Wednesday, June 19, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ኢንተርኔት ሶሳይቲ የበይነ መረብ ጉባዔውን በአዲስ አበባ ማካሄድ ጀመረ

spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

በኢትዮጵያ የድርጅቱን ጽሕፈት ቤት ቅርንጫፍ ከፍቷል

ኢንተርኔት ሶሳይቲ የተሰኘው ዓለም አቀፍ የበይነ መረብ ተቋም በኢትዮጵያ የመጀመርያውን የኢንተርኔት ልማት ኮንፈረንስ ከየካቲት 24 ቀን እስከ የካቲት 26 ቀን 2012 . በአዲስ አበባ ማካሄድ ጀምሯል፡፡ 

ማክሰኞ የካቲት 24 ቀን 2012 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ሒልተን መካሄድ የጀረመው ጉባዔ የውጭና የአገር ውስጥ የዘርፉ ባለድርሻዎች እየተሳተፉበት ሲሆን፣ በኢትዮጵያ ለግሉ ዘርፍ ተሳትፎ ክፍት እየተደረገ የመጣው የቴሌኮም ዘርፍ ከወዲሁ እንዲዘጋጅ ለማድረግና የኢንተርኔት ሥርጭትና ተጠቃሚነትን ለማሳደግ ብሎም ዜጎች በርካታ የቢዝነስ አማራጮችን በበይነ መረብ አማካይነት ማንቀሳቀስ የሚችሉበትን ዕድልና ተጠቃሚነት ለማስፋፋት ያለመ ጉባዔ እንደሆነ ከአዘጋጆቹ ተገልጿል።

በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ያለው የኢንተርኔት ስርፀት 18.6 በመቶ እንደሆነ ሲገለጽ፣ ይህም ከመላው አፍሪካ የኢንተርኔት ስርፀት አኳያ ሲታይአማካዩ ደረጃም እንደሚያንስ ታይቷል፡፡ በአፍሪካ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ዕድገት እያስመዘገቡ ከሚገኙ አገሮች መካከል ኢትዮጵያ ተቀዳሚዋመሆኗ፣ ካላት ስትራቴጂካዊና ጂኦግራፊያዊ አቀማመጥ እንዲሁም 105 ሚሊዮን በላይ ከሆነው የሕዝብ ቁጥሯ አኳያ ለኢንተርኔት ስርፀትና ተጠቃሚነት ትልቅ አቅም እንዳላት የጉባዔው አዘጋጆች አስታውቀዋል፡፡ ከሕዝቧ ውስጥ 60 በመቶ በላይ የሚሆነው 30 ዓመት በታች በሆነ የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኝ የወጣት ኃይል በመሆኑ ጭምር፣ ለወጣቶች ሥራ አጥነትመሰል ችግሮች የኢንተርኔትን ተደራሽነትን ማስፋፋት የመንግሥት ስትራቴጂ መሆኑም ይታወቃል።

ምንም እንኳ በአሁኑ ወቅት የሚታው ሥርጭት ዝቅተኛም ቢሆን፣ በኢትዮጵያ የኢንተርኔት ስርፀት በዓመት 45 በመቶ ዕድገት ቢያስመዘግብም ከሌሎች አቻ የአፍሪካ አገሮች ላይ ለመድረስ ግን አሁንም ይቀራታል። በኢትዮጵያ ከሚታዩ የኢንተርኔት ክፍተቶች ከፍተኛውን ቦታ የሚይዙት በአብዛኛው የአገሪቱ ገጠራማ ክፍሎች የኔትወርክ ግንኙነት አለመኖርና 4 አገልግሎት በዋና ከተማዋ ብቻ መገኘት ዋናዎቹ ናቸው። በተጨማሪም ኢትዮጰያውያን ሌሎችዓለም አገሮች ኢኮኖሚያቸውን ለማሳደግና የሕዝቦቻቸውን ሕይወት ለማሻሻል የሚጠቀሙባቸው ከኢንተርኔት ጋር ተያያዥነት ያላቸው አገልግሎቶች እስካሁን ተጠቃሚ መሆን አልቻሉም።

ኮንፈረንሱ ለፖሊሲ አውጪዎች፣ ተቆጣጣሪዎች፣ ቢዝነሶችና ቴክኖሎጂስቶች እንዲሁም አቅሙ ላላቸው ሥራ ፈጣሪዎች ስለ ኢንተርኔት ሞዴልና ቴክኖሎጂ ግንዛቤ በማስጨበጥ  ከሞኖፖል የተላቀቀ ጠንካራ የኢንተርኔት ሥርዓት በኢትዮጵያ እንዲፈጠር ዓላማ እንዳላው ተገልጿል፡፡ በአፍሪካ የኢንተርኔት ሶሳይቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ዳዊት በቀለ በጉባዔው ወቅት እንደገለጹት፣ ከኢትዮጵያ ጠቅላላ ሕዝብ ውስጥ 20 በመቶ ብቻ በኢንተርኔት የተገናኘ በመሆኑ፣ የሕዝቡን ኑሮ ደረጃ ለማሻሻልና የኢንተርኔትን ተደራሽነት ለማስፋፋት ሰፊ ዕድል አለ፡፡

