Sunday, June 23, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊአስቸኳይ ዕርዳታ ለሚሹ ሰባት ሚሊዮን ወገኖች አንድ ቢሊዮን ዶላር ተጠየቀ

አስቸኳይ ዕርዳታ ለሚሹ ሰባት ሚሊዮን ወገኖች አንድ ቢሊዮን ዶላር ተጠየቀ

ቀን:

ፅኑ ድጋፍ ለሚሹ ሰባት ሚሊዮን አስቸኳይ የምግብ ዕርዳታ ፈላጊዎች፣ እ.ኤ.አ. በ2020 አንድ ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ ተገለጸ፡፡ ዓርብ የካቲት 20 ቀን 2012 ዓ.ም. በጄኔቫ በኢትዮጵያ ሰብዓዊ ዕርዳታ ሁኔታ ላይ ውይይት መደረጉን፣ ብሔራዊ የአደጋ ሥጋትና ሥራ አመራር ኮሚሽንና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት በጋራ ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል፡፡

በኢትዮጵያ በረድኤት አገልግሎት የተሰማሩ የዓለም አቀፍ ማኅበረሰቦችን በመወከል በውይይቱ ላይ ንግግር ያደረጉት ካትሪን ሶዚ፣ በኢትዮጵያ ያለውን ውስብስብ የሰብዓዊ ምኅዳርና ወደፊት ሊያጋጥሙ የሚችሉ አደጋዎችን አስረድተዋል፡፡ ከወዲሁ መቆጣጠር ካልተቻለም የበረሃ አንበጣ፣ እንዲሁም ከምርጫ በፊትና በኋላ የሚከሰቱ ችግሮች ሰብዓዊ ጉዳት ሊያስከትሉ ይችላሉ ሲሉም አክለዋል፡፡

‹‹ሰባት ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን ፅኑ ድጋፍ ይፈልጋሉ፡፡ በባለ ብዙ ዘርፍ ችግሮችም አስቸኳይ ዕርዳታ ያስፈልጋቸዋል፡፡ በተያዘው እ.ኤ.አ. 2020 አንድ ቢሊዮን ዶላር ዕርዳታ ያስፈልጋል፡፡ አስቸኳይ ዕርዳታ ከሚያስፈልጋቸው ውስጥ 81 በመቶ የሚሆኑት ሴቶችና ሕፃናት ናቸው፡፡ ወቅታዊና በቂ ዕርዳታ ማቅረብ ከተቻለ በትንሹ 81 በመቶ በሥራ ላይ ያሉ አጋሮች ሥራቸውን ለማከናወን ዝግጁ ናቸው፤›› ብለዋል፡፡

መንግሥት በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ድጋፍ ምግብና ምግብ ነክ ዕርዳታ ለሚሹ በአደጋዎች፣ በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት በሚከሰቱ ድርቆችና በምግብ እጥረት፣ በግጭት መፈናቀሎች ፈተናዎች ለሚቸገሩ፣ በበሽታዎች፣ ኮሌራን በመሳሰሉ ወረርሽኞችና በመሳሰሉት ለሚጎዱ ሚሊዮኖች ለመድረስ ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ በጋዜጣዊ መግለጫው ተመልክቷል፡፡

የብሔራዊ አደጋ ሥጋትና ሥራ አመራር ኮሚሽነር አቶ ምትኩ ካሳ በበኩላቸው፣ ኢትዮጵያ ለበርካታ ዓመታት ከተደጋጋሚ ድርቆችና በየወቅቱ ከሚያጋጥሙ የጎርፍ አደጋዎች እየተጋለጠች እንደነበር፣ አሁንም ድግምግሞሹና ግፊቱ እየጨመረ መሆኑን አመልክተዋል፡፡ እ.ኤ.አ. ከ2017 ጀምሮ ደግሞ በማኅበረሰቦች ውስጥ የሚከሰቱ ግጭቶች ከሚያስከትሏቸው ተፅዕኖዎች ጋር መጋፈጥ ግድ እንደሆነም አስረድተዋል፡፡

ኮሚሽነሩና የሰብዓዊ ዕርዳታ አስተባባሪዋ ዓለም አቀፍ አጋሮች ድጋፍ እንዲያደርጉ አሳስበው፣ በተጨማሪም አስተማማኝ የመፍትሔ መርሐ ግብሮችን ለማዘጋጀት አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

አስጨናቂው የኑሮ ውድነት ወዴት እያመራ ነው?

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የኑሮ ውድነት እንደ አገር ከባድ ፈተና...

‹‹ወላድ ላማቸውን አርደው ከደኸዩት ወንድማማቾች›› ሁሉም ይማር

በንጉሥ ወዳጅነው   የዕለቱን ጽሑፍ በአንድ አንጋፋ አባት ወግ ልጀምር፡፡ ‹‹የአንድ...

የመጋቢቱ ለውጥና ፈተናዎቹ

በታደሰ ሻንቆ ሀ) ችኩሎችና ገታሮች፣ መፈናቀልና ሞትን ያነገሡበት ጊዜ እላይ ...

ጥራት ያለው አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ሥርዓት ሳይዘረጉ አገልግሎት ለመስጠት መነሳት ስህተት ነው!

በተለያዩ የመንግሥትና የግል ተቋማት ውስጥ ተገልጋዮች በከፈሉት ልክ የሚፈልጉትን...