Saturday, November 26, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ማኅበራዊአዲስ አበባ ከገቡ መንገደኞች የኮሮና ቫይረስ ተመሳሳይ ምልክት ያሳዩ ሦስት ተጠርጣሪዎች ነፃ...

  አዲስ አበባ ከገቡ መንገደኞች የኮሮና ቫይረስ ተመሳሳይ ምልክት ያሳዩ ሦስት ተጠርጣሪዎች ነፃ መሆናቸው ተገለጸ

  ቀን:

  ኮሮና ቫይረስ በስድስት የአፍሪካ አገሮች ተከስቷል

  አዲስ አበባ ከገቡ መንገደኞች የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ተመሳሳይ ምልክት ያሳዩ ሦስት ተጠርጣሪዎች ላይ በተደረገው የላቦራቶሪ ምርመራ ነፃ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ፡፡

  ኢንስቲትዩቱ ኮቪድ-19ን አስመልክቶ የካቲት 24 ቀን 2012 ዓ.ም. በሰጠው ሳምንታዊ መግለጫ እንዳስታወቀው፣ ሰባት አዳዲስ ጭምጭምታዎች ለኢንስቲትዩቱ የድንገተኛ የኅብረተሰብ ጤና አደጋዎች ምላሽ ማስተባበሪያ ማዕከል የደረሱ ሲሆን፣ በሁሉም ጥቆማዎች ላይ ማጣራት ሥራ ተደርጓል፡፡ ሦስት ታካሚዎች የበሽታው ተመሳሳይ ምልክት በማሳየታቸው በለይቶ ማቆያ ክትትልና የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎላቸው ከቫይረሱ ነፃ መሆናቸው ተረጋግጧል፡፡

  በኢትዮጵያ ሁሉም መግቢያ ጣቢያዎች በገቡ 40,518 ሰዎች ላይ የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) እና የኢቦላ ሙቀት ልየታ ምርመራ መደረጉንና በዚህም ቫይረሱ ወደ ኢትዮጵያ እንዳልገባ መረጋገጡንም ኢንስቲትዩት ገልጿል፡፡

  ከጥር 15 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ በአጠቃላይ 90 ጭምጭምታዎች ለኢንስቲትዩቱ የድንገተኛ የኅብረተሰብ ጤና አደጋዎች ምላሽ ማስተባበሪያ ማዕከል ደርሰው በሁሉም ጥቆማዎች ላይ ማጣራት ተደርጓል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ 24ቱ የበሽታው ተመሳሳይ ምልክቶች በማሳየታቸውና በሽታውን ሪፖርት ያደረጉ አገሮች የጉዞ ታሪክ የነበራቸው በመሆኑ፣ በተለያየ ጊዜ በለይቶ ማቆያ ማዕከል እንዲቆዩ ተደርጓል፡፡

  የላቦራቶሪ ምርመራ ውጤታቸው ከቫይረሱ ነፃ መሆናቸውን ማረጋገጡ፣ ወደ ኅብረተሰቡ እንዲቀላቀሉ የተደረገ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ምንም ዓይነት ተጠርጣሪ በለይቶ ማቆያ ውስጥ የሌለ መሆኑን ኢንስቲትዩቱ አስታውቋል፡፡

  በሳምንቱ በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ በሰባቱ መግቢያዎች ብቻ 21,750 መንገደኞች በሙቀት ልየታው ያለፉ ሲሆን፣ ከእነዚህ ውስጥ 508 በሽታውን ሪፖርት ካደረጉ አገሮች የመጡ ናቸው፡፡

  በሽታው ሪፖርት ከተደረገባቸው አገሮች የመጡ ተጓዦች የጤና መረጃ ቅጽ ከመሙላታቸው በተጨማሪ ባሉበት ቦታ ለ14 ቀናት በስልክ የሚደረግ የጤና ክትትል ተደርጎላቸው ያጠናቀቁ 756 ሰዎች ሲሆኑ፣ በአሁኑ ወቅት 932ቱ የጤና ክትትል ላይ ይገኛሉ፡፡

   ከዚሁ ጋር በተያያዘም፣ የኮሮና ቫይረስ በሽታ ለመከላከል ክትትል የሚያደርግ ብሔራዊ ሚኒስትሮች ግብረ ኃይል ተቋቁሟል፡፡ ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የሆነው ኮሚቴው፣ ስድስት አባላት ያሉት ሲሆን እነሱም የሰላም ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል፣ የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ፣ የገቢዎች ሚኒስትር ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው፣ የትራንስፖርት ሚኒስትር ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስና የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ሊያ ታደሰ (ዶ/ር) ናቸው፡፡

  ቫይረሱ በ70 አገሮች የተዛመተ ሲሆን፣ ከእነዚህ ውስጥ ስድስቱ የአፍሪካ አገሮች ናይጄሪያ፣ ግብፅ፣ አልጄሪያ፣ ሞሮኮ፣ ቱኒዝያና ሴኔጋል መሆናቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

  የኮሮና ቫይረስ በሽታ (ኮቪድ-19) የዓለም ሥጋት የመሆኑ መጠን ከጊዜ ወደ ጊዜ በመጨመር ላይ ይገኛል፡፡ እስካሁን ባለው መረጃ በበሽታው የተያዙ ሰዎች 80 በመቶ ቀለል ያለ የመተንፈሻ አካል ሕመም፣ 14 በመቶ በከባድና አምስት በመቶ የሚሆኑት ሰዎች በጽኑ እንደሚታመሙ ያመላክታል፡፡ ሕመሙ ዕድሜያቸው በገፉ የማኅበረሰቡ አባላት እንዲሁም የረዥም ጊዜ ታካሚዎች ማለትም የስኳር፣ የግፊት፣ የልብ፣ የኤችአይቪ ኤድስና የካንሰር በሽታ ታካሚዎች ለከፋ የጤና ዕክል ያጋልጣል፡፡ በሽታው ከመተንፈሻ አካል በተጨማሪ የልብና የኩላሊት ሥራ ማቆም በማስከተል ለሞት የሚዳርግ በሽታ ነው፡፡

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  የትርፍ መጠኑን በ127 በመቶ ያሳደገው አቢሲኒያ ባንክ ካፒታሉን በ2.5 ቢሊዮን ብር እንዲያድግ ወሰነ

  የአቢሲኒያ ባንክ ዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩ  ካፒታል በ2.5 ቢሊዮን ብር...

  አዋሽ ባንክ ካፒታሉን 55 ቢሊዮን ብር ለማድረስ ወሰነ

  የአዋሽ ባንክ ዳይሬክተሮች ቦርድ ዛሬ ህዳር 17 ቀን 2015...

  ከብሔራዊ ባንክ እውቅና ያገኘው ፔይሊንክ አክሲዮን ማህበር ምሥረታውን አካሄደ

  ከገንዘብ ንክኪ ነፃ የሆነ የዲጂታል ክፍያ ሥርዓት ለመተግበር ያቀደው...