Thursday, June 13, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊሄኒከን ኢትዮጵያ ከ150,000 ሕዝብ በላይ ተጠቃሚ የሚያደርጉ ፕሮጀክቶችን አስረከበ

ሄኒከን ኢትዮጵያ ከ150,000 ሕዝብ በላይ ተጠቃሚ የሚያደርጉ ፕሮጀክቶችን አስረከበ

ቀን:

በታምራት ጌታቸው

ሄንከን ኢትዮጵያ በአዲስ አበባ፣ በሻሸመኔ፣ በሐረርና ቡኖ በደሌ አካባቢዎች ከ150,000 በላይ ሕዝብ ተጠቃሚ የሚያደርጉ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን አጠናቆ አስረከበ፡፡ የተራቆቱና ወኃ አጥ አካባቢዎችን በማልማት ኅብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ፕሮጀክቶችን ለማከናወን ደግሞ ከአጋር አካላት ጋር ተፈራርሟል፡፡

በ1932 ዓ.ም. የተቋቋመውና ዘንድሮ 80ኛ ዓመቱን የያዘው የቅዱስ አማኑኤል የአዕምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከፕሮጀክ ተጠቃሚዎች አንዱ ሲሆን፣ በ2010 ዓ.ም. ብቻ ከተለያዩ የአገሪቷ ክፍሎች ለመጡ ከ221‚007 በላይ የአዕምሮ ሕሙማን በድንገተኛና በተመላላሽ እንዲሁም አስተኝቶ ሕክምና ሰጥቷል፡፡ ሆኖም ሆስፒታሉ ካሉበት በርካታ ችግሮች መካከል የሕክምና መስጫ ክፍሎች እጥረት አንዱ እንደሆነ ከሆስፒታሉ ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡

- Advertisement -

ይህንን ችግር ለመቅረፍ ኢንሼቲቩ በ4.2 ሚሊዮን ብር 520 ሜትር ስኩዌር ስፋት ላይ ያረፈ ሕንፃ አስገንብቷል፡፡ ሕንፃው 23 ክፍሎች ሲኖሩት፣ የሥነ አዕምሮ ድንገተኛ ሕክምና፣ እናቶችና ሕፃናት ጤና ምርመራ እንዲሁም ለፋርማሲ አገልግሎት ይውላል፡፡

ግንባታው ከመካሄዱ በፊት በቀን ከ580 በላይ ተመላላሽ ታካሚዎች በአንድ ክፍል ውስጥ ብቻ ይታከሙ እንደነበር፣ አልፎ አልፎ ሐኪሞቻቸውን የሚደበድቡ ሕሙማን እንደሚያጋጥሙ፣ አዲስ የተሠራው ሕንፃ ችግሩን እንደሚያቃልልና የማምለጫ በር ስላለውም ሐኪሞችን እንደሚታደግ ተነግሯል፡፡

ከዚሁ ጎን ለጎን ‹‹የቡርካ ኢንሼቲቭ›› የተባለውና ለሦስት ዓመት የሚቆየው የ30 ሚሊዮን ብር ፕሮጀክት ስምምነትም ተደርጓል፡፡ የተራቆቱ መሬቶችን መልሶ በማልማት፣ የየአካባቢው ማኅበረሰቦች ከማር፣ ከፍራፍሬ እንዲሁም ከሚመነጨው ውኃ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያደርገውን ፕሮጀክት ለመተግበር ሄንከንና ወርልድ ቪዥን ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

በተደጋጋሚ በድርቅ የሚጠቃውና ከፍተኛ ችግር ያለበት በሐረር የሐኪም ጋራ አካባቢ የሚሠራው ፕሮጀክትም፣ ነዋሪዎች ከሚያገኙት ገቢ በተጨማሪ የተፈጥሮ ሀብትን መልሶ በማልማት እንዲጠቀሙና የትም ሳይሄዱ ውኃ እንዲያገኙ ያስችላቸዋል ተብሏል፡፡

በፊርማ ሥነ ሥርዓቱ ላይ እንደተገለጸው፣ ኦሮሚያ ክልል የሚገኘው ቡኖ በደሌ አካባቢ የሚሠራው ፕሮጀክት ሌላው ነው፡፡ በተደጋጋሚ በድርቅ የሚጠቃውን ኅብረተሰብ ተጠቃሚ ለማድረግ፣ በአካባቢው የሚያልፈውን ደበና ወንዝ በመስኖ በማልማትና የአፈር ዕቀባ በመሥራት መልሶ ጥቅም ላይ እንዲውል ይሠራል፡፡ ይህም ከ120,000 በላይ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ እንደሚደረግ ተገልጿል፡፡

በሻሸመኔ ለስድስት የወጣት ማኅበራትም በ1.2 ሚሊዮን ብር መጋዘንና ወፍጮ ቤት አስገንብቶ አስረክቧል፡፡ የአካባቢው ነዋሪዎችም በአካባቢው ወፍጮ ቤት ባለመኖሩ ችግር እንደነበር ገልጸው፣ ወፍጮ ቤቱ በመብራት ችግር ምክንያት ቶሎ ሥራ ሊጀምር እንደማይችል ሥጋታቸውን ተናግረዋል፡፡

ወደ ኢትዮጵያ ከገባ 11 ዓመቱን ያስቆጠረው ሄኒከን ቢራ ፋብሪካ ከ22 ቢሊዮን ብር በላይ ጠቅላላ ኢንቨስትመንት በማድረግ 2,500 ሠራተኞችን ቀጥሮ እየሠራ እንደሚገኝ የድርጅቱ የውጭ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ፍቃዱ በሻህ ገልጸዋል፡፡

ፋብሪካው ከሚያገኘው ትርፍ ሄኒከን ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ. በ2009 አቋቁሞ፣ ከሰሃራ በታች ላሉ አገሮች በተለይ ጤናን ትኩረት በማድረግ የማኅበረሰብ አገልግሎት እንደሚሰጥም አብራርተዋል፡፡ በኢትዮጵያ እ.ኤ.አ. በ2019 ብቻ ከ51 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ የተለያዩ ሥራዎችን እያከናወነ እንደሆነም ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ በመንግሥት የሚታወጁ ንቅናቄዎችን በተመለከተ ባለቤታቸው ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየሞከሩ ነው]

እኔ ምልህ? እ... ዛሬ ደግሞ ምን ልትይ ነው? ንቅናቄዎችን አላበዙባችሁም? የምን ንቅናቄ? በመንግሥት...

የመንግሥት የ2017 ዓ.ም በጀትና የሚነሱ ጥያቄዎች

የ2017 ዓመት የመንግሥት ረቂቅ በጀት ባለፈው ሳምንት መገባደጃ ለሚኒስትሮች...

ከፖለቲካ አባልነትና ከባንክ ድርሻ ነፃ የሆኑ ቦርድ ዳይሬክተሮችን ያካተተው ብሔራዊ ባንክ ያዘጋጃቸው ረቂቅ አዋጅና መመርያዎች

የኢትዮጵያ የብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ ተቋማትን የተመለከቱት ድንጋጌዎችንና የባንክ ማቋቋሚያ...

የልምድ ልውውጥ!

እነሆ መንገድ ከቦሌ ሜክሲኮ። አንዱ እኮ ነው፣ ‹‹እንደ ሰሞኑ...