Monday, February 26, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊባለፈው ዓመት ዕጣ የወጣባቸው የ20/80 ኮንዶሚኒየም ቤቶች ለዕድለኞች ሊተላለፉ ነው

ባለፈው ዓመት ዕጣ የወጣባቸው የ20/80 ኮንዶሚኒየም ቤቶች ለዕድለኞች ሊተላለፉ ነው

ቀን:

ለክፍላተ ከተሞችና ለወረዳዎች ሹማምንት ጠቀም ያለ ጥቅማ ጥቅም ተከበረላቸው

ከዓመት በፊት የካቲት 27 ቀን 2011 ዓ.ም. ዕጣ የወጣባቸው ከ32,000 በላይ የጋራ መኖሪያ ቤቶች፣ ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ዕጣ ለወጣላቸው ዕድለኞች ሊተላለፉ ነው፡፡

ዕጣው በወጣበት ወቅት ቤቶቹ የተገነቡት በኦሮሚያ ክልል እንደሆነ በመግለጽ ውዝግብ በመነሳቱና ቤቶቹን ማስተላለፍ ባለመቻሉ፣ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርና ከኦሮሚያ ክልል የተውጣጣ ኮሚቴ ተቋቁሞ የተነሳውን የውዥንብርና ውዝግብ በማጥናት፣ የመፍትሔ ሐሳብ እንዲያቀርብ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጭምር ትዕዛዝ መሰጠቱ የሚታወስ ቢሆንም፣ ላለፉት አንድ ዓመት ግን ለሕዝብ ምንም የተገለጸ ነገር አልነበረም፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ኮሚቴው ባደረገው ጥናት ዕጣ ከወጣባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ውስጥ 9,000 ቤቶች በኦሮሚያ ክልል ውስጥ መገንባታቸውን አረጋግጦ፣ ለአስተዳደሩና ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ማቅረቡን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ለሪፖርተር አስረድተዋል፡፡  በመሆኑም በከተማ አስተዳደሩ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር በአቶ ደሳለኝ ተረፈ ፊርማ ሰሞኑን ለአሥሩም ክፍላተ ከተሞች የተላከው ደብዳቤ እንደሚያስረዳው፣ ዕጣ የወጣባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች በተያዘው ወር ዕጣ ለወጣላቸው ሰዎች ይተላለፋሉ፡፡ ነገር ግን በኦሮሚያና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወሰን ላይ የተገነቡ ቤቶች ዕጣ ፈንታ ምን እንደሚሆን ተነጋግሮና መፍትሔ አስቀምጦ ስምምነት ላይ ሳይደረስ፣ ቤቶቹን ለዕድለኞቹ ለማስተላለፍ ውል መፈጸም በቀጣዩ ሒደት ላይ ችግር ሊፈጥር እንደሚችል ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ የኮርፖሬሽኑ ኃላፊዎች ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ ቤቶቹ በሙሉ በከተማ አስተዳደሩ አማካይነት ውል ተፈጽሞባቸው ርክክብ ከተፈጸመ በኋላ፣ ወደፊት የሚያስተዳድራቸው የኦሮሚያ ክልል በመሆኑ እንዴት እንደሚሆን በተለይ ጥናቱን አጥንቶ ያቀረበው ኮሚቴ ሊያብራራ ይገባ እንደነበር ተናግረዋል፡፡

የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ከወጣባቸው በኋላ የዕድለኞች ስም ዝርዝርና ሙሉ መግለጫ የከተማ አስተዳደርሩ ልሳን በሆነው ‹‹አዲስ ልሳን ጋዜጣ›› ይታተም እንደነበር ለ12 ዙሮች የወጡ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ያስታወሱት ኃላፊዎቹ፣ ባለፈው ዓመት በ13ኛው ዙር ዕጣ የወጣባቸውም የጋራ መኖሪያ ቤቶች በተመሳሳይ ሁኔታ ዝርዝሩ እንዲታተም ለአዲስ ልሳን ጋዜጣ የተላከ ቢሆንም፣ በወቅቱ በተፈጠረው ችግር ምክንያት እንዳይታተም መታገዱን አስታውሰዋል፡፡ ነገር ግን አሁን እንዲተላለፍ ከተወሰነ ዝርዝሩ ታትሞ መውጣት እንዳለበት፣ ዋና ጥቅሙም የዕጣው ባለቤቶች ችግር ቢገጥማቸው ማስረጃ ሊሆናቸው እንደሚችልም አክለዋል፡፡

በሌላ በኩል ለሌሎች የመገናኛ ብዙኃን መግለጫው ባይሰጥም እንኳን፣ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ወይም ቢሮው በአስተዳደሩ የመገናኛ ብዙኃን ለመግለጽ ለምን እንዳልፈለገ ግልጽ እንዳልሆነላቸውም ተናግረዋል፡፡

ስለቤቶቹ መተላለፍና አጠቃላይ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን በሚመለከት የኮርፖሬሽኑን ኃላፊዎች ሪፖርተር ለማነጋገር ያደረገው ጥረት አልተሳካም፡፡

በሌላ በኩል ሰሞኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የክፍላተ ከተሞች የፋይናንስ ጽሕፈት ቤቶች ለወረዳዎቻቸው ባስተላለፉት ሰርኩላር እንዳስታወቁት፣ ከየካቲት 1 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆን ለተሿሚዎች ጠቀም ያለ ጥቅማ ጥቅም ተከብሮላቸዋል፡፡

በመሆኑም ለክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈጻሚና በተመሳሳይ ደረጃ ለተሾሙ ኃላፊዎች፣ ምክትል ሥራ አስፈጻሚዎችና በተመሳሳይ ደረጃ ለተሾሙ አፈ ጉባዔ፣ ለክፍለ ከተማው ካቢኔ አባላትና በተመሳሳይ ደረጃ ለተሾሙ የጽሕፈት ቤት ኃላፊዎች ከ5,000 እስከ 9,000 ብር የሚደርስ የቤት አበልና የስልክ ክፍያ እንዲፈጸምላቸው፣ በከንቲባው ጽሕፈት ቤት መወሰኑም ታውቋል፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...