ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን (ማርች ኤይት) ምክንያት በማድረግ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሴቶች ብቻ የሚመራ የበረራ ቡድን፣ የካቲት 28 ቀን 2012 ዓ.ም. በቦይንግ 777 ወደ አሜሪካ መዲና ዋሽንግተን ዲሲ ከተማ ተጉዟል፡፡ ከአዲስ አበባ ሲነሳ ፕሬዚዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ የሸኙት ሲሆን፣ በማግሥቱ ዋሽንግተን ዲሲ ሲደርስ በአሜሪካ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ፍፁም አረጋ አቀባበል አድርገውለታል፡፡ አየር መንገዱ ሃቻምና ማርች ኤይት ሲከበር ወደ አርጀንቲና ቦነስ አይረስ በሴቶች የሚመራ በረራ ማድረጉ ይታወሳል፡፡ ፎቶዎቹ በአዲስ አበባ የነበረው አሸኛኘት ያሳያሉ፡፡