Thursday, March 30, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትበአትሌቲክስ የምርጫ ትርምስ ተጀመረ

በአትሌቲክስ የምርጫ ትርምስ ተጀመረ

ቀን:

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ከ800 ሜትር ጀምሮ የተመረጡ ብሔራዊ አትሌቶችን ዝርዝር ይፋ በማድረግ ለኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ማሳወቁን ገልጿል፡፡ ይሁንና ኦሊምፒክና የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ሲቃረቡ እንደዚህ በፊቱ ሁሉ ከአትሌቶችና አሠልጣኞች ምርጫ ጋር የተያያዙ አለመግባባቶች በመደመጥ ላይ ናቸው፡፡ አንዳንድ አትሌቶች በምርጫው ጉዳይ ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ “አድርሶብናል” የሚሉትን በደል መናገር ጀምረዋል፡፡

ከእነዚህ አትሌቶች መካከል ዓምና (እ.ኤ.አ. 2019) በ1,500 ሜትር የዓለም አቀፍ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማኅበር (ኤይኤኤፍ) ተሸላሚ በመሆን የምትታወቀው ጉዳፍ ፀጋዬ ትጠቀሳለች፡፡ የአትሌቷ ቅሬታ ቀደም ሲል ከምትታወቅበት ርቀት በማውጣት 800 ሜትር ለኦሊምፒክ መመረጧ ነው፡፡ ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ በበኩሏ የአትሌቷ ቅሬታ ትክክል አለመሆኑን በተቋሙ ድረ ገጽ በለቀቀው መግለጫ ያስረዳል፡፡

ይሁንና ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ለቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ በ800 ሜትር የተመረጡ አትሌቶች ዝርዝር ውስጥ የአትሌቷ ስም በተራ ቁጥር ሁለት ተካቶ ይገኛል፡፡ በዝርዝሩ የተካተቱ አትሌቶች ሀብታም ዓለሙ፣ ጉዳፍ ፀጋዬ፣ ደርቤ ወልተጂ፣ ሒሩት መሸሻ፣ ፍሬወይኒ ኃይሌ፣ ማህሌት ሙሉጌታ፣ ኮሬ ቶላ፣ ፍሬ ዘውድ ተስፋዬ፣ ነፃነት ደስታ፣ አያል ዳኛቸውና ደራርቱ ደሲሳ ይጠቀሳሉ፡፡ በወንዶች ቶሎሳ በድሩ፣ ተማም ቱራ፣ አዲሱ ግርማ፣ ቱሪ መርከና፣ ዳንኤል ወልዴ፣ አማረ አማኖ፣ ጣሰው ያዳ፣ ባጫ መረዋ፣ አህመድ ሐሰንና ፈቃዱ አበራ ናቸው፡፡

ፌዴሬሽኑ በተመሳሳይም በ1,500 ሜትር፣ በ3000 ሜትር መሰናክል፣ በ5000 ሜትር፣ 10,000 ሜትርና በማራቶን የመረጣቸውን ብሔራዊ አትሌቶችን ዝርዝር የላከ መሆኑ በድረ ገጹ ይፋ አድርጓል፡፡ እንደ አትሌቶች ምርጫ ሁሉ በአሠልጣኞች ምርጫም ፌዴሬሽኑ ወቀሳና ትችት እያስተናገደ ነው፡፡

በሌላ በኩል በቅርቡ ከአትሌቶችና ከአሠልጣኞች ምርጫ ባልተናነሰ ትልቅ የትርምስ አጀንዳ እንደሚሆን የሚጠበቀው ቀደም ሲል ለ800 ሜትር የተመረጡ አትሌቶች የዝግጅትና የሆቴል ወጪ ጉዳይ እንደሆነ የሚናገሩ አልጠፉም፡፡

ማንነታቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ የፌዴሬሽኑ አንዳንድ ሙያተኞች ከሆነ፣ ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ለዚህ ርቀት ብሎ የመረጣቸው 21 አትሌቶች አንዳቸውም ለኦሊምፒክ የሚያበቃ ሚኒማ የሌላቸው በመሆኑና ይህም በቀጣይ ኦሊምፒክ ኮሚቴውንና አትሌቲክስ ፌዴሬሽኑን የሚያከራክር ጉዳይ አንደሚሆን ጭምር ሥጋታቸውን ይገልጻሉ፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[የምክር ቤቱ አባል ላቀረቡት ጥያቄ በተሰጣቸው ምላሽ አቤቱታቸውን ለክቡር ሚኒስትሩ እያቀረቡ ነው]

ክቡር ሚኒስትር እየሆነ ያለው ነገር ትክክል ነው? ምነው? ምክር ቤቱም ሆነ...

የጉራጌ የክልልነት ጥያቄ ትኩሳት

ቅዳሜ መጋቢት 16 ቀን 2015 ዓ.ም. በጉራጌ ዞን ወልቂጤ...

አይ የእኛ ነገር!

የዛሬው ጉዞ ከጀሞ ወደ ፒያሳ ነው፡፡ መንገዱ ለሥራ በሚጣደፉ፣...

የዓለም ኢኮኖሚ መናጋት ለወቅታዊው የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ችግር ምክንያት ነው?

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ባለፈው ማክሰኞ መጋቢት 16...