ የተዳከመው ኢኮኖሚ ተነቃቅቶ ለሚሊዮኖች ሥራ በመፍጠር ተዓምር መሥራት አያቅትም፡፡ በሠለጠነ ንግግር፣ ውይይትና ድርድር የፖለቲካ ምኅዳሩ ክፍት ሲሆን፣ የሐሳብ የበላይነት ያላቸው የፖለቲካ ድርጅቶች የሕዝብ ቀልብ መሳብ ይችላሉ፡፡ ይኼንን ለማድረግ ግን የአገር ፍቅርን በስሜት ብቻ ሳይሆን በተግባር ማሳየት ይገባል፡፡ በተለይ ኢትዮጵያ በታላቁ የህዳሴ ግድብ በምታደርገው ድርድር ጥቅሟ ተላልፎ እንዳይሰጥና በሌሎች ኃይሎች ተፅዕኖ እንዳትንበረከክ፣ ከምንጊዜውም በላይ ኢትዮጵያዊያን አንድነታቸውን ማሳየት ታሪክ የጣለባቸው ግዴታቸው ነው፡፡ ይህንን የታሪክ ምዕራፍ በድል ለመሻገር የሚቻለው እንደ ዓድዋ ጀግኖች ጠንካራ አንድነት በመፍጠር ብቻ ነው፡፡ የዓድዋ ጀግኖችን ታሪክ መድገም የሚቻለውም በዚህ መንገድ ብቻ ነው፡፡ ኢትዮጵያ የምትፈልገውም እንደ ዓድዋ ጀግኖች ከፊት ረድፍ የሚሠለፉላትን የዘመኑን ጀግኖች ብቻ ነው፡፡ ታላቁን የዓድዋ ድል ስንዘክር ለኢትዮጵያ ትንሳዔ ተምሳሌት እናድርገው የሚባለው ለዚህ ነው!

  በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

  ባንኮች እንዲዋሀዱ እስከ ማስገደድ ሊገባ እንደሚችል ብሔራዊ ባንክ ጠቆመ

  በአሁኑ ወቅት የባንኮች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ ችግር የሚሆንና የውጭ...

  የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅን የሚተካ ረቂቅ ተዘጋጀ

  ከቫት ነፃ የነበረው የኤሌክትሪክ ኃይል ገደብ ተቀመጠለት የገንዘብ ሚኒስቴር ከሃያ...

  የአገር ውስጥ የፍራፍሬ ገበያን ፍላጎት ይሸፍናል የተባለለት የብላቴው እርሻ ልማት

  መንግሥት የግብርና ምርታማነትና የፍራፍሬ ምርትን ለማሳደግ በ‹‹አረንጓዴ አሻራ›› በሚል...

  ‹‹ከገበሬው እስከ ሸማቹ ያለውን የንግድ ቅብብሎሽ አመቻቻለሁ›› ያለው ፐርፐዝ ብላክ ውጥኑ ከምን ደረሰ?

  ከመቼውም ጊዜ በላይ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ በተደጋጋሚ የሚሰማ አንድ...
  - Advertisment -

  ትኩስ ፅሁፎች

  [በተቋሙ ሠራተኞች የተወከሉ አንድ ባልደረባ ሚኒስትሩን ለማነጋገር ቀጠሮ ይዘው ወደ ቢሯቸው ገቡ]

  ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም ሰላም ... ተቀመጥ! አመሠግናለሁ ክቡር ሚኒስትር!...

  የጉራጌ ዞን ጥያቄና የክላስተር አደረጃጀት የገጠመው ተቃውሞ

  መንግሥት የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል አካል የነበሩ ዞኖችንና...

  አዋሽ ባንክ ካፒታሉን ወደ 55 ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ያስገደደው ምክንያት ምንድን ነው?

  ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላላ ጉባዔውን ያካሄደው አዋሽ ባንክ የ43 ቢሊዮን...

  አቢሲኒያ ባንክ ካለፈው ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው ትርፍ በማግኘት አዲስ ታሪክ አስመዘገበ

  አቢሲኒያ ባንክ ከቀደሚ የሒሳብ ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው...

  የጉድለታችን ብዛቱ!

  ከፒያሳ ወደ ሜክሲኮ ልንጓዝ ነው። ጎዳናውን ትውስታ እየናጠው ሁለትና...
  spot_img

  ተዛማጅ ፅሁፎች

  ለዘመኑ የማይመጥን አስተሳሰብ ዋጋ ያስከፍላል!

  በኳታር እየተከናወነ ያለው የዓለም ዋንጫ በእግር ኳስ ጨዋታ ውስጥ ያልተጠበቁ ማራኪ ቴክኒኮችንና ታክቲኮችን ከአስገራሚ ውጤቶች ጋር እያስኮመኮመ፣ ከዚህ ቀደም በነበረ ችሎታና ዝና ላይ ተመሥርቶ...

  መንግሥት ለአገር የሚጠቅሙ ምክረ ሐሳቦችን ያዳምጥ!

  በሕዝብ ድምፅ የተመረጠ መንግሥት ለሕዝብ የሚጠቅሙ ሐሳቦችን የማዳመጥ ኃላፊነት አለበት፡፡ ሥራውን ሲያከናውንም በግልጽነት፣ በተጠያቂነትና በኃላፊነት መርህ መመራት ይኖርበታል፡፡ እያንዳንዱ ዕርምጃው በሕግ ከተሰጠው ኃላፊነት አኳያ...

  የሰላም ስምምነቱ ተግባራዊ ይደረግ!

  የሰላም ስምምነቱ ‹‹ታጥቦ ጭቃ›› ሊሆን የሚችልባቸው ምልክቶች እየተስተዋሉ ነው፡፡ ሚሊዮኖችን ለዕልቂት፣ ለመፈናቀል፣ ለከፍተኛ ሰብዓዊ መብት ጥሰትና መሰል ሰቆቃዎች የዳረገው አውዳሚ ጦርነት በፕሪቶሪያው ስምምነት መሠረት...