Saturday, December 3, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ዜናበፕሬዚዳንቷና በቀድሞው ፕሬዚዳንት የሚመሩ ልዑካን በህዳሴ ግድብ የኢትዮጵያን አቋም ለማስረዳት ተሰማሩ

  በፕሬዚዳንቷና በቀድሞው ፕሬዚዳንት የሚመሩ ልዑካን በህዳሴ ግድብ የኢትዮጵያን አቋም ለማስረዳት ተሰማሩ

  ቀን:

  በፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴና በቀድሞው ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ (ዶ/ር) የሚመሩ ሁለት ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ልዑካን፣ ኢትዮጵያ በህዳሴ ግድቡ ላይ የያዘችውን አቋም ለውጭ መንግሥታት ለማስረዳት ወደ ተለያዩ አገሮች ተሰማሩ፡፡

  የህዳሴ ግድቡን በተመለከተ የኢትዮጵያን አቋም ለተለያዩ አገሮች የማስረዳት ዲፕሎማሲያዊ ተልዕኮ ከሐሙስ መጋቢት 3 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ ወደ ሥምሪት የገባ ሲሆን፣ በፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ የሚመራው ልዑክ ለጉዳዩ ጠቀሜታ ባላቸው የአፍሪካ አገሮች ላይ ትኩረቱን አድርጓል፡፡

  በቀድሞው ፕሬዚዳንት የሚመራው ቡድን ደግሞ ለጉዳዩ ጠቀሜታ ባላቸው የአውሮፓ አገሮች ላይ ትኩረቱን ያደረገ ሲሆን፣ የኢትዮጵያን አቋም ለአሜሪካ መንግሥት ዳግም የማስረዳት ተልዕኮም ለዚሁ ቡድን እንደተሰጠ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ ያመለክታል፡፡

  በፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ የሚመራው ቡድን የመጀመርያ መዳረሻውን ኬንያ በማድረግ፣ ከኬንያ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ጋር ታላቁ የህዳሴ ግድብን በተመለከተ የኢትዮጵያን ፅኑ አቋም ማስረዳቱንና በዚህም የኬንያ መንግሥትን በጎ ምላሽ ማግኘቱ ታውቋል፡፡

  ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅና የኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ በዋናነት በህዳሴ ግድቡ ላይ፣ እንዲሁም በሌሎች የሁለትዮሽ ጉዳዮች ከመከሩ በኋላ በውይይታቸው የደረሱባቸውን መግባባቶች የተመለከተ የጋራ የአቋም መግለጫ አውጥተዋል፡፡

  የአፍሪካ አገሮች የሕዝባቸውን ፍላጎቶች ለማሟላት የተፈጥሮ ሀብታቸውን በዘላቂነት ማልማት እንዳለባቸው የኬንያ መንግሥት በፅኑ እንደሚያምን የገለጹት ፕሬዚዳንት ኡሁሩ፣ የአፍሪካ መንግሥታት የተፈጥሮ ሀብታቸውን ለሕዝባቸው ፍላጎትና ጥቅም ሲያለሙ በምክንያታዊና በፍትሐዊ መርሆች መሆን እንዳለበት እንደሚያምኑም አስታውቀዋል፡፡

  በህዳሴ ግድቡ ግንባታ ድርድር ላይ የተፈጠረውን አለመግባባትም አፍሪካውያን በራሳቸው መፍታት የሚችሉ ስለሆነ፣ የአፍሪካ ኅብረት ይህንን ኃላፊነት እንዲወጣ ጥሪ አድርገዋል፡፡

  የዲፕሎማሲ ጉዟቸውን የቀጠሉት ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዓርብ መጋቢት 4  ቀን 2012 ዓ.ም. ኡጋንዳ የገቡ ሲሆን፣ በዚህም ከፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ጋር ተገናኝተው የተጣለባቸውን ኃላፊነት ተወጥተዋል፡፡

  በእሳቸው የሚመራው የልዑካን ቡድን በቀጣይም በሌሎቹ የዓባይ ተፋሰስ አገሮች ተመሳሳይ ጉብኝት በማድረግ፣ ለአባል አገሮቹ መሪዎች የኢትዮጵያን አቋም እንደሚያስረዳ ይጠበቃል፡፡

  በተመሳሳይ በቀድሞ ፕሬዚዳንት ሙላቱ (ዶ/ር) የተመራው ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ከመጋቢት 3 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ ወደተለያዩ የአውሮፓ አገሮች ተሰማርቷል፡፡  

  በአሁኑ ወቅት የጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ልዩ መልዕክተኛ በመሆን እያገለገሉ የሚገኙት የቀድሞ ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ ከሚጓዙባቸው የአውሮፓ አገሮች መካከል ፈረንሣይ አንዷ ስትሆን ጀርመን፣ ጣሊያንና ሩሲያ ሌሎቹ ናቸው፡፡ በተጨማሪም ለዚሁ ተመሳሳይ ተግባር ወደ አሜሪካ ይጓዛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

  በህዳሴ ግድቡ ላይ ያለውን ውጥረት ለመፍታት ኢትዮጵያ በድርድር ብቻ እንደምታምን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያስታወቀ ሲሆን፣ የውጭ ኃይሎችን ፖለቲካዊ ጣልቃ ገብነት እንደማትፈልግ ነገር ግን አፍሪካውያን ድርድሩን ሊያመቻቹ እንደሚችሉ ጠቁሟል፡፡

  ሰሞኑን ከአልጄዚራ ዓረቢኛ ፕሮግራም ጋር ቃለ ምልልስ ያደረጉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው፣ የግብፅ መንግሥት ጉዳዩን ዓለም አቀፋዊ ለማድረግ የተከተለው መንገድ ተገቢ አለመሆኑን ገልጸዋል፡፡

  የኢትዮጵያ ሉዓላዊነትን በተመለከተ ከኢትዮጵያ ውጪ ማንም ሊወስን እንደማይችል የግብፅ መንግሥት ተገንዝቦ፣ ጉዳዩ በሚመለከታቸው አገሮች ብቻ ወደሚደረግ ድርድር እንዲመለስ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

  የዓረብ አገሮች በህዳሴ ግድቡ ላይ ኢትዮጵያን በማውገዝ ከግብፅ ወገን እንዲሠለፉ ማድረጉ ይታወሳል፡፡ በዚህም የተነሳ ውዝግቡ ከሦስቱ አገሮች በመውጣት ወደ የአፍሪካና የዓረብ አገሮች ውዝግብነት እንዳይሸጋገር የፖለቲካ ተንታኞች ሥጋታቸውን እየገለጹ ነው፡፡   

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  [በተቋሙ ሠራተኞች የተወከሉ አንድ ባልደረባ ሚኒስትሩን ለማነጋገር ቀጠሮ ይዘው ወደ ቢሯቸው ገቡ]

  ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም ሰላም ... ተቀመጥ! አመሠግናለሁ ክቡር ሚኒስትር!...

  የጉራጌ ዞን ጥያቄና የክላስተር አደረጃጀት የገጠመው ተቃውሞ

  መንግሥት የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል አካል የነበሩ ዞኖችንና...

  አዋሽ ባንክ ካፒታሉን ወደ 55 ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ያስገደደው ምክንያት ምንድን ነው?

  ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላላ ጉባዔውን ያካሄደው አዋሽ ባንክ የ43 ቢሊዮን...

  አቢሲኒያ ባንክ ካለፈው ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው ትርፍ በማግኘት አዲስ ታሪክ አስመዘገበ

  አቢሲኒያ ባንክ ከቀደሚ የሒሳብ ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው...