የጋሞ ዞን አስተዳደሪ አቶ ብርሃኑ ዘውዴ፣ የጋሞ አባቶች የሰላም ተምሳሌትነት ለአገር ግንባታ በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀው የባህልና ቋንቋ ሲምፖዚየም ላይ የተናገሩት፡፡ የካቲት 30 ቀን 2012 ዓ.ም. በሚሌኒየም አዳራሽ በተካሄደው ሥነ በዓል ላይ አስተዳዳሪው አክለው እንደተናገሩት ዞኑ ኢትዮጵያውያን በሰላም የሚኖሩበት ነው፡፡ በመድረኩ ላይ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ፣ የሰላም ሚኒስትር ሙፈርያት ካሚል፣ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማና ሌሎችም እንደጋሞ አባቶች ዕርጥብ ሳር ይዘው በመንበርከክ ሰላማዊ ተማፅኖ አቅርበዋል፡፡