በመሆኑም በኢንተርኔት ተደራሽነት ላ በመሥራት አንጋፋመንግሥታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች መካከል አንዱ የሆነው ይህ ተቋም ከመንግሥትና ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሥራትበማገዝ ሚናው የረዥም ጊዜ ታሪክና ልምድ እንዳለው አቶ ዳዊት ገልጸዋል፡፡ ተቋሙ ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ባገኘው ዕገዛ ጉባዔውን እንዳሰናዳም ጠቅሰዋል፡፡ ወደፊት በትልልቅ ከተሞችና በገጠራማ አካባባቢዎች የኢንተርኔት ተደራሽነት በማስፋፋት የኅብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማሳደግ የሚደረጉ ጥረቶችን ለማገዝ ፍላጎት እንዳለው አስታውቀዋል።

ጉባዔው ከኢንተርኔት አገልግሎትናቴክኖሎጂ ጥራት እንዲሁምስርፀት ጋር በተያያዘ ኢትዮጵያ ሲያጋጥሟት የሚታዩ ዋና ዋና ተግዳሮቶች ላይ ትኩረት በማድረግ፣ አኅጉራዊና ዓለም አቀፋዊ የኢንተርኔት መሠረተ ልማትቶችን በሚገባ መጠቀም የሚያስችሉ መንገዶችን ለማመላከት የሚያግዙ ሐሳቦች እንደሚንሸራሸሩበት ተጠቅሷል፡፡ የኢትዮጵያን የኢንተርኔት መሠረተ ልማት ለማሻሻል የሚረዱ ቴክኒካዊ አማራጮችን ከመዳሰስ ባሻገር፣ የኢንተርኔት ቴክኖሎጂን በማስፋፋት ረገድ ሊያጋጥሙ ስለሚችሉ መሰናክሎችና ሥጋቶች የመፍትሔ ሐሳቦችና ላይ ውይይት ይደረጋል ተብሏል፡፡

የኢንተርኔት ሶሳይቲ የኢትዮጵያ ሕግጋትን መሠረት በማድረግ በኢንተርኔት አጠቃቀም፣ ለውጥና ዕድገት ላይ የሚሠራ ግን ደግሞ ለትርፍ ያልተቋቋመ የኢንተርኔት ሶሳይቲ ኢትዮጵያ ቻፕተር ወይም ተጠሪ ጽሕፈት ቤት መመሥረቱም በጉባዔው ወቅት ይፋ ተደርጓል። ይህ ቻፕተር የኢንተርኔት ሶሳይቲ ‹‹ኢንተርኔት ለሁሉም›› የተሰኘውን ርዕይ የሚያንፀባርቅና ተልዕኮውም የኢንተርኔት ልማትና አጠቃቀምን ለማስፋፋት እንደሆነ ተብራርቷል

የኢንተርኔት ሶሳይቲ ኢትዮጵያ ቻፕተር ፕሬዚዳንት የሆኑት አዱኛ ነቾ፣ ስለ ኢንተርኔት ሶሳይቲ በሰጡት ማብራሪያ፣ የኢንተርኔት ሶሳይቲ የኢትዮጵያ ቻፕተር ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር በመሥራት ለሁሉም ኢትዮጵያዊ፣ ደኅንነቱና አስተማማኝነቱ የተጠበቀ ተደራሽ የኢንተርኔት አገልግሎትን በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ በሚቻልበት መንገድ ላይ ለመሥራት ዝግጁ ስለመሆኑ አስታውቀዋል፡፡ በመሆኑም ማናቸውም የቴክኒክና ቴክኒካዊ ያልሆነ የሙያ ዘርፍ ላይ ዕውቅቱና ልምዱ ያላቸው ግለሰቦች በአባልነት ተቋሙን በመቀላቀልና ዕገዛ እንዲያደርጉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ኢንተርኔት ሶሳይቲ፣ በዘርፉ አንጋፋ ባለሙያዎች በኢንተርኔት አጠቃቀምና ልማት መስክ እንዲሁም በዘርፉ ለውጥን ለማረጋገጥ የሚሠራ ለትርፍ የማይንቀሳቀስ ድርጅት ስለመሆኑ የተቋሙ መረጃዎች ይገልጻሉ፡፡ በመላው ዓለም ባሉት ቻፕተሮቹና አባላቱ አማካይት የኢንተርኔት ደኅንነትን ለማስጠበቅ ከበርካታ ተቋሞች ጋር የሚሠራ ሲሆን፣ ኢንተርኔት ለሁሉም ተደራሽ እንዲሆን የታቀዱ ፖሊሲዎችን በመደገፍ የሚንቀሳቀስ ተቋም ነው፡፡ ኢንተርኔት ሶሳይቲ የኢንተርኔት ምሕንድስና ግብረ ኃይል (Internet Engineering Task Force) የተሰኘውን ተቋም የሚያንቀሳቅስ ድርጅት ነው።

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች